Telegram Web
በኮቪድ ከስራ ተቀንሶ ጣሊያን ውስጥ በምታሳዝን አፖርትመንት ኩርምት ያለ ሚስኪን፣ ስልኩን ሲነካካ ድንገት ባገኛት ቲክቶክ የምትባል አፕ፣ ያውም ቃል ሳይተነፍስ እንዲህ አለምን ሲሞላት ኤቴስትን "እግዚሀርማ አለ" አያስብለውም ወይ?

ቲክቶክ ባለፈው ዓመት ብቻ 20 ሚሊየን ዶላር በአንድ ዓመት የከፈለው። ለእያንዳንዷ ፖስት ለሚያደርጋት ፖስት 750,000 ዶላር። አልባለገ አልተሳደበ ቃል አልወጣው! እስኪ አንድ ሰው ዘሎ አሜን ይበል! አይዘህ ዘለህ ትቀራለህ!

ሞክር! ስራ! ጣር! ከምንም በላይ ቅን ሁን! ቅን!ቅን! ቅን!

አንተኮ ይሄው ስንት ቀኔ ሰብስክራይብ አድርገኝ ስልህ እንዳላየ ታልፋለህ

በል እዚህ ፅሁፍ ስር ባለው ሊንክ ሰብስክራይብ አድርግ።ተጫነው...👇😁😋
https://youtube.com/@biranayetube?si=puGOMuJp6HbzRKaJ
Majestic!

Gonder, Amhara, Ethiopia...❤️
ጭራሽ መኪና ላላት ሴት
ነበር ስታለቅሱ የነበረዉ ...🙆‍♂😝😂
ለጌታም ጌታ አለው ...😝🙆‍♂😂
ተወ በሉት ይሄን ሰውዬ… ደሞ ከአዲሱ ሚስቱ እንዳያፋታው ...😭

ስማ አዕምሮ… ይሄ ፓስተር ቸሬ… ድርሽ እንዳይል እዚህ ትዳር ውስጥ…🤧
ሰይፍሻ የባለትዳሮችን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ተወው !

ይድረስ ፦ ለሰይፉ ፋንታሁን

ሰይፍሻ አንተ ቅን እና ደግ ሰው ነህ።

ሰይፉ ሾው የተሰኘ ቁጥር 1 የመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢ ነህ። በፕሮግራምህ ለዓመታት ስታዝናናን ፣ ቁምነገር ስታስጨብጠን እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖቻችንን ስትረዳ ፣ እንዲረዱ መንገዱን እያመቻቸህ ትልቅ ስራ ሰርተኻል።

ሰይፍሻ ወንድማችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕሮግራምህ ላይ የምታቀርባቸው በተለይ የባልና ሚስት የትዳር ፍቺ እና ንትርክ በአንተ ፕሮግራም ላይ ባይቀርቡ ባይ ነኝ።

ባለትዳሮቹ ወይ ታርቀው አይታረቁ ሁሉም በየፊናቸው የየራሳቸውን ብሶት እየዘረገፉ ሕዝቡን ግራ ማጋባታቸውን ተያይዘውታል።

ሰይፍሻ ወንድማችን ለዓመታት የገነባኸውን መልካም ስም እና ዝና በሚጨቃጨቁ እና ትዳራቸውን በፍቺ በቋጩ ባለትዳሮች እሰጥ አገባ ምክንያት ሰው አፍ ውስጥ ገብተህ መልካም ስምህን እንዳትንደው በጥንቃቄ ተመልከተው። ከፕሮዲውሰሮችህ ጋር በደንብ አጢነህ ምከርበት።

ከዚህ በኋላ የታመመ ትዳር ያላቸውን ሰዎች አንተ ፕሮግራም ላይ ባታቀርባቸው ስል ወንድማዊ ምክሬን እለግስሃለሁ።

ኢትዮጵያ ውስጥ በአንተ ልክ የመዝናኛ ፕሮግራምን አሳምሮና ቀጥ አድርጎ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለዓመታት ያለመዋዠቅ ፣ የሰራ ሰው አይቼ አላውቅም።

ወንድማችን ሰይፍሻ ፦ የአንተ ተወዳጅ ሾው ላይ ትዳራቸውን በፍቺ ያጠናቀቁ ባለትዳሮች ባይቀርቡ ፣ ጉዳያቸውን በሽምግልና ወይም በፍርድ ቤት ቢጨርሱ ባይ ነኝ።

አክባሪህና አድናቂህ ወንድምህ
ዘሪሁን ተዝናኑ ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!
አዲስ አበባ : የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ተከስቷል

ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮርፕስ (IMC) በአዲስ አበባና በስድስት ክልሎች የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ (ኤምፖክስ) መከሰቱን አስታወቀ።

ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮርፕስ ባለፈው አርብ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት፤ እስከ ሰኔ 3 ቀን በ አዲስ አበባ ከተማ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ሲዳማ፣ ሀረሪና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች 18 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው መረጋገጡን ገልጾ፤ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን አስታውቋል።

በሽታው መጀመሪያ የተገኘው በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ የ27 ቀን ሕፃን ልጅ ላይ መሆኑን የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም በጋራ ባወጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
Maedot le Ethiopia...👇👇👇
https://youtu.be/606v6246Yxg
የተረዳሁት! 7 ነገሮች!
ገለቴ ቁጥር አታውቅም ። የቀድሞ ባሏ ቁጥር ያውቃል!

ገለቴ መርጃ ማስረጃ አታውቅም። የቀድሞ ባሏ መረጃ ማስረጃ ያውቃል!

ገለቴ የእውቀት ችግር አለባት። የቀድሞ ባሏ ላለበት ነገር በቂ እውቀት አለው።

ገለቴ በመሰለኝ ታወራለች ታምናለች። የቀድሞ ባሏ መሰለኝ ብሎ ነገር የለም። ነው ብቻ ነው!

ገለቴ የደበቀችው እውነት አለ። የቀድሞ ባሏ እውነቱንም ሀሰቱን መግለፅ ይችላል።

ገለቴ የሰው ግፊት አለባት እራሷን አታምንም ። የቀድሞ ባሏ በማንም ግፊት አያምንም እራሱን ያምናል።

ገለቴ የህግ ሂደት አይገባትም። የቀድሞ ባለቤቷ ህግን ጥግ ድረስ እና ሂደቱን ያውቃል!

አይዞሽ ገለቴ! ብዙ ማለት ቢቻልም ለአሁን ይብቃ!
👉ሕጻናት ወደገዳም ሳይሆን ወደ ትምህርት ቤት ሂዱ

👉 ስለ ጋብቻም ስለ ምንኩስናም ቢሆን ስለማንኛውም ነገር ማወቅ መረዳት የምንችለው ትምህርት ቤት ነው

ክፉውን እና በጎውን ከለየን በኋላ በጸሎት እግዚአብሔርን ጠይቀን እኛ በመረጥነው ሳይሆን እግዚአብሔር በመረጠልን መኖር እንችላለን የሊቃውንት ጉባዔም አጽንቶ የተቃወመው ይህን ነው

አሥራ ስምንት ዓመት ካልሞላው ልጅ እራስ ላይ ቆብ መስቀል እና ለሚጠባ ልጅ ዲቁና መስጠት መቆም አለበት

በሶስት ዓመቱ ዲቁና ተቀብሎ በጾም ቀን ጧት ወተት ጠጥቶ ከሰዓት የቀደሰ ልጅ ገጥምኛል ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ እራሱ ነገረን ከባድ ነው ማን በዚህ ልጅ ይፈርዳል

👉 አባት አይከሰስ ሰማይ አይታረስ የሚል አባባል አይገባኝም ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው

እንዲህ አይነት ነገር ሥርዓተአበውንም ክብረ ክህነትንም የሚያበላሽ ነው

ከዚህ በኋላማ ምን ይባላል እግዚአብሔር መጨረሻችሁን ያሳምረው ነው

ወደፊት ሊታሰብባቸው ከሚገቡት አንዱ ይህ ነው
አዲስ አበባ ፡ የበሬ የጥሬ ስጋ በኪሎ እስከ 3,500 ብር ይሸጣል

ፊደል ፖስት ቅኝት ባደረገባቸው በቦሌ ፣ሳር ቤት ፣አዲሱ ገበያ ፣ ሰሚት የሚገኙ ስጋ ቤቶች የበሬ ጥሬ ስጋን ከ 2,800 ብር እስከ አስከ 3,500 ብር ድረስ ሲሸጥ መመልከት ችሏል።

ቪአይፒ ተብለው በጣም የተመረጠ ስጋ ለብቻቸው በተዘጋጀላቸው ክፍል ውስጥ አንድ ኪሎ ጥሬ ስጋ እስከ አምስት ሺ ብር የሚሸጥላቸው ሰዎችም አሉ።
ከአልኮል ነጣ ኬኛ አለ! ...😝🙆‍♂😂
ሚሳኤላችሁን ስትወራወሩ ጨረቃዋን መትታቹ ጦስ እንዳታመጡብን አደራ ...🤲🙆‍♂😝
ከሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተብሎ ፣

ይልማ ገብረአብ የለም። አበበ መለሰ የለም። አበጋዝ ሺዎታ የለም። ቴዲ አፍሮ የለም። ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ አለማየሁ ሂርጶ ፣ ኤፍሬም ታምሩና ቴዎድሮስ ታደሰ የሉም።

ሮፍናን የለም። ቀመር የሱፍና አቡሽ ዘለቀ የሉም። ጃምቦ ጆቴ የለም። ነዋይ ደበበና አረጋኸኝ ወራሽ የሉም። ልዑል ሃይሉና ልጅ ሚካኤል የሉም። ኩኩ ሰብስቤና አስቴር አወቀ የሉም። አስቴር ከበደና ፍቅርዐዲስም የሉም። ሃይሉ ፈረጃ የለም። ሚካኤል በላይነህ ፣ ማሪቱ ለገሰ አብዱ ኪያር የሉም።

በህይወት የሌሉት [ እነ አለማየሁ እሸቴ ፣ ጥላሁን ገሰሰ እና ኤልያስ መልካ ...) እና ሌሎች በስም የረሳናቸው የመድረክና ከመድረክ ጀርባ ያሉ አርቲስቶች የሉም።

ከዚያ ማን ቢጋበዝ ጥሩ ነው ... አስጌ ዴንዳሾ ፤ ያሬድ ነጉና መሠሎቹ ...

አንበሳዬ አስበሽዋል ከእነ አስጌ team ጋር መክረህ የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ወደፊት ሲራመድ ...😁🙆‍♂😝
ትዕግስተኛ

እዮብ ...

የጣናነሽ ሹፌሮች ...
#ይህንን ወጣት መርቁልኝ 🙏

ምንያህል (የማዕዶት አዘጋጅ) እየሰራው ያለው ነገር ቅድስት ቤተክርስቲያንን የሚያኮራ ነው እኛም ኮርተንብሃል በቃ አንተ ተፅኖ ፈጣሪ ነህ

ወጣቱ እንዲ ተሰብስቦ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲማር እና እንዲያመሰግን ም/ያት በመሆንህ እጅግ ደስ ይበልህ።

እርሱን በማገዝ ላይ ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆች ተባረኩ አሁንም እንደ ምንያህል ያሉ ወጣት የሚዲያ አካላት ቤተክርስቲያን ያስፈልጋታል

እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ያስፋን ወንድሜ በብዙ በረከት ተባረክ ...🙏❤️🏆
ስለ Ebs tv ሁሌም ለመፃፍ እያሰብኩ ዛሬ ነገ ስል ነበረ ዛሬ ጥቂት መስመርም ቢሆን ልፃፍለት

Ebs ቲቪ መታወቅ ያለበት የመጀመሪያው የአየር ላይ የግል የቴሌቪዥን ጣቢያ ብቻ ተብሎ ሳይሆን እንደውም ካገኘው ሳንቲም ላይ ለማህበረሰቡ በማካፈል ነው

ለምሳሌ በተለያየ መልኩ ለማህበረሰቡ ከሚያካፍላቸው በረከቶች መካከል በጥያቄ እና መልስ በቃጠሎ ፍልሚያ ለበዓል ቀናት ከእንቁላል እስከ ፍሪጅ መሸለም በየመንገዱ ዝፈኑ እያሉ እያዘፈኑ መሸለም የደሃ ቤት ማደስ ህይወታቸው በሆነ አጋጣሚ የተበላሸባቸውን እናቶች አባቶች ወጣቶች ከዛ አስከፊ ህይወት ለመውጣት የሚያስችል እርዳታ በመስጠት እንዲቋቋሙ በማድረግ ኢቢኤስ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል

በዚህ የሰዎችን የተበላሸ ህይወት ለማሻሻል አዲስ ምእራፍ በሚለው ፕሮግራም ከተቋቋመሙት ውስጥ አርቲስት ጋጋ እና የአሁኗ ቀበጥ ዋንቲያ ይጠቀሳሉ

አለ አይደለም ወይ በስም መጥቀስ ማልፈልጋቸው ..... የሚሉት የ 20 አመት ጣቢያ የስፖንሰር መዓት ይጎርፋል አንድም ቀን አንድም ቀን ካገኘው ሳንቲም ላይ ለተቸገሩ ዱንቡሎ ሳንቲም ሲሰጥ ወይም አስተባብሮ ሲያሰጥ አረ በምንም ነገር ሲሸልምም እንኳ ሰምቼም አይቼም አላቅ ።

እናም ኢቢኤስ በርታ በጥቂቱም ቢሆነ ለተቸገሩ የመድረስ አዝናንተህ የመሸለም ካለህ ካገኘኸው የማካፋል ደግነትህ ይቀጥል እንላለን ።
የክረምት ስራዎች ለሕፃናት

ት /ቤት በሚዘጋባቸው ጊዜአት ልጆች አንድ ሞያ እንዲማሩ እና እንዲሰሩበት ማድረግ ለአእምሮአቸው እድገት አስተዋፅኦ ያደርጋል:: በራስ መተማመን እንዲኖራቸው ያደርጋል

የሰሩትን ነገር ደግሞ ሸጠው ትንሽ ገንዘብ እንዲያገኙ ቢሆን የስራን ጥቅም ዋጋ እንዲሰጡ እና ሥራ እንዲወዱ ያደርጋል:: በቤት ዉስጥ ሊሰሩ የሚችሉ, ስልጠናዎች ቢሰጣቸው

👉በክር የሚሰሩ ኮፍያዎች, ያንገት ፎጣዎች, የጠረጴዛ ላይ ትኩስ ነገር ማስቀመጫዎች...
👉ስዕል
👉 የሙዚቃ መሳሪያ, ክራር, ማሲንቆ, guitar, ከበሮ...
👉የምግብ ዝግጀት እና ቤት አያያዝ ስልጠና
👉 ቶሎ የሚደርሱ የጕዋሮ አትክልቶች (ቲማቲም, ቃሪያ, ጎመን, ሰላጣ... አምርተው እንዲሸጡት ማድረግ
👉 ተሽከርካሪ የሕፃናት መጫወቻዎችን እንዲሰሩ ማስተማር

ከቤት ውጪ የሚሰሩ

👉 የ mass sport ከሰፈር ልጆች ጋር
👉የ group ዳንስ ስልጠናዎችን
👉የዋና ስልጠናዎች
👉የስፖርት ፍቅር ላላቸው የእግር ኳስ, volley ball, ጅምናስቲክስ, ሩጫ, ሌሎችም የስፖርት ስልጠናዎች
👉 የሕፃናት ቲያትር, ስነፅሁፍ
👉 የአካባቢ ፅዳት, አካባቢ ጥበቃ... ዛፍ ተከላ ወዘተ
👉 አንድ የውጭ ወይም የሀገር ውስጥ ቋንቋ እንዲማሩ
👉ፈረስ ግልቢያ

በሁሉም ክረምቶች ወላጆች ቀደም ብለው ቢያቅዱ ልጆችን የብዙ ክህሎቶች ባለቤት ማድረግ ይችላሉ::
በነገራቹ ላይ እስራኤላውያን ከእስልምና በላይ አጥብቀው የሚጠሉት ሀይማኖት ክርስትና ነው

የኛ ሀገር ክርስቲያኖች እስራኤላውያንን የሚወዱት ደሞ መፀሀፍ ቅዱስ ጠላታችሁን ውደዱ ስለሚል መሰለኝ ...🤧🙆‍♂️🤣
2025/06/25 05:51:49
Back to Top
HTML Embed Code: