Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/amennnnnnnnnnnnnnnnnnnn/--): Failed to open stream: No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 50
አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር@amennnnnnnnnnnnnnnnnnnn P.7986
AMENNNNNNNNNNNNNNNNNNNN Telegram 7986
ጻድቁ በአየር ላይ ሲጓዙ ድንጋዩን እንደ ሠረገላ ዋርካውን እንደ ጥላ ይጠቀሙበት ነበረ፡፡ ያ እንደ ሠረገላ ሆኖ ያገለግላቸው የነበረው ትልቅ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ ታሪኩም በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ እንድርያስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ናህርው

በዚህችም ቀን ዳግመኛ ከግብፅ አገር ከፍዩም መንደር አባ ናህርው በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ #እግዚአብሔርን እጅግ የሚፈራው ነው በእስክንድርያ ሀገር የሚሠቃዩ የሰማዕታትን ዜና በሰማ ጊዜ ክብር ይግባውና ስለ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለ ስሙ ሊሞት ወደደ በራእይም ወደ አንጾኪያ ሀገር ሒደህ በዚያ ትሞት ዘንድ አለህ አለው።

ወደዚያ መድረስ እንዴት ይቻለኛል በማለት የሚያስብ ሆነ ሊሳፈርም መርከብን ፈለገ በዚያን ጊዜ #እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለት በክንፎቹም ተሸክሞ ወደ አንጾኪያ ሀገር አደረሰው።

በዲዮቅልጥያኖስም ፊት ቀርቦ በ #እግዚአብሔር ታመነ ንጉሡም ስሙንና አገሩን ጠየቀው እርሱም ከግብጽ አገር እንደሆነ አስረዳው ንጉሡም ቃሉን ሰምቶ ለጣዖታቱ ቢሠዋለት ብዙ ገንዘብና የግምጃ ልብሶችን ሊሰጠው ማለለት እርሱ ግን ቃሉን አልሰማም ንጉሱም እኔ ታላቅ ሥቃይን አሠቃይሃለሁ የሚል ቃልን ደግሞ ተናገረው ከሥቃዩም የተነሳ አልፈራም ትእዛዙንም አልሰማም።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ናህርውን በብዙ አይነት ስቃይ እንዲአሰቃዩት ንጉሱ አዘዘ አንድ ጊዜ ለአንበሶች ጣሉት አልነኩትም አንድ ጊዜ ከእሳት ጨመሩት አልተቃጠለም ሌላ ጊዜም በወጭት ቀቀሉት ከማሠቃየትም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ ንጉሡ አዘዘ።

ይህ አባ ናህርውም በግብጽ አገር በሰማዕትነት ስለሞቱ ስለ አንጾኪያ አገር ሰማዕታት ፈንታ በአንጾኪያ አገር በሰማዕትነት አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ሰማዕት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሚናስ_ዘተመይ

በዚህችም ቀን ከገምኑዲ አውራጃ የሀገረ ተመይ ኤጲስቆጶስ የአባ ሚናስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ደጎች #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ዜናቸውም በቅዱሳን አባቶች ዘንድ እስከ ተሰማ ድረስ በጾማቸው በጸሎታቸው በገድል በመጸመዳቸው የመነኰሳትን ሥራ የሚሠሩ ናቸው።

እነርሱም ያለ ፈቃዱ ልጃቸውን ሚስትን አጋቡት ሙሽራዪቱም ወዳለችበት የጫጒላ ቤት ገባ ድንግልናቸውንም ሳያጠፉ ሥጋቸውን በንጽሕና ይጠብቁ ዘንድ ከእርሷ ጋር ተስማሙ ሁለቱም በበጎ ተጋድሎ እየተጋደሉ በአንድነት ኖሩ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚናስ የምንኲስና ልብስ ሊለብስ ወዶ ሚስቱን እንዲህ አላት በዓለም እያለን የምንኲስና ሥራ ልንሠራ ለእኛ አግባብ አይደለም እነርሱ ከልብሳቸው ውስጥ ማቅ በመልበስ በ #እግዚአብሔር_መንፈስ የተደረሱ መጻሕፍትን በማንበብና ለጸሎት በመትጋት ሌሊቱን ሁሉ ይቆሙ ነበርና ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥታ ሸኘችው አሰናበተችውም።

እርሱም ወደ አባ እንጦንዮስ ገዳም ሔደ ከወላጆቹ ሊርቅ ወዶአልና እነርሱ ወደ ሚስቱ ይመልሱት ዘንድ በንጉሥ ትእዛዝ በቦታ ሁሉ እየፈለጉት ነበርና #እግዚአብሔር ሠውሮታልና ከቶ አላገኙትም በዚያም ገዳም በገድል ተጠምዶ ብዙ ጊዜ ኖረ በእስክንድርያም ሊቀ ጳጳሳት የሆነው አባ ሚካኤል ከእርሱ ጋር በምንኵስና ነበር።

ከዚህም በኋላ ሁለቱ ብሩሃን ከዋክብት አባ አብርሃምና አባ ገዓርጊ በነበሩበት ወራት ከነበረበት ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ። ይህ ቅዱስ አባ ሚናስም ተወዳጅ ልጅን ሆናቸው ከእርሳቸውም ዘንድ በበዓታቸው የሚኖርና የሚያገለግላቸው ሆነ የምንኲስናንም ሥራ ጨመረ ከእርሳቸውም ትምህርታቸውን ተጋድሏቸውን በመማር ከብዙዎች በተጋድሎውና በአምልኮቱ ከፍ ከፍ አለ አባ አብርሃምና አባ ገዓርጊ ሌሎችም አባቶች ከእርሱ ተጋድሎ የተነሣ ያደነቁ ነበር።

ሰይጣን ግን በእርሱ ቀንቶ በታላቅ አመታት እግሮቹን መታው ሁለት ወርም በምድር ላይ ወድቆ ኖረ ። ከዚህም በኋላ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ያለ ጥፋት በጤና አሥነሣው።

ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ መርጦ ጠራው የሊቀ ጳጳሳቱም መልእክተኞች ወደርሱ መጡ ከመነኰሳት የሚለይ በመሆኑ ታላቅ ኀዘንን አዘነ ቅዱሳን አባቶችም ይህ ሥራ ከ #እግዚአብሔር ነው አትዘን አሉት።

እርሱም ለ #እግዚአብሔር ትእዛዝ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከሊቀ ጳጳሱ መልክተኞች ጋር አብሮ ሔደ ሊቀ ጳጳሱም ተመይ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾመው ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት በሽተኞችን የሚፈውሳቸው ሆነ በሽታ ያለባቸውም ሁሉ ወደርሱ ይመጣሉ እርሱም ክብር ይግባውና ወደ #እግዚአብሔር በመጸለይ ይፈውሳቸዋል።

ሁለተኛም የተሠወረውን የማወቅ ሀብተ ጸጋ #እግዚአብሔር ሰጠው በሰው ልቡና የታሰበውንም የሚያውቅ ሆነ ኤጲስቆጶሳቱም ሁሉ ከየሀገሮቻቸው በመምጣት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የሚታዘዙለትና ትምህርቱን የሚቀበሉ ሆኑ አሕዛብም ሁሉ ትምህርቱን ይሰሙ ዘንድ ይመጡ ነበር እርሱም ለአራት ሊቃነ ጳጳሳት አባት ሆነ። በሚሾሙ ጊዜ እጁን በላያቸው ጭኖአልና እሊህም በእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑ እለእስክንድሮስ፣ ቆዝሞስ፣ ቴዎድሮስ፣ ሚካኤል ናቸው።

ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ሊለየው በፈቀደ ጊዜ የሚለይበትን ቀን በ #መንፈስ_ቅዱስ አውቆ በሀገረ ስብከቱ ያሉትን ሕዝቡን ሁሉ ልኮ አስመጣቸው። በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ የከበረ የወንጌልንም ትእዛዝ እንዲጠብቁ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ ለእውነተኛው ጠባቂያቸው ለ #ጌታችንና_ለመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሰጣቸውና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ተለይቶ ወደ ወደደው #ክርስቶስ ሔደ ሕዝቡም አለቀሱለት ቸር ጠባቂያቸውም ከእርሳቸው በመለየቱ እጅግ አዘኑ እንደሚገባም ገንዘው እርሱ ራሱ በአዘዛቸው ቦታ አኖሩት።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_ዘኖቢስና_እናቱ_ዘኖብያ

በዚህችም ቀን ቅዱሳን ዘኖቢስና እናቱ ዘኖብያ በሰማዕትነት አረፉ እሊህም ቅዱሳን ተበይስ ከምትባል አገር ከታላላቆቿ ናቸው። እነርሱ ክርስቲያን እንደሆኑ በንጉሥ ዘንድ ወነጀሏቸው ንጉሥም ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘና ሲቀርቡ እንዲህ አላቸው የምትጠበቁት ከምንድን ነው አገራችሁስ ወዴት ነው እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት እኛ ጣዖታትን ከማምለክ እንጠበቃለን እምነታችንም በ #ክርስቶስ ነው ሀገራችንም ተበይስ ይባላል።

መኰንኑም ለአማልክት ሠዉ አላቸው ቅዱሳንም እኛ ለ #ኢየሱስ_ክርስቶስ እንሠዋለን እንጂ ለጣዖታት አንሠዋም አሉት መኰንኑም ተቆጣ ልብሳቸውንም ገፈው በራሳቸው ጠጒር ሰቅለው ይደበድቧቸው ዘንድ አዘዘ ወደ #እግዚአብሔርም ጸለዩ በዚያንም ጊዜ ማሠሪያቸው ተፈታ የብርሃንንም ልብሶች ለብሰው ሕዝቡ አዩአቸው መኰንኑም ወንበሩን ተሸክሞ በኋላቸው ሲከተል ነበር ። ሕዝቡም ይህን በአዩ ጊዜ እንዲህ እያሉ ጩኸው አመሰገኑ ልዩ ጽኑዕ ምስጉን አሸናፊ #እግዚአብሔር የጌትነትህ ክብር በሰማይና በምድር የመላ የ #ክርስቲያን_አምላክ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይልህ ታላቅ ነው።

tgoop.com/amennnnnnnnnnnnnnnnnnnn/7986
Create:
Last Update:

BY አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር

Share with your friend now:
tgoop.com/amennnnnnnnnnnnnnnnnnnn/7986

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

During the meeting with TSE Minister Edson Fachin, Perekopsky also mentioned the TSE channel on the platform as one of the firm's key success stories. Launched as part of the company's commitments to tackle the spread of fake news in Brazil, the verified channel has attracted more than 184,000 members in less than a month. Telegram is a leading cloud-based instant messages platform. It became popular in recent years for its privacy, speed, voice and video quality, and other unmatched features over its main competitor Whatsapp. Among the requests, the Brazilian electoral Court wanted to know if they could obtain data on the origins of malicious content posted on the platform. According to the TSE, this would enable the authorities to track false content and identify the user responsible for publishing it in the first place. Just at this time, Bitcoin and the broader crypto market have dropped to new 2022 lows. The Bitcoin price has tanked 10 percent dropping to $20,000. On the other hand, the altcoin space is witnessing even more brutal correction. Bitcoin has dropped nearly 60 percent year-to-date and more than 70 percent since its all-time high in November 2021. Activate up to 20 bots
from us

Telegram አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር
FROM American