tgoop.com/aybalem_ende/9182
Create:
Last Update:
Last Update:
አባት ወደ ቢሮው ሊሄድ ቦርሳውን እያዘገጃጀ እያለ ልጁ መጣና...
" አባየ መስሪያ ቤትህ ልትሄድ ነው ?"
"አዎ"
" አባየ ቢሮህ በሰዓት ስንት ነው የሚከፍልህ ?"
" ይህ የአንተ ጉዳይ አይደለም... አይመለከትህም" " አባየ ንገረኝ ፈልጌው ነው ? " አይን አይኑን እያየ
" ውይ ምን ያደርግልሃል ... እሺ 100 ብር ነው " ብሎት ሊሄድ ሲል
" አባየ 50 ብር አበድረኝ "
" አንተ ልጅ ላቤን ጠብ አድርጌ የማመጣው ላንተ ኮልኮሌ መግዣ መሰለህ ? ዞር በል ወደዛ አሁን ልሂድበት " ሲለው ልጁ እያለቀሰ ወደ መኝታ ቤቱ ገብቶ ጋደም አለ ፡፡ አባት የልጁ ማልቀስ ስላሳዘነው ወደ ልጁ መኝታ ክፍል ሄደ
" ልጀ ተኛህ እንዴ ? " " አልተኛሁም " አለው እምባውን ከአይኑ ላይ አየጠረገ "50 ብርህን እንካ " ልጁ እየሳቀ ተቀበለው
" ደስ አለህ አይደል ? ሰዓት ስለደረሰ ልሂድ "
" ቆይ አባየ እንዳትሄድ" ከአልጋው ስር የሰበሰበውን ሳንቲም እና ብሮች አወጣና ለአባቱ አሳየዉ
" አባየ ይኸ አጎቶቼ እኛ ቤት ሲመጡ የሚሰጡኝን የሰበሰብኩት ብር ነው አንተ ከሰጠኸኝ ብር ጋር ሲደመር መቶ ብር ይሆናል ይኸን ብር እንካ #ለአንድ_ሰዓት ከኔ ጋር አብረኸኝ እንድትሆን እፈልጋለሁ...
ለልጆቻችን #ብር ሳይሆን #ግዜ እንስጣቸው፡፡
🆔 @aybalem_ende
BY አይባልም™
Share with your friend now:
tgoop.com/aybalem_ende/9182