tgoop.com/aybalem_ende/9246
Create:
Last Update:
Last Update:
* #ሰው_ለምን_ተፈጠረ...?
እስቲ መጀመሪያ አንድ ሰው ወንበር ለምን ተፈጠረ ብሎ ቢጠይቃችሁ መልሳችሁ ምን ይሆናል? እርግጠኛ ነኝ ሁላችሁም ለመቀመጫነት ብላችሁ እንደምትመልሱ፡፡ አዎ ወንበርን የሰው ልጅ ሲሰራው ወይም ሲፈጥረው ለመቀመጫነት እንዲያገለግል ወይም (Serve) እንዲያረግ ነው፡፡
#የሰው_ልጅንም_ፈጣሪ_ሲፈጥረው ለእራሱ ብቻ እንዲኖር አይደለም፡፡ ተፈጥሮን🌾 ፣ እንሰሳትን🦌 ከምንም በላይ ደሞ የገዛ አምሳያው የሆኑትን ሌሎች ሰዎች👫 እንዲያገለግል ወይም (Serve) እንዲያረግ ነው፡፡
#እናም ሁሌ በዕለት ተዕለት ውሏችን ከእኛ አልፈን ለሌሎች እናስብ፤ ከመብላት አልፈን እናብላ፤ ከመጠጣት አልፈን እናጠጣ፤ ከመልበስ አልፈን እናልብስ፤ በአጠቃላይ ለሌሎች ደስታና ምቾት እንኑር፡፡ የዛኔ ህይወት እራሱ ጣዕም ይኖራታል፡፡
: - : - : - : - :
🆔 @aybalem_ende
BY አይባልም™
Share with your friend now:
tgoop.com/aybalem_ende/9246