Telegram Web
በቀኝ አውለኝ ...🤲🙆‍♂😭
ምስኪን የቀን ሰራተኞች ህይወት እያለፈ የሚገኝበት ግንባታ ስፍራ

በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ እየተገነባ በሚገኘው አያት ሪል እስቴት ላይ በግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት ሠራተኞች፤ ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወት ማለፋን አሐዱ ከቦታው ተገኝቶ ማረጋገጥ ችሏል።

አደጋው የደረሰው በልስን ሥራ ላይ ተሠማርተው በነበሩ ሠራተኞች ላይ ሲሆን፤ ሁለት ሠራተኞች ከሕንጻው 4ተኛ ፎቅ ላይ ሆነው የልስን ሥራ በማከናወን ላይ ሳሉ የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦው በመበጠሱ አደጋው ደርሷል።

በወቅቱም ከሕንጻው ስር በመጎዝ ላይ የነበረ አንድ ሠራተኛ ዊንቹ ወድቆበት ወዲያውኑ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፤ ከወደቁት ሁለት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ሠራተኛም በተመሳሳይ ወዲያው ሕይወቱ አልፏል።

የልስን ሥራ ሲሰራ የነበረው አንዱ ሠራተኛ ደግሞ፤ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ለሕክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

በትናትናው ዕለትም 4 የቀን ሥራ ሠራተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሪል እስቴቱ ሕንጻ ላይ ወድቀው ሁለት ሠራተኞች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በሁለቱ ሠራተኞች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አሐዱ ያነጋገራቸው የሪል እስቴቱ የግንባታ ሠራተኞች ገልጸዋል።

እንዲሁም ከትናንት በስተያ ሐሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አምስት የግንባታ ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ መውደቃቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የሁለቱ ሠራተኞች ሕይወት ሲያልፍ በሦስቱ ሠራተኞች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

በሕንጻው ግንባታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች በተደጋጋሚ ተመሳሳይ አደጋ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ አሐዱ የገለጹ ሲሆን፤ በሳምንት አንድ ወይ ሁለት ሠራተኞች አደጋ እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

ሠራተኞቹ አክለውም፤ ሪል እስቴቱ በሠራተኞች ደህንነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሰይፉ ያን የሚያክል ሾው ላይ አቅርቦትም ልጁ ሊምረው አልቻለም ...🙆‍♂😝😂
እረ በስመአብ ...🙆‍♂😭😝
"ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን፡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ"

ሮሜ 8÷35-39።
ሰላም እደሩልኝ ...😭
ካሜሩን ዲያዝ ትባላለች። አሜሪካ ውስጥ ስመጥር ከሚባሉ ሰዎች ተርታ የምትሰለፍ ናት። ተዋናይት፣ፀሐፊ፣ስራ ፈጣሪ እና ሞዴሊስት ናት።

እና እቺ ስመጥር፣ሀብታም ሴት በህይወቷ ሜካፕ የሚባል ፊቷን አስነክታው አታቅም። ለምን እንደሆነ ስትጠየቅም የኔ ያለሆነውን ወጣትነት ከማየው፣የራሴን እርጅና ባየው እመርጣለሁ ነበር ያለችው።

ዛሬ ላይ 53 አመቷ ቢሆንም እንደሚታየው ግርማሞገስ ያላት ወይዘሮ ናት።
Wow...😃❤️🇪🇹
ሶስቴ የተወለደችው ልጅ

የ16 ሳምንት እድሜ ሁኗት የእናቷ ሆድ ውስጥ እያለች ዶክተሮች አስደንጋጭ ነገር ተመለከቱ። የመቀመጫዋ አጥንት(tailbone) ላይ ትልቅ ዕጢ እያደገ ነው። ያ ደግሞ ትንሽ ከቆየ እዛው እያለች ይገላታል። ስለዚህ ዶ/ሮች አውጥተው በቀዶ ጥገና ዕጢውን አስወግደው ጊዜዋ ደርሶ ወደ ምድር በሙሉ ጊዜ ለመኖር እስክትመጣ መልሰው የናቷ ሆድ ውስጥ አስገቧት።

እንዲሁም 23 ሳምንት ሲሆናት በልብ ችግር ለመሞት ተቃረበች በዚህ ሰዓት የቴክሳስ ህፃናት ሆስፒታል ዶ/ሮች የማይቻል የሚመስለውን ነገር አደረጉ። ለሁለተኛ ጊዜ ህፃኗን ከእናቷ ሆድ በከፊል አውጥተው አክመው ወደ ቦታዋ መለሷት።

ለ3ኛ ጊዜ ጊዜዋ ሲደርስ ተወልዳ በጤና እየኖረች ትገኛለች።

ፈጣሪ አትሙች ያላትን ነብስ ከአንበሳ መንጋጋ ያወጣታል፣ እቶኑን እሳት ያቀዘቅዘዋል። ለሱ ምን ይሳነዋል።
የታሪክ ማስታወሻ
ሻምበል አበበ ቢቂላ ከዉድ ቤተሰቡ ጋር ...❤️
አትግደሉብን !!

አለም በቃኝ ብለው እግዚአብሄርን ለማገልገል የመነኑትን በመ*ግ**ደል የሚገኝ ፅድቅ ሆነ የፓለቲካ ትርፍ የለም አትግደሉብን ...!
ቀሲስ ደበበ እስጢፋኖስ በሰሜን አሜሪካ ቨርጂንያ የደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ካህን ዛሬ ዘማሪት ዮርዳኖስ ደረጀ በ SHEGER INFO ላይ በመቅረብ ስሙን አንስታ ከ16 ዓመት በፊት በአገልግሎት ላይ በትራስ አፍኖ ፡ ደፍሮኛል ስትል ክስ አቅርባለች።

በዚህም ተግባር አስረግዞኝ አሁን ቁርጥ እርሱን የሚመስል የ15ዓመት ልጅ ይዤ ኑሮ ከብዶኝ ለጐዳና ህይወት ልወጣ ነውና ልጁን አምኖ በመቀበል ተገቢውን ድጋፍ ያድርግልኝ ካልሆነም የልጅነት ማረጋገጫ ምርመራ(DNA)ተደርጐ ቁርጡ ይታወቅ ስትል በአደባባይ ጠይቃለች። እውነት መምህሩ ይህንን የረከሰ ተግባር ፈፅመው ከሆነ የደ*ፈ*ሩ*ት ዘማሪዋን ብቻ ሳይሆን ቤተ ዕምነቷን፣መቅደሱን እንዲሁም መላውን ምዕመን ነው። መምህሩ ደግሞ ድርጊቱን ሳይፈፅሙት ከሆነ ይህ ክስ የቀረበው በሀሰት የተከሰሱት እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ቤተ ክርስቲያኗም ናትና ጉዳዩን በአስቸኳይ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል።
ልክ እንደ cafe, restaurant እና hotel ለ social media influencer tip መስጠት ተጀምሯል።

ለመቀበል account ይክፈቱ ...👇👇👇
https://jami.bio/sign-up?referrer=tesfa
ቀሲስ ደበበ እስጢፋኖስ የተከሰሱበት ታዳጊ አብለኔሲል በፎቶ ይህን ይመስላል።
ፍርዱን ለእናንተ!!!!
2025/06/26 01:36:36
Back to Top
HTML Embed Code: