መንገድ ላይ
(በእውቀቱ ስዩም)
በቀደም ፥ ዠርመን ፥ኑረንበርግ ከተማ ውስጥ አንድ ሰውየ አገኘሁ፤
ሰውየው የቆዩ ናቸው፤ የበርሊን ግንብ ያፈረሰውን ዶዘር የነዱት እሳቸው ናቸው ይባላል፤
“አዲስ አበባ እንዴት ናት ?” አሉኝ፤
“አዲስ አበባ እየታደሰች ነው፤ ከተማይቱ ሸብረቅ ደመቅ ብላለች “ አልኳቸው፤
ትንሽ ተካከዙና እንዲህ አሉ፥
“ በቀድሞ የኢትዮጵያ ባህል፥ አንድን ነገር ጨርሶ ማስወገድ ሀጢአት ነው፤ ለምሳሌ የልጅ ጸጉር ሲላጭ ትንሽ ጠጉር ማስቀረት ግድ ነው፤ “ቁንጮ “ ይባላል፤ ምግብ ስትበላ ፥ ጨርሰህ አትበላም፤ ማእዱ ላይ የእንጀራ ቁራሽ ማስቀረት ይኖርብሀል፤ “ሞሰብ ጠባቂ” ይባላል፤ ወይም “የቆሌ ደርሻ “ ይባላል፤ አዝመራ ስትሰበስብ፥ ሙጥጥ አድርጎ መሰብሰብ ነውር ነው፤ ድሆች ለቅመው እንዲበሉት የምትተወው ርዝራዥ እህል መተው አለብህ ፤ “ቃርሚያ" እንለዋለን፤ በጦርነት ወቅት ሀይል እንኩዋ ቢኖርህ ጠላትህን ሙሉ በሙሉ መፍጀት የለብህም፤ ለወሬ ነጋሪ ማስቀረት አለብህ “
“ እህ”
“ እንዲሁም፥ ከተማ ሲታደስ ከነባሩ ውስጥ ለምልክት ለአንቲካ ያክል ማስቀረት ይገባል ፤ ከተማ ሲታደስ ብቻ ሳይሆን ሲደበደብ እንኩዋ ተመርጦ ምህረት የሚደረግለት አለ፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጀርመን ጠላቶች የሂትለር ተወዳጅ አገር የነበረችውን ይቺን ከተማ ሲያወድሙ ዋና ዋናዎችን ህንጻዎችን እና ሀውልቶችን መርጠው አትርፈዋል፤ ምን እያልሁ እንደሆነ ገብቶሀል?”
“አልገባኝም” ብየ ደረቅሁ፤
“አዲስ አበባ አዲስ ከተማ መሆን የለባትም፤ ለመኖር የምትመች ከተማ ሆና ነው መታደስ ያለባት “
"እና እኔ የከተማዋ ከንቲባ አይደለሁ ፤ ይሄን ለምን ይነግሩኛል "
ደማቸው ሲፈላ ይታወቀኛል፤ ዞር ብለው ሊሄዱ ሲሉ፤
“መጽሀፌን ግዙኝ “ አልኳቸው፤
“አይኔን ስስለሚያመኝ ማንበብ አልችልም” ሲሉ መሰሉልኝ፤
“ ግዴለዎትም ! ይግዙትና ልጅዎ ያነበዋል
“ልጄ ሞቷል”
“ነፍስ ይማር ! አፈሩን ገላባ ያድርግለት ! ያም ሆኖ ግዙኝ”
“በል ቻው !”
“በህግ አምላክ ግዙኝ “
“ አጨቅጭቀኝ ! ገዢው ፓርቲ ይግዛህ”

#STREW
ይህ ፊልም በጣም አስደናቂ ፊልም ነው።
በዋናነት 5 ከባድ የህይወት ቻሌንጆችን ያሳያል፦
1ኛ) Single mom ሆኖ ልጅ ማሳደግ ምን ያክል ከባድ እንደሆነ
2ኛ) ማጣት (ድህነት) ምን ያክል ክፉ እንደሆነ
3ኛ) በሰዎች ተቀባይነት ማጣት(rejection) እንዴት እንደሚጎዳ
4) ምንም ከባድ ሁኔታ ቢያጋጥመንም ስሜታችንን አለመግዛት የሚያስከፍለው ዋጋ ከባድ መሆኑን
5ኛ) Black American መሆን በራሱ የሚያስከፍለው ዋጋ ከባድ መሆኑን
✍️አንዳንድ ቀን አለ ሁሉ ነገር ጭልምልም የሚልበት፥ የሚጠምበት፥ በሮች ሁሉ ዝግትግት የሚሉበት።
ታዲያ በዚህ ጊዜ ብልህ ሰው በራሱ መንገድ ሄዶ ይበልጥ ነገሮችን አያወሳስብም። ልቡን ከፍቶ ብቸኛ ረዳት ወደሚሆነው ወደ ፈጣሪው ይጮሃል።
አምላክ እግዚአብሔር ቸር ነው ጬኸታችንን ይሰማል። አሜን ይስማን...🙏

12 ተማሪዎች ተጎዱ::
በአዲስ አበባ ከተማ የዉሀ ማጠራቀሚ ታንከር በትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍል ላይ ወድቆ 12 ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 ከሰዓት በኋላ ሸጎሌ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ ከሚገኝ በመኖሪያ ቤት ጣሪያ ላይ ተሰቅሎ የነበረዉ የዉሀ ማጠራቀሚ ታንከር በትምህርት ቤት በመዉደቁ በተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
አደጋዉ ያጋጠመዉ ከትምህርት ቤቱ አጠገብ የሚገኝና በግለሰብ መኖሪያ ቤት ጣሪያ ላይ የነበረና 3 ሺህ ሊትር ዉሀ የያዘ የዉሀ ታንከር ፍቅር የመጀመሪያ ደረጃ በሚባል ት/ቤት ጣሪያ ዘልቆ ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባቱ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስሬት ሬድዮ ተናግረዋል ።
ታንከሩ ጣሪያዉን ሰንጥቆ ሲገባ ተማሪዎቹ በክፍል ዉስጥ በመማር ላይ የነበሩ ሲሆን በዚህም 12 ተማሪዎች ቀላልና መካከለኛ ጉዳት ደርሷባቸዋል።
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር በአደረጉት ርብርብ በተማሪዎቹ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸዉን ተማሪዎች በኮሚሽኑ አምቡላንሶች ዉስጥ ህክምና እየተደረገላቸዉ ወደ አቤት ሆስፒታል ተወስደዋል።
ትምህርት ቤቱ ፍቅር የመጀመሪያ ደረጃ የተባለ የግል ትምህርት ቤት ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸዉ የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸዉ።የዉሀ መያዥ ታንከሮች በሚሰቀሉበት ከከፍታ ቦታ ላይ ወድቀዉ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ የሚሰቀለዉ የዉሀ ታንከር በብረትና በአርማታ የታሰረ እንዲሁም አስፈላጊዉን የደህንነት መስፈርት ያሟል መሆን አለባቸው ሲሉ አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

Like 10 days before i tried to transfer money to my Mpesa wallet from CBE and guess what? ከሲቢኢ ቆርጦ mpesa ላይ አልገባም ነበር and i had to wait 72 hrs to get my money back...
and in this week.. ATM ላይ 1k ላወጣ ሞክሬ ብሩን ቆርጦ ሳይሰጠኝ ቀረ and i had to notify the bank...
አሁን ደሞ ከ10k በላይ በካሽ መገበያየት አይቻልም እያለን ነው መንግስታችን. They really expects farmers to use mobile banking ጤፍ ከበት በግ ምናምን ለመሸጠት...
imagine a poor farmer using a digital wallet or USSD, and trust instant transfers. በግንድ ባንክና ቴሌ ብር ሲስተም ለዛውም...
forcing people to digital systems without proper infrastructure. አቀልዷ ...🙄

ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ህንፃ.. የሆነ ድርጅት ወይም Company አይደለም። አፓርትመንትም አይደለም። የአንድ ግለሰብ መኖርያ ቤት ነው። እዚህ ህንፃ ላይ የሚኖረው 1 ሰው ብቻ ነው። ይህ ቤት የአንድ ህንዳዊ ቢሊየነር መኖርያ ቤት ነው። የቤቱ ባለቤት Mukesh Ambani ይባላል።
.
Mukesh Ambani የአለማችን 7ኛ ቢሊየነር ነው። አጠቃላይ ሀብቱም ወደ 116 ቢሊየን ዶላር አካባቢ ይጠጋል። ይህ የ Ambani መኖርያ ቤት G + 27 ፎቅ ያለው ሲሆን 173 ሜትር ርዝማኔ አለው። Ambani እና ሚስቱ Nita እዚህ ቤት ውስጥ ለብቻቸው ነው የሚኖሩት።
.
10 ሺ ካሬ ሜትር ላይ የተንጣለለው ይህ መኖርያ ቤት 50 መኝታ ክፍሎች፣ 67 ሽንት ቤቶች፣ 2 ሲኒማ እና 10 ሊፍቶች ያሉት ሲሆን ሊፍቶቹም እጅግ ፈጣን ናቸው። የአለማችን ውዱ መኖርያ ቤት ተብሎም በ Guinness world record ላይ ተመዝግቧል ...😎

ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
ምንም ያላደረጉ ዜጎች ከመኪናቸው እንዲወርዱ ተደርገው የሽንት ቤት ሽታ እና ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ባለ ሽታ ባለበት ቦታ ፖሊሶች ምክንያቱን እንኳን በአግባቡ አስረድተው ባልገለፁት ቦታ ታግተው ይገኛሉ

ካንሰር አለበት 3 ወር ነው የቀረው ባለችው ቀሪ ጊዜ አብረሸው ሁኚ እና ሀብቱ ያንቺ ይሆናል ብለው አጋቧት
ብታየው ብታየው አ ይ ሞ ት ም 3 ወር አልፎ 10 ኛ ወር ገባ 1 አመት ሆነው አሁንም ብታየው አልሞት አለ ባሌ ከካንሰር ዳነልኝ ብላ መደሰት ፈጣሪዋን ማመስገን ሲገባት የእሱ ከካንሰር መዳን ለእሷ ቢዝነስ አዋጪ አይደለም
ሰርጋቸው Viral ስለነበር ስትፈታው ሰው ምን ይለኛል ብላ እንኳን ቆም ብላ አላሰበችም የፈጠነ ነው የፈታችው ከምር ግን ግፈኛ ነች እንደዚህ አይደረግም ነውር ነው
አንዳንድ ሰው ለገንዘብ የማይከፍለው መስእዋትነት የለም ...😭

አትሙት ያላት ነብስ
በትላንትናው ዕለት በህንድ የአውሮፕላን አደጋ ብቸኛው የተረፈው ሰው ኩማር ራሜሽ ሲሆን፣ ያጋጠመውን እንዲህ ሲል ገልጿል፦
"ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ነበር። በሕይወት ያለሁም አልመሰለኝም። ብድግ ስል ብዙ አስክሬኖች እዚያና እዚያ ተበታትነው አይቼ በጣም ደነገጥኩኝ። ወዲያውኑ መሮጥ ጀመርኩ።
'ወንድሜ የት ነህ? ወንድሜ የት ነው?' እያልኩኝ በከፍተኛ ድምፅ እጮህ ነበር። ወንድሜ ከእኔ ትንሽ ራቅ ብሎ ከነበረው ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር።
ምን እንደሆነ ባላውቅም፣ በዛን ወቅት አንድ ኃይል ሰውነቴን እንደወረረኝ ይሰማኛል። በሕይወት እንድተርፍ የረዳኝ ነገር እንዳለም ይሰማኛል።ሲል ተናግሯል::
ቀና ካልደረሰህ እንዲህ ነው::

New video on YouTube...👇👇👇
https://youtu.be/3qkglf6MIE4?si=TQeF6emk0lEKDS_t