😂አሳዬና ኮሮና ምንና ምን ናቸው?
«በዘውድአለም ታደሠ»
ለውጡ ከመጣ በኋላ ግራ እያጋባኝ ያለው የባልንጀራዬ አሳዬ
ደርቤ ጉዳይ ነው። በአጭር ግዜ ፀጉሩ ሸሽቶ ሸሽቶ ዳርፉር ሊደርስ
ነው። አናቱ ላይ የቀሩት ለነፍሳቸው ያደሩ ሶስት ፀጉሮች ናቸው።
ፖለቲከኛ ከሆነ ወዲህ «ለዚች ሐገር ስል ተመለጥኩ» ይላል አሉ
ትናንት ቤቱ ስሄድ ሶስት ፌስ ማስክ ደራርቦ አድርጎ በላዩ ላይ ጋቢ
ተከናንቦ ሊታከም የሚሄድ ብርድ በሽተኛ ይመስላል። ወደቤቱ
ልገባ ስል ተንደርድሮ መጥቶ በሁለት ሜትር ርቀት አቆመኝና
ሙቀቴን በአይኑ ለመለካት ከሞከረ በኋላ «ሳይህ ኮሮና የያዘህ
አትመስልም ግባ» አለኝ። ጥንቃቄው እየገረመኝ ወደቤቱ ስገባ
ልጆቹን ሳፋ ውስጥ በሳኒታይዘር ዘፍዝፏቸዋል
ገብቼ ሶፋው ላይ ስቀመጥ ሜትር አምጥቶ በጥንቃቄ ለካና
በሁለት ሜትር ርቀት በጥንቃቄ ተቀመጠ። ፍልቅልቋ ባለቤቱ
ከጓዳ መጣችና (ያው የኔ ነገር አይሆንላትም)
«ውይ ዜድዬ መጣህ እንዴ?» ብላ ልትጨብጠኝ ስትጠጋኝ
እንደተቀመጠ ሁለት ሜትር ዘሎ ተጠመጠመባት። ቀልቧ
የተገፈፈው ሚስቱ «ምን ሆነሃል አንተ ሰውዬ?» ስትለው
«በበሽታ ልትጨርሺን ነው እንዴ ሴትዮ የምን ሰላምታ ነው በዚህ
በከፋ ዘመን?» ብሎ እየተንቀተቀጠ ጮኸባት።
የጓደኛዬ አሳዬ ሁኔታ ምንም የጤና አልመሰለኝም። ኮሮና አስም
ያለበትን ሰው የበለጠ ይጎዳል የሚል ወሬ ከሰማ ወዲህ ለሽንት
ራሱ ከክፍሉ አይወጣም። የሆነ በሽታው እሱን ፈልጎ ኢትዮጵያ
የመጣ ነው ያስመሰለው። በዚያ ላይ በሽታውን ይከላከላል የተባለ
ነገር ሁሉ ይሞክራል። እስፖርት ጥሩ ነው ሲባል ከሰማ እዚያው
ሳሎኑ ውስጥ እስፖርት ይሰራል። ሚስቱ እንደነገረቺኝ ከሆነ
ባለፈው ገመድ እዘላለሁ ብሎ በዚያ ቁመቱ ሲዘል የገዛ ገመዱ
ጠልፎት ወድቆ የልጆቹ አምላክ ነው ያተረፈው።
ገዳም ያሉ ሰዎች ፌጦ ነጭ ሽንኩርትና ዚንጅብል በሽታውን
ይከላከላል ብለዋል የሚል ወሬ ሲሰማ አንድ ኪሎ ፌጦ በሁለት
እንጀራ በልቶ የሰውነቱ ሙቀት 45 ዲግሪ ደርሶ ነበር። መከረኛ
ሚስቱ በረዶ ውስጥ ዘፍዝፋው ነው ከሞት የተረፈው። ያም ሆኖ
አልተማረም። መድሃኒት ነው የተባለውን ሁሉ ይበላል። እስካሁን
ያልበላው ያለም ዋንጫ ብቻ ነው። አሁን ደሞ የደምበጫ አረቄ
ጥሩ ነው ብለውት በየቀኑ አንድ ጠርሙስ አረቄ ጨርሶ ያድራል
አሉ። ባለቤቱ እንደነገረቺኝ ከሆነ ተኮራምቶ አረቄውን ይጀምርና
ሞቅ እያለው ሲመጣ ጋቢውንና ፌስ ማስኩን ያወልቃል። ቀን
ሙሉ ሳኒታይዘር ውስጥ የሚዘፈዝፋቸውን መከረኛ ልጆቹንም ከሳፋ
ውስጥ ያወጣል። ወደመስከሩ ሲጠጋ ደግሞ
«ይሁን ብለን ነው እንጂ እንኳን ለኮሮና ለጣሊያንም
አልተንበረከክንም» ብሎ እየፎከረ ከቤት ይወጣና ያገኘውን ሁሉ
ወልዶ እንዳሳደገ ሰው አገላብጦ እየሳመ ዞሮ ዞሮ ይመለሳል
አለችኝ።😂😂
«በዘውድአለም ታደሠ»
ለውጡ ከመጣ በኋላ ግራ እያጋባኝ ያለው የባልንጀራዬ አሳዬ
ደርቤ ጉዳይ ነው። በአጭር ግዜ ፀጉሩ ሸሽቶ ሸሽቶ ዳርፉር ሊደርስ
ነው። አናቱ ላይ የቀሩት ለነፍሳቸው ያደሩ ሶስት ፀጉሮች ናቸው።
ፖለቲከኛ ከሆነ ወዲህ «ለዚች ሐገር ስል ተመለጥኩ» ይላል አሉ
ትናንት ቤቱ ስሄድ ሶስት ፌስ ማስክ ደራርቦ አድርጎ በላዩ ላይ ጋቢ
ተከናንቦ ሊታከም የሚሄድ ብርድ በሽተኛ ይመስላል። ወደቤቱ
ልገባ ስል ተንደርድሮ መጥቶ በሁለት ሜትር ርቀት አቆመኝና
ሙቀቴን በአይኑ ለመለካት ከሞከረ በኋላ «ሳይህ ኮሮና የያዘህ
አትመስልም ግባ» አለኝ። ጥንቃቄው እየገረመኝ ወደቤቱ ስገባ
ልጆቹን ሳፋ ውስጥ በሳኒታይዘር ዘፍዝፏቸዋል
ገብቼ ሶፋው ላይ ስቀመጥ ሜትር አምጥቶ በጥንቃቄ ለካና
በሁለት ሜትር ርቀት በጥንቃቄ ተቀመጠ። ፍልቅልቋ ባለቤቱ
ከጓዳ መጣችና (ያው የኔ ነገር አይሆንላትም)
«ውይ ዜድዬ መጣህ እንዴ?» ብላ ልትጨብጠኝ ስትጠጋኝ
እንደተቀመጠ ሁለት ሜትር ዘሎ ተጠመጠመባት። ቀልቧ
የተገፈፈው ሚስቱ «ምን ሆነሃል አንተ ሰውዬ?» ስትለው
«በበሽታ ልትጨርሺን ነው እንዴ ሴትዮ የምን ሰላምታ ነው በዚህ
በከፋ ዘመን?» ብሎ እየተንቀተቀጠ ጮኸባት።
የጓደኛዬ አሳዬ ሁኔታ ምንም የጤና አልመሰለኝም። ኮሮና አስም
ያለበትን ሰው የበለጠ ይጎዳል የሚል ወሬ ከሰማ ወዲህ ለሽንት
ራሱ ከክፍሉ አይወጣም። የሆነ በሽታው እሱን ፈልጎ ኢትዮጵያ
የመጣ ነው ያስመሰለው። በዚያ ላይ በሽታውን ይከላከላል የተባለ
ነገር ሁሉ ይሞክራል። እስፖርት ጥሩ ነው ሲባል ከሰማ እዚያው
ሳሎኑ ውስጥ እስፖርት ይሰራል። ሚስቱ እንደነገረቺኝ ከሆነ
ባለፈው ገመድ እዘላለሁ ብሎ በዚያ ቁመቱ ሲዘል የገዛ ገመዱ
ጠልፎት ወድቆ የልጆቹ አምላክ ነው ያተረፈው።
ገዳም ያሉ ሰዎች ፌጦ ነጭ ሽንኩርትና ዚንጅብል በሽታውን
ይከላከላል ብለዋል የሚል ወሬ ሲሰማ አንድ ኪሎ ፌጦ በሁለት
እንጀራ በልቶ የሰውነቱ ሙቀት 45 ዲግሪ ደርሶ ነበር። መከረኛ
ሚስቱ በረዶ ውስጥ ዘፍዝፋው ነው ከሞት የተረፈው። ያም ሆኖ
አልተማረም። መድሃኒት ነው የተባለውን ሁሉ ይበላል። እስካሁን
ያልበላው ያለም ዋንጫ ብቻ ነው። አሁን ደሞ የደምበጫ አረቄ
ጥሩ ነው ብለውት በየቀኑ አንድ ጠርሙስ አረቄ ጨርሶ ያድራል
አሉ። ባለቤቱ እንደነገረቺኝ ከሆነ ተኮራምቶ አረቄውን ይጀምርና
ሞቅ እያለው ሲመጣ ጋቢውንና ፌስ ማስኩን ያወልቃል። ቀን
ሙሉ ሳኒታይዘር ውስጥ የሚዘፈዝፋቸውን መከረኛ ልጆቹንም ከሳፋ
ውስጥ ያወጣል። ወደመስከሩ ሲጠጋ ደግሞ
«ይሁን ብለን ነው እንጂ እንኳን ለኮሮና ለጣሊያንም
አልተንበረከክንም» ብሎ እየፎከረ ከቤት ይወጣና ያገኘውን ሁሉ
ወልዶ እንዳሳደገ ሰው አገላብጦ እየሳመ ዞሮ ዞሮ ይመለሳል
አለችኝ።😂😂
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#VIDEO
▂ ▃ ▄ ▅ ▆ ▇ █ █ ▇ ▆ ▅ ▄ ▃ ▂
▂ ▃ ▄ ▅ ▆ ▇ █ █ ▇ ▆ ▅ ▄ ▃ ▂