Telegram Web
I love this ...❤️
Meskel demera...🙏
1
ስፖርትና ፖለቲካ! ራሺያና እስራኤል! ንጉስ ካንቶና

እኔ ኤሪክ ካንቶና እባላለሁ። ለፈረንሣይ ብሄራዊ ቡድንና ለማንቸስተር ዩናይትድ ተጫውቻለሁ። እግር ኳስ ዓለምን በሁሉ መስክ በፖለቲካው በኢኮኖሚው በባህል ያስተሳሰረ ኋያል የዓለማችን ተወዳጁ ስፖርት ነው።

ግን ፍትሃዊነቱን ከቅርብ ግዜ ወዲህ እጠራጠራለሁ ስፖርት በሚፈልገው አንድነት ሁሉን በዕኩል መነፀር በሚያይበት መንፈስ እየተጓዘ ነው ብየም አላምንም።
እግር ኳስ በጠቅላላው በዚህ ወቅት ሚዛኑን አዛብቷል። ፍትህን አጓሏል። ስፖርት እንደ እስራኤል ያሉ ሀገራትን ከመድረኩ ማገድ ነበረበት።

ለምን ካላችሁ? ራሺያ ዩክሬን ላይ ጦርነት ከከፈተች ገና 4ኛ ቀኑ ዓለም ተረባረበባት። ገለልተኞቹ የሚባሉት እንደ FIFA, UEFA, IOC ያሉ የስፖርት ማህበራት ዘመቱባት። ራሺያ ይኸው እስካሁን ከአለም ዋንጫና ከአውሮፓ ውድድሮች እንዲሁም ከታላቁ የኦሎምፒክ ጨዋታ መድረኮች እንደታገደች ክለቦቿ ከማንኛውም ውድድር ተሳትፎ እንደተገለሉም ነው።

716 ቀናት ሙሉ ይኸው ዛሬም ድረስ የማያባራ ጭፍጨፋ በምስኪን ፍልስጤማውያን የምትፈፅመው እስራኤል ግን በሁሉም መስክ በስፖርቱ ትካፈላለች። ክለቦቿ ብሄራዊ ቡድኗ ስፖርተኞቿን ያገለለ የተቃወመ አንዳች ተቋም ወይ ሀገር ግን በምድራችን የለም። እኮ ለምን?

ስፖርት ዘር ሀይማኖት ቀለም የሌለው ሰላምን እኩልነትን ፍትሃዊነትን አንድነትን የሚሰብክ የሰው ልጆች ሁሉ የነፃነት መድረክ ከሆነ እስራዔልን ለምን ዝም አለ?

ለዚህ ነው ስፖርት እግር ኳስ ከወትሮ ድንቅ የሰላም የአንድነት ሁሉን የሰው ልጅ እኩል ከሚመለከትበት መርሁ አፈንግጧል የምለው። በጋራ ትብብር ይህንን ማውገዝ ያስፈልጋል። ስፖርት ያለኛ ደጋፊዎች ምንም ነው። ሀይላችንን ለዕንዲህ ዐይነት 2 መስመር በረገጡ ተግባራት ላይ በአንድነት ማሳየት መቃወም አለብን።
በእርዳታ ስም ኪሳቸውን የሚያደልቡ፣ እፍረት የሌላቸው ደፋሮች።

TikTok ላይ ለሀቅ የሚረዳ ሰው ቢኖር በቁጥር 2 ወይም 3 ብቻ ነው። ፍራኦል ከኪሱ አውጥቶ ለሚረዳው ግን በዚህ ልክ ለምን ዘመቻ እንደተከፈተበት ሊገባኝ አልቻለም። "ካለኝ ላይ ላካፍል፣ ለወገኖቼ ልድረስ..." ብሎ ላለፉት 4 አመታት 2021 ጀምሮ በ TikTok አማካኝነት የበርካቶችን ህይወት አቃንቷል። በእርዳታ ስራ ውስጥ የተሰማሩ እጅግ በርካታ አይን ያወጡ ሌቦች ፊትለፊታችን ቁልጭ ቁልጭ እያሉ በዘርና በሀይማኖት ስለተሸፈኑ ብቻ እነሱ ላሽ ተብለው ፍራኦል ከኪሱ አውጥቶ ለረዳው ግን የማንም አፍ መክፈቻ ሲሆን መመልከት ያናድዳል።
.
የፍራኦል ስም እ'ን'ዲጠለሽ ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት ደግሞ ሚኪ ፊታውራሪና ማስተር አብነት ናቸው። ፍራኦል ለተረጂዎቹ የሚያደርሰው በማስተር አብነትና በፊታውራሪ በኩል ነው። ገንዘብ ለእነሱ ልኮላቸው እነሱ ደግሞ ለተረጂዎች የሚያደርሱት።

ነገር ግን ቃል ለገባላቸው ሰዎች ልኮ [እያንዳንዱን ገንዘብ የላከበት ደረሰኝ አለ] በማስተር አብነት በኩልና በሌሎችም እንዲደርስ የተላከውን ገንዘብ በሚያሳዝንና በሚያሳፍር ሁኔታ ለተረጂዎቹ የሚደርሳቸው ግን ከግማሽ በታች የሆነው ነው። ፍራኦል ለረጅም ጊዜ በእነ ማስተር አብነትና በሌሎች 2 ግለሰቦች ሲዘረፍ ቆይቷል። እከሳቸዋለሁ እያለ ነው፤ ስላጭበረበሩት፣ ስለዘረፉት፣ መጠቀሚያ ስላደረጉት፣ ስሙ እንዲጠፋ ስላደረጉ።

በአሁኑ ሰአት ከገንዘቤም ከስሜም አልሆንኩም እያለ ነው። እስካሁን ድረስ ከ 100ሺ ዶላር በላይ [በአሁኑ ምንዛሬ 16 ሚሊየን ብር] የሚሆን ገንዘብ ለማስተር አብነትና ለሌሎች 2 ግለሰቦች እንደላከ የሚያስረዳ ሰነድ አያይዟል።

ማስተር አብነትንና ሌሎችን በህግ አጠይቃለሁ እያለም ነው። ታዲያ በዚህ ምክንያት TikTokን ትቶ ወደ FB መጥቷል።
ከማስተር አብነት ጋር የሰራነውን በማስረጃ ተማምነን ጨርሰናል አብነት በጨዋነትና በታማኝነትሁሉንም እርዳታዎች በትክክል ለትክክለኛው ተረጂ አድርሷል በተለይ ቦረና ላይ ብዙ ሰርተናል ቀጥል አሁንም አብረህ ነኝ በርታ

Fraol eticha...✌️
ቤቢ ሻወር ...
ሼባ ሻወር ...
🤬2
የ2018 ጎቤ ኮኮብ

በቲክቶክ መጀመሪያ የተለቀቀው ቪዲዮ 3.5 ሚሊዮን ሲታይ ከዛ በኋላ በተለያዩ ሰዎች የተቀረው ቪዲዮ አብዛኛው በሚሊዮን እይታ በማግኘት ተወዳጅነትን ያተረፈ ሙሉ ባንድ የሆነ ሰው ነው።

ባሉካ መቼ ሰጠ ...😂🏆❤️
ውሎ አዳር በሚባል ፕሮግራም ለአመታት ሙሉ ኢትዮጵያን ዞራ የሰራችው አንጋፋና ተወዳጇ ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ ዛሬ ዕውቅና ተሰጥቷታል።

እጅግ ብርቱ ጋዜጠኛ በእውነት ይገባታል። በነገራችን ላይ በየጊዜው በአዲስ አከባቢ ተገኝታ ሰለሚትሰራ ብዙዎች የእሷን ፕሮግራም ይወዱታል።

ውሎ አዳር ለቱሪዝም ዘርፍ የራሱን አስታወፆኦ በእጅጉ ማብከቱም ተዘግቧል።
👍3
ደሃም የዩናይትድ ደጋፊም የሆንኩት እኔ ...🙆‍♂😂😭
Arsenal...❤️
👍2
Wired earphones...😎
ትንሿ ልጄ እግዚአብሔር እንዴት ይሰቀላል? አሸንፈውት ነው? ብላ ጠየቀችኝ።

ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ላይ በንጹህ ፈራጅነቱ የወሰነውን የሞት ፍርድ በራሱ ላይ በዚህ መስቀል ፈጽሞት ሰውን ከሞት ፍርድ ማዳኑን፣ ይህም በገዛ ፍቃዱና እኛን በመውደዱ እንደሆነ አስረዳሁ። እግዚአብሔር ለፍርዱም ለፍቅሩም ታማኝ መሆኑን አስረዳሁ።

ልጆች ስለሞተላቸውና ሞትን አሸንፎ ስለተነሳው ንጉሳቸው እንዲያውቁ ወላጆች መስራት አለብን። የሃይማኖታችን መሰረት ይሄ ነው። መሰረት ላይ የቆመ ህንጻ እንደማይወድቅ እናውቃለን። ይህ የሚያምር መስቀል በውስጡ የተፈጸመውን ሃሳብ ሰው ሁሉ ሊያውቀው ይገባል።
"የመጀመሪያ ፍቅረኛየ ታስጨንቀኝ ነበር።ሁሌ ልምምድ እና ጨዋታ ስለሚኖረኝ ግዜ አልሰጣትም ነበር።አንድ ቀን በብስጭት ጡፋ መጣችና ወይ እኔን ወይ ኳስህን ምረጥ ብላኝ ጥላኝ ሄደች።

አንዳንዴ አስታውሳታለው የመጀመሪያ ፍቅር ከባድ ነው።" ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ
አርቴታ የጦር ጄት ፓይለቶችን ወደልምምድ ሜዳ ሊጋብዝ መሆኑ ተሰምቷል!

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ ሮያል ኤር ፎርስ የተሰኘውን የእንግሊዝ አየር ሀይል ፓይለቶችን ሊጋብዝ መሆኑ ተሰምቷል።

የግብዣው መንስኤም እነዚህ ፓይለቶች በውጊያ ላይ ሆነው የሚግባቡበት መንገድ እጅግ አጭር እና ግልፅ በመሆኑ ተጫዋቾቹም ከነሱ ልምድ በመውሰድ በሜዳ ላይ ያላቸውን መናበብ አንንዲያሻሽሉ በማሰብ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

አርቴታ አምፖልን በመጠቀም የቡድን ህብረትን ከማስረዳት ጀምሮ ቡድኑ በተለያዩ ዘርፎች እንዲሻሻል የተደበቁ ፕሮፌሽናል ስልክ ሰራቂዎችን እስከመቅጠር ለየት ያሉ ነገሮችን እንደሚያደርግ ይታወቃል።
TikTok ላይ Funny content ከሚሰሩ ቲክቶከሮች መካከል ሁልጊዜም ቢሆን አቋሙ የማይወርድ፣ ሁሌም የሚያዝናናኝ እና ፈታ የሚያደርገኝ Tik Toker ቢኖር በርጠሚዮስ ነው። የእሱ sense of Humor ይለያል።

The Best Ethiopian Entertainment Tik Toker of all time ...👑
የሀገሬ ልጅ፣ ዛሬ ያልሆነ ነገ ይሆናል፣ ዛሬ ያልተሳካ ነገ ይሳካል፣ ዛሬ የጠፋ ነገ ይገኛል፣ ዛሬ ያኮረፈህ ነገ ይታረቅሀል፣ ዛሬ የበደለህ ነገ ይክስሀል፣ ዛሬ የጠየመ ነገ ይፈካል! ጊዜ ንጉስ ነው።

ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ይባል የለ? ለጊዜ ዕድል ስጠው፣ ውስጥህ በተስፋ ይሞላ! ወደ ፊት ሂድ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ። በፍጹም
ሶሻል ሚዲያ እገዛ ከጠየቁ ሰዎች መሃል እንደዚህ ልጅ ህዝቡ ውስጥ የገባ የለም። 'ደገፍ አድርጉኝና ልቆስቁሰው። ወንድማችሁ አይደለሁ ?' የምትለዋ ንግግሩ የምትረሳ አይደለችም። እገዛ ፣ ትብብር ለመጠየቅ 'ደገፍ አድርጉኝ...' ማለት ከእሱ በኋላ ተለምዳ ፈምሳለች።

በምን አስታወስኩት ?

በአጋጣሚ ከሆነ ጀለስ ጋር በወሬ ወሬ ስለዚህ ልጅ ተነስቶ ፣ እንዳለው ቃሉን አክብሮ እንደቆሰቆሰው ነገረኝ። ከተማው ላይ አሉ ከሚባሉ የቤት ደላላዎች መሃል አንዱ ሆኗል አለኝ። እንዳለውም ከእራሱ አልፎ ለብዙ ሰዎች የሚተርፍ ባለሃብት እንደሆነ አጫወተኝ !

አይፀዳም ወይ ?

ሶሻል ሚዲያ ላይ አንዴ እገዛ የጠየቁ ሰዎች ሱስ ሆኖባቸው በተደጋጋሚ ህዝቡን በሚያሰለቹበት በዚህ ሰዓት እንደዚህ ለእራስም ለቃልም መታመን መታደል ነው። ጉብዝና ነው። ወንድነትም ጭምር ነው

ከዚህ በላይ ቆስቁሰው ብራዘር ...🏆
1
ዩቲዩብ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍል ነው

ዩቲዩብ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበበትን ክስ ተከትሎ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማማ፡፡

ባለቤትነቱ የጉግል ኩባንያ የሆነው ዩቲዩብ በፈረንጆቹ 2021 ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን ለአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለማስረከብ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ በዋሽንግተን ሁከት በተነሳበት ማግስት የዶናልድ ትራምፕን አካውንት ለቀናት ዘግቶ እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱ የተፈጠረውን ሁኔታ ተከትሎ ከዩቲዩብ በተጨማሪ ኤክስ እና ፌስቡክ የፕሬዚዳንቱን አካውንት በጊዜያዊነት ማገዳቸው ይታወቃል።

ይህንን የኩባንያዎቹን ውሳኔ ተከትሎ ‘ፖለቲካዊ መድሎ ተፈፅሞብኛል’ በሚል ወደ ፍርድ ቤት ያመሩት ዶናልድ ትራምፕ ኩባንያዎቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስወሰን ችለዋል።

በዚህም ጥፋቱን አስቀድሞ ያመነው ዩቲዩብ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ለመክፈል መስማማቱ የተገለፀ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ኤክስ እና ፌስቡክ በፍርድ ቤት የሚወሰንባቸውን የገንዘብ ካሳ ለፕሬዚዳንቱ ይከፍላሉ ተብሏል፡፡

ትራምፕ ከዩቲዩብ ከሚያገኙት ካሳ 22 ሚሊየን ዶላሩን በናሽናል ሞል ትረስት ፈንድ አማካኝነት በነጩ ቤተመንግሥት ለሚገነባው አዲስ አዳራሽ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ነው የተባለው፡፡

ቀሪውን 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ደግሞ የአሜሪካ ኮንሰርቫቲቭ ሕብረትን ጨምሮ የዶናልድ ትራምፕን ክስ ለደገፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በድጋፍ መልክ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡
በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ የ"ፍቅር እስከመቃብር" መጽሐፍ ደራሲን ሀዲስ አለማየሁን ከመጽሐፉ ዋና ገጸባህሪ በዛብህ ጋ በማነጻጸር እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ "... ለምን ሌላ ትዳር ሣይመሰርቱ ከ50 አመታት በላይ ቆዩ? ልጅም እንኳን አልወለዱም?"

የጣት ቀለበታቸውን አሣዩኝ።

"ይሔን ቀለበት ያሰረችልኝ ክበበፀሐይ ናት። እኔም አስሬላታለሁ። እሷ የኔን ሣታወልቀው ነው ያረፈችው። እኔም የእሷን አላወልቀውም። ማንም አያወልቀውም። እሷ ነች ያሰረችልኝ!"

ጥቤ ሲደመድምም፦ "ታዲያ ፍቅር እስከ መቃብር የሚባለው ታሪክ ከሀዲስ ሕይወት ሌላ ምን አለ? ለትዳራቸው እስከ መጨረሻው ድረስ ታማኝ የሆኑ ክስተት ናቸው!!"

ታላቁ ፈተና የሚጽፉትን፣የሚናገሩትን ሆኖ መገኘት ነው!!
1
2025/10/08 11:32:49
Back to Top
HTML Embed Code: