Telegram Web
በሃይማኖት ስም፤ ህዝብን ማታለልና መበዝበዝ የነበረና ያለ ነገር ነው፤ በማህበረሰብ ውስጥ ማምረት የተሳናቸው ነቀዞች "የግዜር ወኪል ነን" ብለው አምራቹን ባላገር ሲዘርፉት ኖረዋል

የተሰበሰበው ህዝብስ በዚህ መጠን ተላላ መሆኑ “ምድር ተከፍታ ብትውጠኝ” አያሰኝም? ወይስ ሁሉም የቀሽም ተውኔቱ ተካፋይና ተጠቃሚ ነው?

የሚገርመው፤ ሁሌም አንድ “ተአምር” ከታየ በሁዋላ ታምረኞች ሩምታ መዝሙር ከመድረክ ይለቃሉ፤ የሩምታው መዝሙር አላማ ምእመኑ ተረጋግቶ እንዳያስብ፤እንዳይመዝን ልቡን መስለብ ነው፤ ባገራችን፤ የእምነት ተግባር ዜጎች መልካም ምግባር እንዲላበሱ ማድረግ መሆኑ ተረስቱዋል፤ የተእምራት ስራ ባብዛኛው ፤ አጋንንትን በማውጣትና በሽተኛ በመፈወስ ዙርያ ታጥሮ ቆይቱዋል፤ እኒህ ነገሮች ለማጭበርበርና ለማደናገር የተመቹ ናቸው፤

በከተማችን እንደ ክረምት ሙጃ የፈሉት ነብያት የሚሰሩት ብቸኛ ታእምር ካለ፤ አንድ ማይክ እና የላብ ማበሻ ቁራጭ መሃረብ ይዘው ፤ ባጭር ጊዜ ውስጥ ሃብታም መሆናቸው ነው፤ በተረፈ ምንም አይነት ልእለ-ስብ ችሎታ የላቸውም፤ አለን ካሉ ደግሞ የሚከተሉትን ነገሮች ሰርተው ያሳዩኝ!

-አምስት እንጀራውን ባርከው በአምስት ሚሊዮን አባዝተው ፤ የተራቡ ወገኖቻችንን ሲመግቡ ያሳዩኝ!

-ኢየሱስ በቃና ዘገሊላ እንዳደረገው፤ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ ይቀይሩልን፤ ኢትዮጵያ የለገዳዲን ወንዝ እንደ ስሙ፤ ወደ ወይን ጠጅ ቀይራ ለውጭ ገበያ እንድታቀርብና እንድትከብር ያድርጉ!

-ሙሴ እንዳደረገው በውሃ ላይ ሰልጥነው ያሳዩን፤ አባይን በነፋስ አውታር አስረው ይገድቡልን፤

-ኢየሱስ እንዳደረገው፤ ሙታንን ያስነሱልኝ! ለናሙና ያክል ይድነቃቸው ተሰማን፤ አበበ ቢቂላን፤ ድምፃዊ ንግስት አበበን ፤ ተስፋየ ካሳን ይቀስቅሱልኝ ፤ ሌላው ቀስ ብሎ ይደርሳል
ቆይ ግን መንፈሳቸውን ነው እንዴ የምትስለው...🙄🙆‍♂😭
ቤት ተለቆ ሊመስልህ ይችላል... ግን ትራፊኮች ከታክሲዎች ያወጡት የትርፍ መጫኛ ወንበሮች ናቸው...😳🙆‍♂😂
ጀለስ: ሴት ማለት ምን ማለት ነው?

ጆርዲ: ጡት ያላት ምናምን...

...💀🙆‍♂😝
በዚህ ሰምንት ምቾት የነሳኝ አንዱ ጉዳይ ይህ ለሐጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ በስሙ በተቋቋመው ፋውንዴሽን የሚዘጋጀው ሽልማት ነው። ፋውንዴሽኑ በተለያዩ ዘርፎች የዘንድሮ ዕጩዎችን ይፋ አድርጓል። የእጩዎቹ ዝርዝር አስደንግጦኛል።

ድምፃዊ አንዷለም ጎሣ በሶስት ይሁን በአራት ዘርፍ ለሽልማት ታጭቷል። እንደኔ እንደኔ የአንዷለም መታጨት በደንብ መጤን አለበት። ሲለ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን ሲለ ፍትሕ እና ሞራል'ም መታሰብ አለበት። ለቀነኒ ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ መንገድ ሕይወታቸውን ላጡ ሴቶች ነፍስ ዋጋ መስጠት እና አጋርነት ማሳየትም ይገባል። ደግሞም ከየትኛውም '' ወርቅ ሙዚቃ '' የሰው ነፍስ በላጭ መሆኗን አንዘንጋ። በዚህ ላይ አንድ ለፍትሕ ሲታገል በኖረ እና እራሱም ፍትሕን በተነፈገ ሰው ስም የተሰየመ ተቋም ሁልጊዜም ሲለ ፍትሕ መጮኽ እና ከተበዳይ ጎን የመቆም ሞራላዊ ግዴታ አለበት።

በመሆኑም ነገሮች በደንብ ጠርቶ...እውነት እስክትወጣ አንዷለም ወደዚህኛው ሽልማት ባይጠራ [ባይታጭ] እላለሁ...

[ ይህ ነገር ካልተስተካከለ ለፍትሕ እቆማለሁ የሚል ሰው በዚህ መድረክ ላይ መገኘት የለበትም ]።
የዛሬ አመት አካባቢ ነበር ይቺ ብራዚላዊት በነበረባት የቆዳ ህመም ምክንያት ከቤት እንደማትወጣና ከህመሙ በላይ ብቸኝነት እየጎዳት እንደሆነ በፌስቡክ ገጿ ላይ በፃፈችው ፖስት ስር ሺዎች ኮሜንት ጥሩ ያልሆነ ልብ ሰባሪ ነበር

አንድ ኮሜንትና አንድ ሰው ግን ያልጠበቀችው ነበር ሊያገኛት እንደሚፈልግ ሲነግራት አላመነችም ከብዙ ተማፅኖ በኋላ አገኘችው እኔ አለሁልሽ ብሎ አብሯት ለመኖር ለጋብቻ ጠየቃት ከጋብቻ ፎቶዋ በኋላ ጠፍታ ዛሬ ደሞ ድጋሚ የልጅ እናት ሆና ብቅ ብላ እንደገና መነጋገሪያ ሆናለች።

ሰው የሚለው አያጣምና ሀላፊነት የጎደለው እናትነት ነው መልኳ ህፃኑን ያስፈራራል እያሉ አባቱን ሳይቀር ልብ የሚሰብር አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ ...😢🤷‍♂💔
ለጥንቃቄ ⚠️ ⛔️

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ከሚገኙ ካፌዎች በአንዱ፣ አንድ ኩባያ ዝንጅብል ሻይ አስገራሚ ዋጋ - 659 ብር እየተሸጠ ነው።

ስለዚህ፣

* ቦታው ያምራል፣
* ቡና ልጠጣ"

ብላችሁ ወደ እነዚህ ካፌዎች ከመግባታችሁ በፊት ዋጋቸውን እንድትጠይቁ እና ጥንቃቄ እንድታደርጉ እያሳሰብን ነው።

ያለፍላጎት ውድ ዋጋ ከፍላችሁ እንዳትገረሙ!

©️ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም.
በቀኝ አውለኝ ...🤲🙆‍♂😭
ምስኪን የቀን ሰራተኞች ህይወት እያለፈ የሚገኝበት ግንባታ ስፍራ

በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ እየተገነባ በሚገኘው አያት ሪል እስቴት ላይ በግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት ሠራተኞች፤ ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወት ማለፋን አሐዱ ከቦታው ተገኝቶ ማረጋገጥ ችሏል።

አደጋው የደረሰው በልስን ሥራ ላይ ተሠማርተው በነበሩ ሠራተኞች ላይ ሲሆን፤ ሁለት ሠራተኞች ከሕንጻው 4ተኛ ፎቅ ላይ ሆነው የልስን ሥራ በማከናወን ላይ ሳሉ የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦው በመበጠሱ አደጋው ደርሷል።

በወቅቱም ከሕንጻው ስር በመጎዝ ላይ የነበረ አንድ ሠራተኛ ዊንቹ ወድቆበት ወዲያውኑ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፤ ከወደቁት ሁለት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ሠራተኛም በተመሳሳይ ወዲያው ሕይወቱ አልፏል።

የልስን ሥራ ሲሰራ የነበረው አንዱ ሠራተኛ ደግሞ፤ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ለሕክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

በትናትናው ዕለትም 4 የቀን ሥራ ሠራተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሪል እስቴቱ ሕንጻ ላይ ወድቀው ሁለት ሠራተኞች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በሁለቱ ሠራተኞች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አሐዱ ያነጋገራቸው የሪል እስቴቱ የግንባታ ሠራተኞች ገልጸዋል።

እንዲሁም ከትናንት በስተያ ሐሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አምስት የግንባታ ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ መውደቃቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የሁለቱ ሠራተኞች ሕይወት ሲያልፍ በሦስቱ ሠራተኞች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

በሕንጻው ግንባታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች በተደጋጋሚ ተመሳሳይ አደጋ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ አሐዱ የገለጹ ሲሆን፤ በሳምንት አንድ ወይ ሁለት ሠራተኞች አደጋ እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

ሠራተኞቹ አክለውም፤ ሪል እስቴቱ በሠራተኞች ደህንነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሰይፉ ያን የሚያክል ሾው ላይ አቅርቦትም ልጁ ሊምረው አልቻለም ...🙆‍♂😝😂
እረ በስመአብ ...🙆‍♂😭😝
"ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን፡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ"

ሮሜ 8÷35-39።
ሰላም እደሩልኝ ...😭
ካሜሩን ዲያዝ ትባላለች። አሜሪካ ውስጥ ስመጥር ከሚባሉ ሰዎች ተርታ የምትሰለፍ ናት። ተዋናይት፣ፀሐፊ፣ስራ ፈጣሪ እና ሞዴሊስት ናት።

እና እቺ ስመጥር፣ሀብታም ሴት በህይወቷ ሜካፕ የሚባል ፊቷን አስነክታው አታቅም። ለምን እንደሆነ ስትጠየቅም የኔ ያለሆነውን ወጣትነት ከማየው፣የራሴን እርጅና ባየው እመርጣለሁ ነበር ያለችው።

ዛሬ ላይ 53 አመቷ ቢሆንም እንደሚታየው ግርማሞገስ ያላት ወይዘሮ ናት።
2025/06/26 21:37:34
Back to Top
HTML Embed Code: