Telegram Web
የዚህን ወጣት ታሪክ 💔

የተወለደው ከደሃ ቤተሰብ ነው፣ ለችግር እጅ ያልሰጠው ወጣቱ እስከ 10ኛ ክፍል በጥሩ ውጤት በማጠናቀቅ ማትሪክ ተፈተነ።

ወደ ዩኒቨርሲቲ ቢሄድ ምኞቱ ነበር ግን የሚያስተምረው የሚደግፈው ሰው ያስፈልጓል አዲስ አበባ የሚገኝ ዘመዱን እንዲረዳው ጠየቀው ፕሪፓራቶሪ ከምትገባ ዲፕሎማ ተወዳደር ብሎ ምላሽ ሰጠው።

ዩኒቨርሲቲ የመማር ህልሙ ተጨናገፈ ያለው አማራጭ ፕሪፓራቶሪ የሚለውን ትቶ ዲፕሎማ ተምሮ በአጭር ጊዜ ስራ ይዞ ታናናሾቹን ማስተማር የሚለው ውሳኔ በመወሰን የጤና ትምህርት ተወዳድሮ በመግባት ትምህርቱን በአግባቡ ጨርሶ በማዕረግ ተመረቀ።

ከተመረቀ በኋላ ሁለት አመት ወደ ቤተሰብ ተመልሶ ያለ ስራ ተቀምጧል። ከሁለት አመት በኋላ ህልሙ የነበረውን የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመማር ፕሪፓራቶሪ ተመዘገበ ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ የ12 ክፍል ፈተናን ጥሩ ውጤት በማምጣት አምቦ ዩኒቨርሲቲ በኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ትምህርት ተመደበ።

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ጥሩ ውጤት በማምጣት እዛው መምህር በመሆን ተቀጠረ፣ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በማግኘት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን መከታተል ጀመረ።

በዚህ ውስጥ እያለ ትዳር መሰረተ። ባለቤቱ ወለጋ ጊዳሚ የሚባል ቦታ ገጠር ውስጥ ነበር የምትሰራው እሱን አቁማ እሱ ጋር እንድትመጣ ካደረገ በኋላ ስራ ጀመረች። ከብዙ የህይወት ውጣ ውረድ በኋላ ልጅ ወለዱ ልጃቸውም 3 አመት ሞላት።

የሚስቱ እህት ቅዳሜ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ስለምትመረቅ ልጁ፣ ሚስቱ እና የባለቤቱ እናት ለማስመረቅ ሐረማያ ሄዱ።

ከምርቃት በኋላ ትንሿ ልጅ አባቴ ናፍቆኛል እንሂድ በማለት በማልቀሷ ከምርቃት በኋላ መቆየት ቢፈልጉም ሰኞ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ቃሊቲ ፐብሊክ ባስ ባደረሰባቸው አደጋ ህይወታቸው ካለፈ 9 ሰዎች የዚህ ወጣት ልጅ፣ ሚስትና የሚስቱ እናት አሉበት።
Guys ይሄ ቻይና በራሱ ቋንቋ እየዘፈነ ነው
ኮሜንቱ ደሞ ሁሉም በሀበሻ ተሞልቷል

what's going on? ...😳🤷‍♂😂
" ኤልያስ መልካ ታሞ ሲተኛ አንድ ሰው አላየውም። "፡-ድምፃዊት መሰሉ ፋንታሁን

በስንት ታዋቂ ድምፃዊያን እንዳልተከበበ ሲወድቅ ዞር ብሎ የሚያየው አልነበረም ማለት ልብ የሚሰብር ነው።

አንዳንዴ የማትጠብቁት ወዳጃችሁም ቀን አይቶ ይሸሻል። በተለይ ከጥቅም ጋር የተያያዘ ጓደኝነት ከሆነ ወዳጅነታችሁ ጥቅም ላይ ያተኮረ ብቻ ይሆናል።

ያ ሲቆም መለያየት ይመጣል። ይህ ደግሞ ከጥቅም ጋር የተሳሰረ ጓደኝነት ይባላል።

በ1993 ዓ.ም "ፍቅር" ጋዜጣ ላይ ይመስለኛል። ከ400 በላይ የዘፈን ግጥም የደረሰው ተመስገን ተካ ከሞተ ከመንፈቅ በኋላ ባለቤቱ ቃለ መጠይቅ በተደረገችበት ወቅት አንድ የተናገረችው ነገር እስከዛሬ ከአእምሮዬ አልጠፋም።

"ተመስገን 2 ህፃን ልጆቹን ጥሎብኝ ነው የሞተው፣የምንተዳደረው በእሱ ገቢ ነበር። እሱ በሕይወት እያለ ቤታችን በታዋቂ ዘፋኞች እንደተሞላ ነበር።

ሲሞት ግን ተመላልሶ የጠየቀን ከድምፃዊ አረጋኸኝ ወራሽ በቀር ማንም አልነበረም።" ብላለች። ይኸው ነው።

"በደራበትማ፣ሰው መች ጠፋ
ይቆጠራል ወዳጅ፣ቀን ሲከፋ"

የሚለውን የቴዲ አፍሮን ሙዚቃ ያቀናበረው ኤሊያስ መልካ ነው። ለዚህም ጥሩ መገለጫ ይሆናል።
2025/06/26 06:35:55
Back to Top
HTML Embed Code: