AMENNNNNNNNNNNNNNNNNNNN Telegram 7770
ከመዋል የሚቀር አይኖርምና ንጉሣችንና አባታችን ቅዱስ ይምርሐነ #ክርስቶስም የእረፍት ዘመኑ ሲደርስ #እግዚአብሔር_አምላክ ቃል ኪዳኑን ለዘላለም እንደሚያፀናለት ነግሮት በዚህች በተባረከች #በጥቅምት_19 ቀን በክብር አሳረፈው።

መቃብሩንም አስቀድሞ እነደነገረው በዛው በተቀደሰ ዋሻ ውስጥ አደረገለት። እናም ዛሬ ድረስ ቦታው በክብር ተጠብቆ ይኖራል። ምእመናንም ቃል ኪዳኑን በማሰብ "ማረኝ ይምርሐ" እያሉ መቃብሩን ይዞራሉ። ያንን ከሰማይ የወረደለትን #መስቀልም በቤተመቅደሱ የሚያገለግሉት ካህናት አባቶች ቦታውን ለመሳለም የሚመጣውን ሕዝበ ክርስቲያን በበዓል ቀን ይባርኩበታል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት ይምርሐነ #ክርስቶስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_በርቶሎሜዎስና_ሚስቱ

ዳግመኛም በዚህች ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ።

እሊህ ቅዱሳንም የግብጽ ምዕራብ ከሆነ ፍዩም ከሚባል አገር ናቸው ክርስቲያኖችም እንደሆኑ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሏቸው መኰንኑም ልኮ አስቀረባቸውና ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በፊቱ ታመኑ።

መኰንኑም ጥልቅ ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸው በዚያም እንዲጨምሩአቸውና በሕይወታቸው እንዲደፍኑባቸው አዘዘ። መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባቸው በዚህም ምስክርነታቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#የጳውሎስ_ሳምሳጢን_ውግዘት

በዚችም ቀን ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ተደረገ። ይህ ጳውሎስም ከአንጾኪያ አገሮች በአንዲቱ አገር ኤጲስቆጶስነት በተሾመ ጊዜ ክፉ ዘርን ሰይጣን በልቡ ውስጥ ዘራበት #ሎቱ_ስብሐት አካላዊ ቃልን አካል እንደሌለ የ #ክርስቶስም ጥንት መገኛው #ሎቱ_ስብሐት ከ #ማርያም እንደሆነ እርሱም አለምን ያድንበት ዘንድ #ሎቱ_ስብሐት #እግዚአብሔር የፈጠረው እንደሆነ #ሎቱ_ስብሐት ከመለኮትም ጋር ያልተዋሐደ በላዩ ወርዶ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ አደረበት እንጂ ብሎ የሚያምን ሆነ በ #ወልድም ቢሆን በ #መንፈስ_ቅዱስም ቢሆን የሚያምን አልሆነም።

ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት በአንድነት ተሰበሰቡ የእስክንድርያው አባ ዲዮናስ የሮሜ አባ ዲዮናስዮስ እሊህ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ እርጅናቸው ከዚያ ደርሰው ከእርሳቸው ጋር ሊሰበሰቡ አልቻሉም ነገር ግን መልእክትን ጻፉ።

የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስም እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈ። የ #እግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ #ክርስቶስ በ #መለኮቱም ከእርሱ ጋር ትክክል የሆነ እርሱም ከሦስቱ አካላት አንዱ #ወልድ ስለእኛ ከ #እመቤታችን ከቅድስት ድንግል #ማርያም ያለ ዘር ስጋንና ነፍስን ነሥቶ ፍጹም ሰው የሆነ በመለኮቱ ከ #አብ ከ #መንፈስ_ቅዱስ ጋር ትክክል ሲሆን እንደእኛ ፊጹም ሰው ሁኗል ከተዋሕዶውም በኋላ ያለ መለያየትና ያለ መቀላቀል ሁለቱ ባሕርያት አንድ ሁነዋል ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍት ምስክሮችን ጠቅሶ እያስረዳ ጽፎ ይቺንም መልእክት ከሁለት ምሁራን ቀሳውስት ጋር ላካት።

በዚያንም ጊዜ አሥራ ሦስቱ ኤጲስቆጶሳትና እሊህ ሁለቱ ቀሳውስት ጉባኤ አድርገው ይህን ጳውሊ ሳምሳጢን አቅርበው የአባ ዲዮናስን መልእክት በፊቱ አነበቡ። ዳግመኛም #ክርስቶስ የ #እግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ የጌትነቱ ነጸብራቅ ነው የሚለውን የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስን ቃል በመጥቀስ እርሱ ከ #አብ ከ #መንፈስ_ቅዱስ ጋር በትክክልነት እንደሚኖር አስረዱት እርሱ ግን ቃላቸውን አልተቀበለም።

ከዚህም በኋላ በእርሱ ትምህርት የሚያምኑትን ሁሉ አው*ግዘው ከምእመናን ለይተው አሳደዱት። ለምእመናንም ሥርዓትን ሠሩ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አበው በጸሎታቸው ከስሕተት ይጠብቀን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘጸይለም

በዚችም ቀን የጸይለም አገር የከበረ አባት ዮሐንስ አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ከሀገሩ ታላላቆች ወገን ናቸው የአባቱም ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሣራ ነው እነርሱም ልጆች ስለ ሌሏቸው ብዙ ዘመን ወደ #እግዚአብሔር እየለመኑ ኖሩ።

በአንዲትም ዕለት ሁለት መነኰሳት ወደ እነርሱ እንግድነት መጡ እነርሱም በክብር ተቀብለው አሳደሩአቸው። እሊህ መነኰሳትም አብርሃምን ልጅ የለህምን አሉት እርሱም እንባውን እየአፈሰሰ አባቶቼ ልጅ የለኝም አሁንማ እኔ አረጀሁ የሚስቴም የልጅነቷ ወራት አለፈ ብሎ መለሰላቸው። እሊህ መነኰሳትም ስለ እርሳቸው ጸለዩላቸው ባርከዋቸውም ጎዳናቸውን ተጓዙ።

ከጥቂትም ቀን በኋላ ቅድስትሳራ ፀነሰች ደስ የሚያሰኝም ልጅን ወለደች ስሙንም ዮሐንስ ብለው ሰየሙት በእርሱም ደስ አላቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት እየአስተማሩ አሳደጉት።

ዐሥራ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ መምህሩ ቤት መነኰሳት መጡ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር እንዲወስዱት ለመናቸው እነርሱም አባትህን እንፈራለንና እኛ አንወስድህም አሉት። መነኰሳቱም ወደቦታቸው እየሔዱ ሳሉ ወደ መረጠው ጎዳና ይመራው ዘንድ ዮሐንስ ተነሥቶ ወደ #እግዚአብሔር ጸለየ ከመምህሩም ቤት ወጥቶ ሊደርስባቸው ወዶ መነኰሳቱን በኋላቸው ተከተላቸው ወደ ታላቅ ወንዝም ደረሰ ብቻውንም መሻገር ፈርቶ ቆመ ከዚያም ሳለ ዓረቦች ከግመሎቻቸው ጋር መጡ ያሻገሩትም ዘንድ ለመናቸው እነርሱም ከእርሳቸው ጋር አሻገሩት አንወስድህም ወደአሉት መነኰሳት ወደ ገዳማቸው በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ደረሰ።

ከእርሳቸውም አንዱ አባ ስምዖን የሚባለው ዮሐንስን ወስዶ ደቀ መዝሙሩ አድርጎ ከሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር አኖረው።

አባ ስምዖን የሚሞትበት ጊዜ እንደቀረበ በአወቀ ጊዜ ልጆቹን ጠርቶ ከሞትኩ በኋላ በእናንተ ላይ የሚሆነውን #እግዚአብሔር ያሳየኝን እነግራችሁ ዘንድ ልጆቼ ኑ አላቸውና ከእናንተ አንዱን ጅብ ነጥቆ ይወስደዋል። ሁለተኛው ወደ ዓለም ተመልሶ ይባክናል። የሦስተኛው ግን ዜናው በዓለሙ ሁሉ ይሰማል አላቸው።

ከዚህም በኋላ አረጋዊው ስምዖን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ተመልክቶ ልጄ ሆይ በ #ክርስቶስ ፍቅር ጽና ለብዙዎች አባት ልትሆን እርሱ መርጦሃልና አለው። አባ ስምዖንም ከአረፈ በኋላ በሦስተኛው ቀን አንዱ ረድዕ ወደ ዓለም ተመልሶ ሚስት አገባ ሁለተኛው ወዴት እንደ ደረሰ አልታወቀም። አባ ዮሐንስም ብቻውን ቀረ ፈጽሞ አዘነ በልቡ እንዲህ አለ የጓደኞቼን ወሬ እጠይቅ ዘንድ ከገዳም ወጥቼ ልውረድ ይህንንም ብሎ ከገዳሙ ወጥቶ ሲወርድ የጸይለም ጦረኞች ተቀበሉት ደም ግባታቸው ከሚአምር ከሁለት ሴቶች ጋር አሥረው ወሰዱት በጒዞም ላይ እያሉ ለእንስሶቻቸውና ለራሳቸው የሚጠጡት ውኃ አጡ። አባ ዮሐንስም ከዚህ በረሀ ውስጥ ፈጣሪዬ ውኃን ቢአወጣላችሁ ትለቁኛላችሁን አላቸው አዎን አሉት። በዚያንም ጊዜ አባ ዮሐንስ በስመ #አብ #ወወልድ ወ #መንፈስ_ቅዱስ ብሎ በምድር ላይ አማተበ ውኃም ፈልቆላቸው ጠጥተው ረኩ።

tgoop.com/amennnnnnnnnnnnnnnnnnnn/7770
Create:
Last Update:

BY አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር

Share with your friend now:
tgoop.com/amennnnnnnnnnnnnnnnnnnn/7770

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Administrators Telegram message that reads: "Bear Market Screaming Therapy Group. You are only allowed to send screaming voice notes. Everything else = BAN. Text pics, videos, stickers, gif = BAN. Anything other than screaming = BAN. You think you are smart = BAN. According to media reports, the privacy watchdog was considering “blacklisting” some online platforms that have repeatedly posted doxxing information, with sources saying most messages were shared on Telegram. To view your bio, click the Menu icon and select “View channel info.” Judge Hui described Ng as inciting others to “commit a massacre” with three posts teaching people to make “toxic chlorine gas bombs,” target police stations, police quarters and the city’s metro stations. This offence was “rather serious,” the court said.
from us

Telegram አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር
FROM American