Telegram Web
“ፈጣሪ አለኝ ብለህ በለሊት ጫካ ብትገባ ፈጣሪ አለኝ ብሎ የወጣ ጅብ ይበላሀል"

ፈጣሪህን አትፈታተን...!!!
ቬሮኒካ ከና ለገና የሀበሻን አፍ ፈርታ

'' የጋሽ አዳነ ተካ ወንድም አጎቴ ነዉ ''

ብላ አብራራችልን

እንዲ አስፈሪ ህዝብ ሆነናል ማለት ነዉ...🙆‍♂😭😂
በዐይነ ቁራኛ እየተከታተልናችሁ ነው ...🙆‍♂😝🤣
ተሳዳቢው ማነው ...?👇👇
https://youtu.be/g-kEswx9BKM
እስራኤል የክርስትያን ሀገር አይደለችም ኢራንም አረብ ሀገር አይደለችም !

👉ኢራን አረብ ሀገር አይደለችም። ፐርሺያን ናት። በፐርሺያንና በአረብያን መሀል ሰፊ ልዩነት አለ

👉እስራኤል የክርስትያን ሀገር አይደለችም። ይልቁንም የጂውሾች ሀገር ናት።

👉በእስራኤል ክርስትናም እስልምናም ማይኖሪቲ ናቸው። ግን የሙስሊም ቁጥር ከክርስትያን ይበልጣል። ጅውሽ ባይኖር እስራኤል የሙስሊም ሀገር ትሆን ነበር።

👉ኢራን በአንፃሩ ከእስራኤል በላይ ብዙ ቁጥር ያላቸው ክርስቲያን ዜጎች አሏት።

👉እስራኤል ውስጥ ካሉ ክርስትያኖች ይልቅ አረቦች በቂጥር ይበዛሉ።

👉ክርስቲያንነትን መስበክ ከእስራኤል ይልቅ ኢራን ውስጥ መስበክ እጅግ ቀላል ነው።

👉ኢራኖች ፐርዥያን ወይም ፋርሲን ይናገራሉ እንጂ ጆሯቸው ቢቆረጥ አረቢክ ኣይችሉም። ትንሽ ናቸው ሚችሉት።

👉ኢራን የሙስሊም ሀገር ብትሆንም የሽኣ ሙስሊም ሀገር ናት። እነ ሳውዲ እና ብዙ የእስልምና ሀገራት ሚከተሉት የሱኒ እስልምና ተቃራኒ ናት። በሀገራቱም እንደጠላት ትፈረጃለች። እንደ እስልምና ስጋትም ትታያለች

👉እስራኤል ካሉ የክርስትያን ቤ/ክ በላይ ፍልስጤም ውስጥ ብዙ ቤ/ክ ኣለ። እየሱስም የተወለደው ፍልስጤም ውስጥ ነው።

እና ምን መሰለህ እዚ social media ላይ ሆነህ ክርስትያን ስለሆን እስራኤልን ሙስሊም ስለሆንክ ኢራንን አትደግፍ። መደገፍ ካለብህ ተበዳይን ብቻ ደግፍ። ሲጀመር ጦርነት ሚባል ነገር አትደግፍ። የሰው እልቂት እንጂ ምንም ሚያመጣው ነገር ስለሌለ።
ሚሳኤል ነው ወይስ ስፐርም ነው የሚተኳኮሱት ...🙄😳🙆‍♂
ጆርዲን እና ቲጂ ያደረጉትን የፌሚኒዝም ክርክር አየሁት፡፡ በጣም ደስ ያለኝ እንዲህ አይነት ሴቶች እየመጡ መሆናቸው ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ሀሳባዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የምንከታተለውና የምንማረው ከወንዶች ነበር፡፡ የሁለቱን ክርክር የተከታተልኩት ደግፌም ሆነ ተቃውሜ ሀሳብ ለመስጠት ሳይሆን ለመማር ነው፡፡

በሴቶች ላይ ስታዘበው የነበረው ነገር፤ ጠንካራ ጉዳዮች ላይ አይሳተፉም፡፡ አንባቢ ከተባሉም ብዙዎች የሚያነቡት ልቦለድ ነው፤ የሚያዩት ሮማንቲክ ፊልም ነው፡፡ እንደ ምርምር እና ፖለቲካ ያሉ ጠንካራ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡

ለምሳሌ፤ የግጥም ምሽት እና የፊልም ምርቃት ላይ ብዙ ሴቶች ይገኛሉ፤ ጠንካራ የሚባሉ ጉዳዮች ላይ ግን በጣም ጥቂት ናቸው፤ ጭራሹንም ላይኖሩም ይችላሉ፡፡

የሴቶች እኩልነት የሚመጣው ሴቶች በጠንካራ ጉዳዮች ላይ ሲሳተፉ ነው፡፡ አርዓያ ሆነው ሲታዩ ነው፡፡ አለበለዚያ ‹‹ፌሚኒስት ነኝ›› እያሉ ማውራት ብቻውን ለውጥ አያመጣም፡፡

ፌሚኒስቶች የሚያነሱት ችግር የሚቀረፈው በሴታዊ እንቅስቃሴ አይደለም! ማህበረሰባዊና አገራዊ የአስተሳሰብ መሠልጠን ሲመጣ ነው፡፡ ፌሚኒስቶች የሚያነሱት ችግር የሚቀረፈው አገሪቱ ሰብዓዊ መብት የሚከበርባት አገር ስትሆን ነው፤ ህግና ሥርዓት የሚያከብር መንግሥት እና ሕዝብ ሲፈጠር ነው፡፡

ስለዚህ የሴቶች ትግል መሆን ያለበት እንደ ሴትነት ብቻ ሳይሆን እንደ አጠቃላይ እንደ አገር ነው፤ ለዚህ ደግሞ በጠንካራ ጉዳዮች ላይ ሊሳተፉ ይገባል!
"መምህሩ" ተሐድሶ ያስፈልገናል ብለዋል! (ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ)

" ... ወገኖቼ በጣም ልብ በሉ! ይህ መልዕክት ዛሬም ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ብዙ ትምህርት ይሰጣል ። ኢየሱስን ከማክበር ይልቅ ቅዱሳን መላዕክትን በላቀ ሁኔታ ማክበር የተለየ በረከት ያሰጠናል ብለን ለምናምን ሰዎች አመለካከታችንን እንድናስተካክል ማስተማሪያ ነው፡፡ቅዱሳን መላዕክትን ማክበር ተገቢና በጣምም አስፈላጊ ሥርዐት ነው። በአፋችን ክርስቶስ አምላክ ነው እያልን በተግባር ግን ከክርስቶስ በላይ ለመላዕክት የምንፈጽማቸው ሃይማኖታዊ ተግባራት እንደ አይሁድ ክርስቲያኖች እኛንም ያስወቅሱናል። ብዙዎቻችሁ ታዝባችሁ ይሆናል ዛሬ ኢየሱስ ነው ሲባል ቤተክርስቲያን የሚሄደው ሰው በጣት የሚቆጠር ነው፤ ስለ ኢየሱስ ክብር ሲዘምርና የክርስቶስን ክብር ከፍ አድርጎ ሲገልጽ የሚውለው በጣም ጥቂት ነው።

ዛሬ ገብርኤል ነው፣ ወይም ሚካኤል ነው ሲባል ግን በየቤተክርስቲያኑ የሚተመውን ሕዝብ ስንመለከትና ከክርስቶስ በላይ ለመላዕክቱ ሲዘምር፣ እልል ሲል፣ ሲመሰክር የሚውለውን ሕዝብ ግን ስንመለከት ለክርስቶስ በልባችን የሰጠነው ቦታ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ ማሳያ ነው። እንደ አይሁድ በደሙ ካገኘነው ጽድቅ ይልቅ በሥጋዊ ሕይወታችን ያገኘናቸው ስጦታዎች እጅግ እንደላቁብን ማሳያ ነውና ሁላችን መዳንን እንወርስ ዘንድ ሕይወቱን በመስቀል የሰጠንን ጌታ ከማንም በላይ አልቀን በልባችን ዙፋን ላይ ልናነግሥ ይገባል።

ክብርና ምሥጋና አምልኮና ጌትነት ለታረደው በግ ይሁን።"

("መምህር" ታሪኩ አበራ)
አስጌ ሳትሆን አሽቄ ብለንሀል...😝😁🙆‍♂
ለህክምና ባለሙያዎች ጥያቄ ድጋፉን የገለጸው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ታገደ

በቅርቡ የጤና ባለሙያዎች ያደረጉትን ስራ የማቆም አድማ ተከትሎ አመራሩ ታስረውበት የነበረው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር መታገዱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

እግዱ የተላለፈው ከኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን በኩል መሆኑን የገለጹት አቶ ዮናታን የእግድ ደብዳቤው ላይ “ጠቅላላ ጉባኤ አላካሄዳችሁም፣ የፋይናንስ ሪፖርት አላቀረባችሁም” የሚሉ ክሶች መነሳታቸውን ተናግረዋል።

አቶ ዮናታን አያይዘውም፤ "በመመሪያ እና የሀገሪቱ ህግ በሚፈቅደው ነው የተንቀሳቀስነው ከዛ ውጪ ያደረግነው ነገር የለም" ሲሉ ጠቅሰው፤ እግዱ በዋነኝነት ከጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ ጋር የተገናኘ ነው ብለው እንደሚያምኑ" አስታውቀዋል።

ማህበሩ የተመሰረተበት ዓላማ "ለጤና ባለሙያዎች ድምጽ ለመሆን ነው" ሲሉ ገልጸው ጤና ባለሙያዎች "ተገቢውን ቦታ እንዲያገኙ እና በሰሩት ልክ እንዲከፈላቸው ነው ድምጽ ስናሰማ የቆየነው" ብለዋል።
እግረኞች ከቤት ስትወጡ ይቺን ነገር አንብባችሁ ውጡ ...✌️
አይ አስጌ ካንተ ምን ይጠበቃል ...😳🙆‍♂😂
ህግ ትምህርት ቤት እያለሁ ስለ መሰማት መብት "right to be heard" ስንማር

መምህሬ የነገረን ሁሌም የማስታውሳት አንድ እውነታን ደጋግሞ ይነግረን ነበር።

ሁሉን አዋቂው (Omniscience ) የሆነው እግዚአብሄርም አዳም ፍሬውን እንደበላ እያወቀ እንኳ "...ፍሬውን በላህ ወይ..." በማለት ጠይቆ የአዳምን የመሰማት መብቱን አክብሮለት ነበር ይለናል።

እውነት ነው። አምላክ የመሰማትን መብት አልነፈገም። በፍጥረት ጅማሬ ያከበረው መብትም ይሄን መብት ይመስለኛል።

ብሄራዊ ጀግናችን ገለቴ ቡርቃ በህይወቷ ስለሆነው ነገር ባዝንም በዛኛው ወገን ያለው ሳልሰማ አስተያየት መስጠት አልፈልግም።

ሁሉም ወገን ይሰማ ከማለት ውጪ። ከሁለት ወገን ሳይሰሙ ከውሳኔ መድረስ የደቦ ፍርድ ነው።

- ብስራት መለሰ (የፋና ጋዜጠኛ) ...🏆👏✌️
ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት ከአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ መያዟን ሪፖርት አመላከተ

ኢትዮጵያ ለመኖር እጅግ ውድ ከሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች መካከል ቀዳሚ ደረጃ ስትይዝ ከዓለም 53ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ሪፖርት አመላከተ።

የዓለማችን ትልቁ የኑሮ ውድነት የመረጃ ቋት ባወጣው አዲስ ሪፖርት እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያውያን አሁን ላይ እንደ ምግብ እና ትራንስፖርት ባሉ መሰረታዊ ነገሮች ላይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ዜጎች የበለጠ ገንዘባቸውን ያወጣሉ።

በሪፖርቱ መሰረት፣ በኑሮ ውድነት ኢትዮጵያ ከዓለም 53ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው 46.5 የኑሮ ውድነት ጠቋሚ ነጥብ በመስመዝገብ ሲሆን፣ ይህም አፍሪካ ውስጥ ካሉ አገሮች ሁሉ ከፍተኛው ነው።

በሀገሪቱ የሚታየው የሸቀጦች ዋጋ መወደድ በኑሮ ውድነት ደረጃ አንደኛ እንድትሆን ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። ይህም በተለይ በቋሚ ወይም በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ ሰዎች ሳምንታዊ ወጪያቸውን ለመሸፈን እየከበዳቸው መምጣቱን የሚያሳይ ነው መባሉን ኤፒኤ ኒውስ ዘግቧል።
ቱሪዝም የገባት ሳውዲ

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (UAE) ለክርስቲያኖ ሮናልዶ የክብር ሃውልት ለማቆም ሽር ጉድ መጀመሯን አሳውቃለች በዛሬው ዕለትም መሰረት መጣሉ ተገልጿል ይላል ዜናው

ነገ ከነገወዲያ ሳውዲን ለመጎብኘት የሚሄድ የሮናልዶ አድናቂ ቱሪስት የሮናልዶን ሃውልት ለማየት አብሮ ሰልፊ ፎቶ ለመነሳት አንድ ቱሪስት ቢያንስ ሊቆይበት ካሰበው ቀን 1 ቀን ሊያራዝም ይችላል

ከእያንዳንዱ የጎብኝ ቆይታ ሳውዴ ዶላሯን ታፍሳለች

ኢትዮጲያስ ?

የቦብ ማርሌን ሃውልትን አፍርሳ ጥሻ ውስጥ ትጥለዋለች በዓለም በሰብአዊ እርዳታ የሚታወቁትን የስንቱን ድሃ ችግር የቀረፉትን የኢትዮጵያ ባለውለታን የካርል ሃይንዝቦምን ሃውልት እና በስማቸው የሰየመውን አደባባይ አፍርሳ ሃውልቱን ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ትከተዋለች

አፍራሽ የሆነ ትውልድ
ማን ነው ስምህ ?
አፍራሽ ነው ያለው ፓስተሩ
ከሺህ ቃላት

ይቺ ፎቶ ድምጽ አላት!
ጌታ ሆይ ብቻ እየለየህ... እንደው ዝም ብለህ እንዳታጭደን...😳🙆‍♂😭
2025/06/26 16:54:00
Back to Top
HTML Embed Code: