tgoop.com/eiasc1/39
Last Update:
ትኩረት የሚሻው የጉራ ፈርዳው የሰላማዊ ዜጎች ጭፍጨፋ
በቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የአያሌ ንፁኃን ሰዎች ህይወት ማለፉን ከተለያየ አካላት ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ባለፉት ሳምንታት መሰል ጥቃቶች በቤኒሻንጉል ክልል የብዙዎችን ህይወት ቀጥፏል።
በጉራ ፈርዳ ወረዳ በአሮጌ ብርሃን፣ ሹጲ እና ዠኒቃ ቀበሌዎች የደረሰው ጥቃት በኋይማኖት አባት (ቓዲ)፣ ወላድ፣ እርጉዝ እና ህፃናት ሳይቀሩ የተጨፈጨፉበት በመሆኑ ጥቃቱን የከፋ ያደርገዋል።
በዚህ ጥቃት ሳቢያ ከቤታቸው ተፈናቅለው ቢፍቱ ወረዳ አካባቢ ለተጠለሉት ወገኖች ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ስንጠይቅ መንግስት በዚህ እኩይ ወንጀል እጃቸው ያለበትን አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ በማቅረብ በቦታው መረጋጋት የማስፈን ሚናውን በተገቢው ሁኔታ እንዲወጣ እንዲሁም ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን አስቸኳይ እርዳታ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።
በአጠቃላይ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ማንኛውም በንፁኋን ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚቃጡ ጥቃቶች እያወገዘ የሃገሪቱ ህልውና መሰረት የሆኑትን የአብሮነት፣ መከባበርና እና መተዛዘን እሴቶች መመናመንና የስርአት አልበኝነትና ጭካኔ መበራከት ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል።
በመሰረቱ የሰው ልጅ ህይወት (ዘር፣ ጎሳም ሆነ እምነት ሳይልይ) እጅግ የተከበረ እንደመሆኑና የህዝባችን መገለጫ የሆነውን ሰላማዊነት የመጠበቅ የሁሉም ወገን ኋላፊነት ሆኖ የጋራ ሃገር ግንባታ ያለ ሰላም እና ደህንነት የማይታሰብ እንደሆነ እናምናለን።
የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ የመንግስት አካላትና ሌሎች የሚመለከታቸው ወገኖች በዚህ ረገድ የበኩላቸውን ኋላፊነት በመወጣት መሰል ጥቃቶች እንዳይከሰቱ የመፍትሄ መንገዶች ላይ መስራት እንዳለባቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በዚህ ረገድ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በተለይም የአስተዳደር እና ስራ አመራር ቦርዱ የበኩሉን ሚና ለመወጣት ያለውን ዝግጁነት እየገለፀ የትብብር ጥሪውን ያቀርባል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
የስራ አመራር ቦርድ
ጥቅምት 14/ 2013
BY Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
Share with your friend now:
tgoop.com/eiasc1/39