ይድረስ ለAlex Abreham
እባክኽ 🙏
~ ሥጋ ቤት ስኼድ፤
~ ሥጋ ቤቱ ደጃፍ ላይ ቆሜ አንድ ዐሥር ኪሎ የቁርጥና የክትፎ ሥጋ ሳስመዝን፤
~ በቁሜም ጮማ ጣል የተደረገበት ከረሜላ ስበላ፤
~ ለሥጋ ቆራጩ ከጥሩ ቲፕ ጋር ገንዘብ ስከፍል፤
~ የተገዛውን ሥጋ በወዛደር አሸክሜ ወደ ቤቴ ይዤ ስኼድ፤
~ ከሴትዮዬ እና ከኹለት ልጆቼ ጋር ስበላ፤
~ ''እስኪ ከጥሬው ጥቂት ስጪኝ?'' ስላት፣ እርሷ ከአዋዜ ጋር ስታቀርብልኝ፤
~ ልጆቼ፣ "አባታችን ጥሬ ሥጋ ስጠን?" ሲሉኝ፤
~ "ልጅ ጥሬ እንጂ፣ ጥሬ ሥጋ አይበላም! እንዲያውም እንቊላል ይጠበስላችኹና ብሉ!" ብዬ ስቆጣቸው፤
~ ለሚስቴ ከአዋዜው ጠቀስ አድርጌ ሳጎርሳት፤
~ "ሆድኽን ይቆረዝዝኻል፤ ይኽችን ቅመስ!" ብላ አረቄ ስትሰጠኝ፤
~ ለራሷም ስታቀዳ፤ ጠጥተን በደስታ ስንሣሣቅ ወዘተ
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (በAI) ፊልም ሥራልኝ!?
ስሞትልኽ አሌክስ አንድ ኪሎ ሥጋ እስከ 3,500 ብር ለመግዛት የወር ደመወዜ ስለማይበቃ ሥጋ በ'AI' አስበላኝ!? ...ዓለሜን አሳየኝ!?
ሁምናሳ ገርቢቻ ረቢ ነኝ የምንጊዜም አድናቂኽና ወንድምኽ!
በሃይሉ ገ/እግዚአብሄር
AI ምስል ፦ አሌክስ አብርሃም

በ56 ሚሊየን ብር የተሰራው ድልድይ ተመረቀ!
በወላይታ ዞን 56 ሚሊየን ብር የወጣበት "ድልድይ" ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

እስራኤል የክርስትያን ሀገር አይደለችም ኢራንም አረብ ሀገር አይደለችም !
👉ኢራን አረብ ሀገር አይደለችም። ፐርሺያን ናት። በፐርሺያንና በአረብያን መሀል ሰፊ ልዩነት አለ
👉እስራኤል የክርስትያን ሀገር አይደለችም። ይልቁንም የጂውሾች ሀገር ናት።
👉በእስራኤል ክርስትናም እስልምናም ማይኖሪቲ ናቸው። ግን የሙስሊም ቁጥር ከክርስትያን ይበልጣል። ጅውሽ ባይኖር እስራኤል የሙስሊም ሀገር ትሆን ነበር።
👉ኢራን በአንፃሩ ከእስራኤል በላይ ብዙ ቁጥር ያላቸው ክርስቲያን ዜጎች አሏት።
👉እስራኤል ውስጥ ካሉ ክርስትያኖች ይልቅ አረቦች በቂጥር ይበዛሉ።
👉ክርስቲያንነትን መስበክ ከእስራኤል ይልቅ ኢራን ውስጥ መስበክ እጅግ ቀላል ነው።
👉ኢራኖች ፐርዥያን ወይም ፋርሲን ይናገራሉ እንጂ ጆሯቸው ቢቆረጥ አረቢክ ኣይችሉም። ትንሽ ናቸው ሚችሉት።
👉ኢራን የሙስሊም ሀገር ብትሆንም የሽኣ ሙስሊም ሀገር ናት። እነ ሳውዲ እና ብዙ የእስልምና ሀገራት ሚከተሉት የሱኒ እስልምና ተቃራኒ ናት። በሀገራቱም እንደጠላት ትፈረጃለች። እንደ እስልምና ስጋትም ትታያለች
👉እስራኤል ካሉ የክርስትያን ቤ/ክ በላይ ፍልስጤም ውስጥ ብዙ ቤ/ክ ኣለ። እየሱስም የተወለደው ፍልስጤም ውስጥ ነው።
እና ምን መሰለህ እዚ social media ላይ ሆነህ ክርስትያን ስለሆን እስራኤልን ሙስሊም ስለሆንክ ኢራንን አትደግፍ። መደገፍ ካለብህ ተበዳይን ብቻ ደግፍ። ሲጀመር ጦርነት ሚባል ነገር አትደግፍ። የሰው እልቂት እንጂ ምንም ሚያመጣው ነገር ስለሌለ።

ጆርዲን እና ቲጂ ያደረጉትን የፌሚኒዝም ክርክር አየሁት፡፡ በጣም ደስ ያለኝ እንዲህ አይነት ሴቶች እየመጡ መሆናቸው ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ሀሳባዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የምንከታተለውና የምንማረው ከወንዶች ነበር፡፡ የሁለቱን ክርክር የተከታተልኩት ደግፌም ሆነ ተቃውሜ ሀሳብ ለመስጠት ሳይሆን ለመማር ነው፡፡
በሴቶች ላይ ስታዘበው የነበረው ነገር፤ ጠንካራ ጉዳዮች ላይ አይሳተፉም፡፡ አንባቢ ከተባሉም ብዙዎች የሚያነቡት ልቦለድ ነው፤ የሚያዩት ሮማንቲክ ፊልም ነው፡፡ እንደ ምርምር እና ፖለቲካ ያሉ ጠንካራ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡
ለምሳሌ፤ የግጥም ምሽት እና የፊልም ምርቃት ላይ ብዙ ሴቶች ይገኛሉ፤ ጠንካራ የሚባሉ ጉዳዮች ላይ ግን በጣም ጥቂት ናቸው፤ ጭራሹንም ላይኖሩም ይችላሉ፡፡
የሴቶች እኩልነት የሚመጣው ሴቶች በጠንካራ ጉዳዮች ላይ ሲሳተፉ ነው፡፡ አርዓያ ሆነው ሲታዩ ነው፡፡ አለበለዚያ ‹‹ፌሚኒስት ነኝ›› እያሉ ማውራት ብቻውን ለውጥ አያመጣም፡፡
ፌሚኒስቶች የሚያነሱት ችግር የሚቀረፈው በሴታዊ እንቅስቃሴ አይደለም! ማህበረሰባዊና አገራዊ የአስተሳሰብ መሠልጠን ሲመጣ ነው፡፡ ፌሚኒስቶች የሚያነሱት ችግር የሚቀረፈው አገሪቱ ሰብዓዊ መብት የሚከበርባት አገር ስትሆን ነው፤ ህግና ሥርዓት የሚያከብር መንግሥት እና ሕዝብ ሲፈጠር ነው፡፡
ስለዚህ የሴቶች ትግል መሆን ያለበት እንደ ሴትነት ብቻ ሳይሆን እንደ አጠቃላይ እንደ አገር ነው፤ ለዚህ ደግሞ በጠንካራ ጉዳዮች ላይ ሊሳተፉ ይገባል!

"መምህሩ" ተሐድሶ ያስፈልገናል ብለዋል! (ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ)
" ... ወገኖቼ በጣም ልብ በሉ! ይህ መልዕክት ዛሬም ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ብዙ ትምህርት ይሰጣል ። ኢየሱስን ከማክበር ይልቅ ቅዱሳን መላዕክትን በላቀ ሁኔታ ማክበር የተለየ በረከት ያሰጠናል ብለን ለምናምን ሰዎች አመለካከታችንን እንድናስተካክል ማስተማሪያ ነው፡፡ቅዱሳን መላዕክትን ማክበር ተገቢና በጣምም አስፈላጊ ሥርዐት ነው። በአፋችን ክርስቶስ አምላክ ነው እያልን በተግባር ግን ከክርስቶስ በላይ ለመላዕክት የምንፈጽማቸው ሃይማኖታዊ ተግባራት እንደ አይሁድ ክርስቲያኖች እኛንም ያስወቅሱናል። ብዙዎቻችሁ ታዝባችሁ ይሆናል ዛሬ ኢየሱስ ነው ሲባል ቤተክርስቲያን የሚሄደው ሰው በጣት የሚቆጠር ነው፤ ስለ ኢየሱስ ክብር ሲዘምርና የክርስቶስን ክብር ከፍ አድርጎ ሲገልጽ የሚውለው በጣም ጥቂት ነው።
ዛሬ ገብርኤል ነው፣ ወይም ሚካኤል ነው ሲባል ግን በየቤተክርስቲያኑ የሚተመውን ሕዝብ ስንመለከትና ከክርስቶስ በላይ ለመላዕክቱ ሲዘምር፣ እልል ሲል፣ ሲመሰክር የሚውለውን ሕዝብ ግን ስንመለከት ለክርስቶስ በልባችን የሰጠነው ቦታ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ ማሳያ ነው። እንደ አይሁድ በደሙ ካገኘነው ጽድቅ ይልቅ በሥጋዊ ሕይወታችን ያገኘናቸው ስጦታዎች እጅግ እንደላቁብን ማሳያ ነውና ሁላችን መዳንን እንወርስ ዘንድ ሕይወቱን በመስቀል የሰጠንን ጌታ ከማንም በላይ አልቀን በልባችን ዙፋን ላይ ልናነግሥ ይገባል።
ክብርና ምሥጋና አምልኮና ጌትነት ለታረደው በግ ይሁን።"
("መምህር" ታሪኩ አበራ)

ለህክምና ባለሙያዎች ጥያቄ ድጋፉን የገለጸው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ታገደ
በቅርቡ የጤና ባለሙያዎች ያደረጉትን ስራ የማቆም አድማ ተከትሎ አመራሩ ታስረውበት የነበረው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር መታገዱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
እግዱ የተላለፈው ከኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን በኩል መሆኑን የገለጹት አቶ ዮናታን የእግድ ደብዳቤው ላይ “ጠቅላላ ጉባኤ አላካሄዳችሁም፣ የፋይናንስ ሪፖርት አላቀረባችሁም” የሚሉ ክሶች መነሳታቸውን ተናግረዋል።
አቶ ዮናታን አያይዘውም፤ "በመመሪያ እና የሀገሪቱ ህግ በሚፈቅደው ነው የተንቀሳቀስነው ከዛ ውጪ ያደረግነው ነገር የለም" ሲሉ ጠቅሰው፤ እግዱ በዋነኝነት ከጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ ጋር የተገናኘ ነው ብለው እንደሚያምኑ" አስታውቀዋል።
ማህበሩ የተመሰረተበት ዓላማ "ለጤና ባለሙያዎች ድምጽ ለመሆን ነው" ሲሉ ገልጸው ጤና ባለሙያዎች "ተገቢውን ቦታ እንዲያገኙ እና በሰሩት ልክ እንዲከፈላቸው ነው ድምጽ ስናሰማ የቆየነው" ብለዋል።