Telegram Web
የምድር #ባቡር ተሽከርካሪዎችን እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እያጓጓዘ ነው - ከ1940-ዎቹ አጋማሽ እስከ 1950-ዎቹ መጀመሪያ እንደተነሱ የሚገመቱ ፎቶግራፎች

#Flatbed #Freight #Wagons of the Franco Ethiopian #Railway Corporation bringing motor vehicles and construction equipment from the port of Djibouti to Ethiopia possibly in the 1950s/1960s. Source does not tell us the specific year/s
የሀገር ባለውለታ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)
ፍትህ ይፈልጋል!

ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ የተላለፈ አሳሳቢ ጥያቄ

ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛና የኢትዮጵያ ስፖርት ሕያው ቤተ-መጻሕፍት የነበረው ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) አሟሟት ዙሪያ ተገቢው ምርመራ እንዲደረግለት ጥሪ ቀረበ።

📌 የጥያቄው ዋና ነጥብ:

የሀገር ባለውለታ፣
የብዙዎችን ትውልድ ስፖርት ያስተማረውና ስለ እግር ኳስ እድገት ያልደከመው ገነነ መኩሪያ፣ በእርግጥ ራሱን አጥፍቷል በሚል የመጀመሪያ መረጃ ዙሪያ ጥርጣሬዎች መኖራቸውን ምንጮች ይጠቁማሉ።

* የመጀመሪያ ምርመራ ማስረጃ:
በጉዳዩ ላይ የመጀመሪያ ምርመራ ያደረጉ ግለሰቦች እንዳሉት፣ የተገኘው ማስረጃ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ራሱን አጥፍቶ ሞቷል የሚያስብል አለመሆኑን ያሳያል።

* የህዝብ ጥያቄ:
የገነነን ጽሑፍ ያላነበበ የስፖርት አፍቃሪ በሀገሪቱ የለም። ለኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ ግለሰብ ትክክለኛ ፍትህ ሊያገኝ ይገባል።

🚔 ለፖሊስ የቀረበው ልባዊ ልመና:

ለፌዴራል ፖሊስ እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ ይህንን ጉዳይ ከስር ከመሰረቱ እንደ አዲስ እንዲይዙት እና እስከ መጨረሻው አጣርተው፣ ትክክለኛውን የሞት ምክንያት አውጥተው፣ ለኢትዮጵያ ህዝብና ቤተሰቡ ፍትህ እንዲሰጡ በትህትና እንጠይቃለን።

ገነነ መኩሪያ በህይወት እያለ ሀገሩ ባትሸልመውም፣ ቢያንስ ከሞት በኋላ ፍትህን መንፈግ የለባትም።

ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ፍትህ ይገባዋል!
2
አሳዛኝ መረጃ‼️

ከታች ምስሏን የምታዮአት ወጣት እህታችን #liza ትባላለች። በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ትምህርቷን ትከታተል ነበር።

መስከረም 27/2018 ዓ.ም ስልኳን ለማሰራት ከግቢው ወጥታ ሳትመለስ ቀርታለች።

መሰወሯን ተከትሎ በተደረገ ፍለጋም እጅግ አሳዛኝ በሆነ መልኩ የአስገድዶ መድፈር ተፈፅሞባት ተገድላ ተገኝታለች!

ይህቺ እህታችን ፍትህ ታገኝ ዘንድ ድምፅ ልንሆናት ይገባል!

#ፍትህ_ለሊዛ #jusice_for_liza
2
ተጠንቀቁ !!

እዚህ MRI ምሥል ላይ የሞታዩዎትው ሶስት ሰዎች በሙሉ አንድ መኪና ውስጥ ነበሩ። መኪናው አደጋ ደረሰበትና ሁሉም በፅኑ ተጐድተው ሆስፒታል ገቡ ።

ከመካከላቸው አንዳቸውም የደህንነት ቀበቶ ( ሲት ቤልት) አላሰሩም ።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አደጋው በደረሰባቸው ወቅት..

በግራ በኩል ያለው ሰውዬ እግሩን አነባብሮ ነበር የተቀመጠው ።እንደምታዩት የሁለቱም እግሮች የጭን አጥንቶች ተሰባብረዋል ።

መሃል ላይ የሞታዩት ሰውየ ቀበቶ ባያስርም የተቀመጠው ግን በትክክል ነበር - የአንድ እግሩ አጥንቶች ሁለት ቦታ ላይ ተሰብረዋል .. አንድ እግሩ ተርፏል ።

በቀኝ ጥግ ላይ የሞታዩት 3ኛው ግራ እግሩን ዳሽ ቦርድ ላይ አድርጐ ነበር የተቀመጠው .. አደጋው ሲደርስ ውጤቱ ከአጥንቱም አልፎ እግሩን ቆርጦ ጥሎታል።

ወዳጆች ሆይ !
መኪና ስትነዱም ሆነ ስትሳፈሩ ቀበቶ እስሩ! ... መኪና ውስጥ በአግባቡ ተቀመጡ..

ያላችሁ ህይወትና አካል አንድ ብቻ ነው!
2
በሩሲያ ልጅ መውለድ ኢንቨስትመንት ሊሆን ነው

ሩሲያ ቤተሰቦች ልጆች እንዲወልዱ እያበረታታች ሲሆን፤ ለዚህም ሦስት ወይም ከዚያ በላይ ልጆች ለሚወልዱ ቤተሰቦች ብዙ ጥቅማጥቅሞችን አቅርባለች፡፡ ጥቅማጥቅሞቹ የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-

• እስከ 1 ሚሊዮን ሩብልስ የሚደርስ የገንዘብ ጉርሻ

• መኖሪያ ቤት መገንቢያ መሬት

• ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎትና የት/ቤት ምገባ ለልጆች

• ነጻ የሕክምና አገልግሎቶች

• የመብራትና የነዳጅ ክፍያዎች ከቀረጥ ነፃና ቅናሽ

• ዓመታዊ የቤተሰብ ጉዞዎችና የእረፍት ጊዜያት

ይሄ ፖሊሲ ወደፊት ወላጅነትን ወደ ኢንቨስትመንት የሚቀይር ነው ተብሏል፡፡
እናግዛት ነው ታግዘን ነው የሚባለው ...🧐🙆‍♂😭
🏟️ 1284 games played
⚽️ 946 career goals
🏆 35 trophies won
🌕 5 Ballon d’Or won
💰 Billionaire

…but the same 𝐏𝐀𝐒𝐒𝐈𝐎𝐍 as the first day. 🇵🇹
ይህንን ወንድማችንን እንዴት አያችሁት?

ወንድማችን በጣም ሀብታም ነው። ነገር ግን ሀብቱን ሙሉ በሙሉ መቀበል የተቸገርኩበት ምክንያት፣ ያደረገው ጫማ ዋጋ 1 ሚሊዮን ሲሆን፣ ለመቅዶኒያ ሰጠ የተባለው ግን 500 ሺሕ ብር ነው። ወደ 7 ሰዓቱች ያሉት ሲሆን፣ አጠቃላይ ዋጋቸው 400 ሺሕ ዶላር (56 ሚሊዮን ብር) እንደሆነ ተናግሯል።

የ 1 ጫማ እና 7 ሰዓቶች ዋጋ ደምረን 57 ሚሊዮን ብር ከሆነ፣ ሌላውን ቤቱ ይቁጠረው።

ወደ ዋና ጉዳዬ ልሻገር፣ "ይህን ያህል ሀብት ያለው ሰው፣ ለመቅዶኒያ 500 ሺሕ ብር ሰጠ" መባሉ ፌር አይደለም።

ለማንኛውም በወጣ ይተካ ...✌️
"ያንተ ቀን ሲመጣ ወንፊትም ውሀ ይይዝልሀል።"

ጋሽ ኩማ ቶሎ ይባላሉ። በቲክቶክ ከ230 ሺ ሰው በላይ ይከተሏቸዋል። ጋሽ ኩማ በዚህ ዕድሚያቸው ከሱቅ ሆነው ራሳቸውን እየቀረፁ : ኤዲት እያደረጉ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን የሚያሳዩ አዛውንት ናቸው።

በዚህ ዕድሚያቸው ፈታ እያሉ ሰውን ፈታ የሚያደርጉ አባት መሆናቸው ያስገርማል። በተለይ የታወቁት ደሞ " አንተ ጎብዘሀል ዛሬ በጊዜ መጣህ" የሚለው ቪዲዮ ህዝብ ዘንድ በስፋት ተደራሽ ሆኖ ሰውም ወዷቸዋል።

ከዕለታት በአንዱ ቀን ያቺ ደሳሳ ሱቃቸው ባዶ ሆነች : ጎደለች ይህን ያዩ ኢትዮጲያውያን ሱቃቸውን ሞሉላቸው። አሁን አዲስ አበባ መጥተው ማስታወቂያውን ተቆጣጥረውታል።ካልተሳሳትኩ ይህን አባባል ያስታውሰኛል።

"ያንተ ቀን ሲመጣ ወንፊትም ውሀ ይይዝልሀል" የሚለው አባባል ከባይስ ቀጥሎ በእሳቸው ላይም ሰርቷል። ጋሽ ኩማ ይመቾት ...
እኛ ያላፀደቅነው፣ እኛ ያላወቅነው፣ እኛ ያልደረስንበት ሁሉ የሰይጣን ነው ከሚል ሰው ይጠብቃቹህ Manifestation/ The new age movement ሰላቢነት ነው በአጭሩ መሰይጠን ማለት ነው ይሉናል ዶክተሩ

የቀሲስ ዘበነ ዋናው ችግራቸው የሚመስለኝ በዲግሪያቸው ብዛት አዋቂነታቸውን ለመለካት መሞከራቸው፣ በምሁር ነኝ pride መውደቃቸው

ያ ደግሞ እሳቸው የሚያውቁትን ሌላ ሰው የሚያውቅ እንዳይመስላቸው አደረጋቸው። ለዚያ ነው በቃለ መጠይቆቻቸው “ሰው አያውቀውም፣ ብዙ ሰው አያውቀውም” የሚል ነገር ደጋግመው የሚናገሩት።

ሰይፉ ጋር ያደረጉትም ቃለመጠይቅ ላይ Jargon ያበዙት፣ ያልተማሩ ሰዎች አይረዱትም የሚሉት፣ ብዙ ሰው አያውቀውም የሚልን ቃል የሚደጋግሙት በዚህ “የምሁር ነኝ” አደገኛ Pride ስለወደቁ ይመስለኛል።
እንዳያመልጣችሁ : tiktok ላይ ገንዘብ እየታፈሰ ነው ...👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMAX252Rd/
ስልካቸውን ለተቃውሞ ወደ ሜዳ የወረወሩት ደጋፊዎች!

ባሳለፍነው ሳምንት በኤዢያ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የዩኒይትድ አረብ ኤምሬትስ በኳታር አቻው 2-1 በመሸነፍ ከአለም ዋንጫ ውጪ ሆነዋል።

ታዲያ ኳታር ተጉዘው ጨዋታውን ሲመለከቱ የነበሩት የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ደጋፊዎች በውጤቱ በመበሳጨት ስልካቸውን ወደ ሜዳ ሲወረውሩ ተስተውሏል።

ከስልክ በተጨማሪ የውሀ መያዣ ኮርዳ እና ጫማ ጭምር ወደ ሜዳ ተወርውሯል።
“ፌክ ላይፍ ስታይል” እንደ ማስታወቂያ (forex trading)

ፎሬክስ ትሬዲንግ ብዙ ተዋናዮች ያሉበት በቀን እስከ 7 ትሪሊየን እሚነገድበት የአለማችን ትልቁ የፋይናንሻል ገበያ ነው። በክህሎትና በዲሲፒሊን ለነገደበት የሚባለውን ያህል ባይሆንም በረጅም ጊዜ ትርፋማ ሊያደርግ የሚችል ነው።

ፎሬክስ ማስታወቂያ “ስካም” ነው። ጥቂቶች ነግደው በሚያተርፉበት በዚህ ዘርፍ ከ90% በላይ የሆኑት ሪቴይል ትሬደሮች ከስረው የሚወጡበት ነው።

በአለማቀፉ ደረጃ በየዩቱቡ እጅግ ቅንጡ ህይወትን እያሳዩ ህይወታችን በትሬዲንግ እንዲህ ተለወጠ ምን ትጠብቃላችሁ? ይላሉ። እንደዚህ የሚያደርጉ አብዛኛዎቹ ህይወታቸው የተለወጠው ህልምን በመሸጥ እንጂ በትሬዲንግ አይደለም።

- ከፎሬከ‍እስ ደላላዎች ኮሚሽን ለማግኘት በሪፈራል ሊንክ ይጠቀማሉ

- ኮርሶችንና የትሬዲንግ ሲግናሎችን ይሸጣሉ።

- ከ Prof fund firms ኮሚሽን ያገኛሉ

- ከ social media ተመልካች ያገኛሉ

ሰዎች ሚስጥሩን አገኘንው ብለው እንዲያምኑ ያማልላሉ። ሰዎች ለአቋራጭ ሀብት ያላቸውን ጉጉት ተመርኩዘው “ይህን ህይወት ነው የምፈልገው” እንዲሉ የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማሉ።

- መኪናዎችን
- Airbnb villa
- የዲዛይነር ልብሶችን ተከራይተው ቀረፃ ያደርጋሉ

እነዚህ ሰዎችን ስታዩ እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቁ

- ቅንጡ ህይወቱን ለምን ያሳየኛል?

- ሺ ብሮከር በሞላበት ለምን በዚህ ሊንክ ተመዝገብ እያለ ይወተውተኛል?

- 100 ዶላርን ወደ 30ሺ ዶላር መለወጥ የሚችል ከሆነ ወደ ቴሌግራም ቻናሉ እንድቀላቀል ለምን ይወተውተኛል? እሱ ያለውን እያባዛ አይሰራም?

- የሚሊየን ዶላር ሰዓት የሚያደርግ ግለሰብ ለምን ላይክ ሼር ሰብስክራይብ እያለ ይወተውታል?

- በዲሞ አካውንቱ ሳይሆን ለምን ላይቭ ትሬዲንጉን አያሳየኝም?
ከነዚ ፎቶውች ምን እንማር...?

ትናንት በድሮን ሲፈላለጉ ነበር
ዛሬ እጅ ለእጅ ተያይዘዋል ይሳሳቃሉ
ፓርክ እየጎበኙ ይታያሉ

የትናንት አይጥና ድመቶች
ዛሬ እጅና ጓንት ሆነው ተመለከትን!

ዛሬ ጠላቴ ያልነው የነገ ወዳጃችን ከሆነ
ጦርነት እልቂት ለምንስ ያስፈልገናል?

የትናት ወዳጆች በተራቸው ዛሬ ጠላት ሆነዋል

ነገ የትናንት ጠላቶች ወዳጅ ሆነው
ወዳጆች ደግሞ ጠላቶች መሆናቸው አይቀሬ ነው።

እያለ እየተፈራረቀ ይቀጥላል

የሚያልቀውም ማለቁን ይቀጥላል...💔
💯2
ህይወት እንደኖርካት ናት ...😁
2025/10/18 08:38:45
Back to Top
HTML Embed Code: