Telegram Web
#እንኳን_ደስ_አላችህ_ታላቅ_ቅናሽ❗️
=====
👉ለውድ ደንበኞቻችን
ከወዲሁ እንኳን 1446ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን  በዓሉን  ምክንያት በማድረግ ከ 10 በላይ  በሚሆኑት የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች ላይ ለጥቂት ቀናት ብቻ  የሚቆይ ከመደበኛው የስልጠና ክፍያ በ20% ታላቅ ቅናሽ አድርገናል❗️
👉ቅናሹ የሚቆይው ለትንሽ ቀናት ስለሆነ በመረጡት ዘርፍና በመረጡት ፈረቃ ቀድመው በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ❗️
👉ስልጠናው የሚሰጠው በክፍል፣በወርክሾፕና በሳይት/በኢንዱስትሪ ልምምድ ሲሆን ሲጨርሱ 100% የስራ ዕድል አለው ❗️

👉ልዩነታችን ግልፅ ነው ይመዝገቡ❗️ይሰልጥኑ❗️ልዩነት ፈጣሪ ባለሙያ ይሁኑ❗️ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️
👉በአጭር ጊዜ ስልጠና የረዥም ጊዜ ህልምዎን ያሳኩ❗️
ልዩነታችን ብቁ ባለሙያ  ማድረጋችን ብቻ አይደለም የሥራ ባለቤት ማድረጋችንም ነው❗️


Telegram:
https://shorturl.at/zKTN2
Website:
www.amenelectrical.com
TikTok:
https://shorturl.at/VQN6I
Youtube:
https://shorturl.at/I8eyb
Facebook:
https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL

#አድራሻ
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)

#ለተጨማሪ_መረጃ
👇
0991156969
0939555510
#አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩት
#የደህንነት_ካሜራ_ስርዓት(CCTV Camera System) ማለት ምን ማለት ነው
==
👉CCTV(Closed Circuit Television) ስርዓት አንድና ከዛ በላይ የሆኑ የደህንነት ካሜራዎች (Security cameras) ኔትወርክን ሪከርድ ከሚያደርግ መሳሪያ እና ከማከማቻ መሳሪያ(Storage device) የሚገናኝበት ስርዓት ነው።
👉ከተለመደው ቴሌቪዥን የሚለየው ለክትትልና ለደህንነት ሲባል በይፋ ለህዝብ የማይሰራጭበት የቲቪ ስርዓት ነው።

*⃣ #ጠቀሜታዎቹ
የሚከተሉት ዋና ዋና ጠቀሜታዎች አሉት።
1. ደህንነትን  ለማረጋገጥና ወንጀልን ለመከላከል(Security & Crime Prevention)
👉በመኖሪያ ቤቶች፣ በንግድ ቤተቶች; ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ወዘተ ሊፈጠሩ የሚችሉ ዝርፊያን፣ ስርቆትና ሌሎች ወንጀሎችን ለመከላከል ይረዳል።
2. ለትራፊክ ቁጥጥር(Trafic Monitoring)
👉 መንገዶችና አውራ ጎዳናዎች ላይ የሚከሰቱ የትራፊክ እንቅስቃሴዎ ለመቆጣጠር።
3. የኢንዱስትሪ ቁጥጥር ለማድረግ(Industrial  Surveillance )
👉ፋብሪካዎችና የመጋዝኖችን ደህንነት ለመጠበቅ ይጠቅማል።
4. ሩቅ ከሆነ ቦታ ቁጥጥር ለማድረግ(Remote Monitorinግ)
👉ሞባይል ወይም ኮምፒዩተር በመጠቀም ሩቅ ከሆነ ቦታ ሆነው የሥራ፣ የንግድና የመኖሪያ ቦታዎን እንቅስቃሴ መቆጣጠር መቻል።
5. ለምርመራ የሚውል ማስረጃ ለመሰብሰብ (Evidence Collection for Investigations)
👉 ማስረጃ ለመሰብሰብ የወንጀል ተጠያቂዎችን ለመለየት ያገለግላል።
6. የአእምሮ ሰላም (Peace of Minde)ይሰጣል
👉የቤት ባለቤቶች ንብረታቸው 24 ሰዓት ቁጥጥር እንደሚደረግለት ስለሚያውቁ የበለጠ ደህንነት እንዲሰማቸው ያደርጋል።

ክፍል 1---
👉#ስልጠና_ለመሰልጠን_ከፈለጉ_ይደውሉ❗️
*⃣#የደህንነት_ካሜራ_አይነቶች(Types Of Security Cameras)
👉 ሦስት አይነት የደህንነት ካሜራዎች አሉ። እነርሱም፦

1⃣. #አናሎግ (Analog) CCTV ካሜራ
👉ቀላል እና አስቀድሞ የነበረ ቴክኖሎጂ ነው።
👉ምስሎችን በኮክሲያል ኬብል (coaxial cable) ያስተላልፋል።
👉የምስል ጥራቱ (resolution) ከዲጂታል ካሜራ ያነሰ ነው (ብዙው ጊዜ 720p ነው)።
👉ለትንንሽ እና መሰረታዊ የደህንነት ፍላጎቶች ተስማሚ ሲሆን ዋጋውን በአንፃራዊ ሲታይ ይቀንሳል።
2⃣. #ድጂታል (IP/Network) CCTV ካሜራ
👉የላቀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከፍተኛ ጥራት ያለው ምስል ይሰጣል (1080p, 4K, ወዘተ)።
👉በኢንተርኔት ወይም LAN ኔትወርክ ይሰራል።e
👉ተጨማሪ ባህሪያት አሉት (ማለትም፣ በርቀት ለመቆጣጠር፣ AI የእንቅስቃሴ ማሳወቂያ፣ ወዘተ)።
👉ለትላልቅ የደህንነት ስርዓቶች ተስማሚ ነው።
👉ዋጋቸው ከ አናሎግ ይወደዳል።
3⃣. #ሃይብሪድ (Hybrid) CCTV ካሜራ
👉አናሎግ እና ዲጂታል ስርዓቶችን በአንድነት የያዘ ነው።
👉ከአሁን ካለው አናሎግ ስርዓት ጋር ለመስራት ተስማሚ።
👉ወደ ሙሉ ዲጂታል ስርዓት ለመሸጋገር ይረዳል።
👉የተለያዩ የካሜራ ዓይነቶችን በአንድ ስርዓት ውስጥ ለማዋሃድ ያስችላል።

#ክፍል_2
👉#ክፍል_3 ይቀጥል የምትሉ #Comment መስጫው ላይ #Amen ብላችሁ ፃፉልን❗️


#አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩት
EBCS-10 Electrical Installation of Buildings.pdf
156.7 MB
የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ደንብና  መመሪያ ማወቅ ከፈለጉ እነዚህን መፅሐፎች ያንብቡ❗️
#Troubleshooting_and_Repairing_Major_Appliances_Eric_Kleinert_z.pdf
45.2 MB
የቤት እቃዎች ጥገናን(Home Appilaince Maintenance) መማር ወይም ጥንቅቅ አድርጋችሁ ማወቅ ከፈለጋችሁ ደግሞ ይህን መፅሐፍ አንብቡ❗️
#የCCTV_ካሜራ_ስርዓት_ክፍሎች
=====
👉የደህንነት ካሜራ ስርዓት (CCTV (Closed-Circuit Television) System   ዋና ዋና ክፍሎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦
1. ካሜራ
👉እንቅስቃሴዎችን በምስል ወይም በቪዲዮ ቀርፆ በማስቀረት መረጃ እንድናገኝ የሚረዳን ሲሆን የተለያዩ አይነት ካሜራዎች አሉ። እነርሱም፦ Dome, C-Mount, Day/Night, PTZ etc
2. የምስል/የቪዲዮ  መቅጃ  መሣሪያ (Recording Device)
👉የደህንነት ካሜራ ስርዓት ዋናው ክፍል ሲሆን በካሜራው የተቀረፀውን ምስል ወይም ቪዲዮ ተቀብሎ ለማከማቼት(Store) የሚያገለግል ክፍል ነው።
👉የተለያየ አይነት  የምስል/የቪዲዮ  መቅጃ  መሣሪያ ያለ ሲሆን ዋና ዋናዎችሁ የሚከተሉት ናቸው!
ሀ. DVR (Digital Video Recorder): 
👉 በካሜራ የተቀረፀውን ምስል/ቪዲዮ ከአናሎግ ፎርማት ወደ ድጂታል ፎርማት በመቀየርና በመጭመቅ  ሀርድ ድራቭ ላይ የሚያስቀምጥ መሳሪያ ነው።
👉አናሎግ ካሜራ የሚቀበል ሲሆን አነስተኛ የምስል/የሚዲዮ ጥራት አለው።
ለ. አውታረ መረብ ቪዲዮ መቅጃ/ NVR (Network Video Recorder):-
👉መረጃዎችን ኮድ የሚያደርገውና ፎርማት የሚሰጠው ካሜራ ላይ እያለ ሲሆን ይህን ምስል/ቪዲዮ ሀርድ ድራይቭ ላይ ለማከማቼት ይረዳናል።
👉 IP ካሜራዎችን የሚቀበል ሲሆን ጥራት ያለው ቪዲዮ/ምስል እንዲኖረን ያደርጋል።
ሐ. ሃይብሪድ ሬከርደር (Hybrid Recorder/HVR):-
 👉 ሁለቱንም የካሜራ አይነቶች ይቀበላል።
3. ማከማቻ (Storage)
👉የተቀዱ ምስሎች የሚከማቹበት (HDD፣ SSD ወይም  Cloud) ማለት ነው።
4. ማሳያ (Monitor)
👉የተቀረፀውን ምስል /ቪዲዮ ለማየት የምንጠቀምበት ነው።
5. ገመዶች_እና_ማገናኛዎች (Cables & Connectors)
👉መረጃዎችን ከላኪው ወደ ተቀባዩ መረጃዎችን ለማስተላለፍ የምንጠቀምበት የግንኙነት ቻናል ነው።
👉 Coaxial cable, Twisted Pair cable, fiber optic cable etc እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።

#ክፍል_3
👉#ክፍል_4_ይቀጥል የምትሉ #Amen ብላችሁ #Comment አድርጉ❗️

#የደህንነት_ካሜራና_የፋየር_አላርም_ሲስተም ስልጠና መሰልጠን ከፈለጉ ይደውሉ❗️

#አድራሻ
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)

#ለተጨማሪ_መረጃ
👇
0991156969
0939555510

#አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩት
#የኤሌክትሪክ_ሥራ_የሙያ_ብቃት_ማረጋገጫ_የምስክር_ወረቀት_አሰጣጥ_ሒደት
========
የኢትዮጵያ  ኢነርጂ ባለስልጣን  በአዋጅ  ቁጥር 810/2006  የኤሌክትሪክ  ስራ የብቃት ማረጋገጫ  የምስክር ወረቀት ለመስጠት በተሰጠው ስልጣን መሰረት የኤሌክትሪክ ሥራ የሙያ  ብቃት ማረጋገጫ እየሠጠ ይገኛል፡፡ በኤሌክትሪክ  ሥራ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሠጣጥ መመሪያ ቁጥር 1/2011 ዓ.ም. መሠረት
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሚሠጥባቸዉ የኤሌክትሪክ ሥራ ዓይነቶች፣
የኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን ፣
•የኤሌክትሪክ ዲዛይንና ቁጥጥር እና
•የኤሌክትሪክ  ፍተሻና ምርመራ ናቸዉ፡፡    ይህ ብሮሸር በባለሥልጣኑ የብቃት ማረጋገጥና ቴክኒካል ሬጉሌሽን ዳይሬክቶሬት  የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሒደትን በሚመለከት ለባለሙያዎች መረጃ ለመስጠት የተዘጋጀ ብሮሸር ነው፡፡ 
1.የኤሌክትሪክ ስራ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ  የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ቅደም ተከተል 
1. አመልካቾች የሚፈልጉትን  የሙያ ብቃት ደረጃ በተመለከተ የማመልከቻ ቅፅ እንዲሞሉና ባቀረቡት ሰነድ የተጠየቁትን መሥፈርት ማሟላታቸው ተረጋግጦ እንዱመዘገቡ ይደረጋል፡፡ 
2.  የፅሁፍና የተግባር ፈተና ይሰጣል፡፡ ውጤቱም ወዱያውኑ ይፋ ይሆናል።
3. የፅሁፍና የተግባር ምዘናውን ያለፉ ሰርተፊኬት ይረከባሉ። ያላለፉ ደግሞ ሰነዳቸው ይመለስላቸዋል፡፡
4. አመልካቾች በፈተናው ውጤት ላይ ጥርጣሬ ካላቸው ጥያቄያቸውን ላረመው አካል በማቅረብ ውጤቱ ተመርምሮ ፈጣን ምላሽ ይሰጣቸዋል፡፡ 
4. ለኤሌክትሪክ ሥራ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማመልከት መቅረብ ስለሚገባቸው  መረጃዎችና  ማስረጃዎች
I. ማን ኛውም  የኤሌክትሪክ  ሥራ  የብቃት ማረጋገጫ  ምስክር ወረቀት ለማግኘት  የሚቀርብ  አመልካች  መጠኑ  3X4 የሆነ  ከ6 ወር ወዲህ  የተነሳው 2 ጉርድ  ፎቶ ግራፍ  ማቅረብ  አለበት፡:
II. የኤሌክትሪክ  ሥራ  የብቃት  ማረጋገጫ  ምስክር ወረቀት ለማግኘት  ከሚቀርብ  ማመልከቻ  ጋር  እንደደረጃዉ  መቅረብ   የሚኖርበት  የትምህርት ማስረጃ
ሀ) በኤሌክትሪካል  ምህንድስና ፣ ኤሌክትሪካል/ኤሌክትሮኒክሰ  ቴክኖሎጂ ፣ በኤሌክትሮ ሜካኒካል  ምህንድስና  ወይም
ለ) የኤሌክትሪክ  ሙያ  ከማስተማር  ጋር  የሚያያዝ  ትምህርት  ማስረጃ (BEd) ወይም
ሐ) በየደረጃው ከሚገኙ  የሙያና  ቴክኒክ  ሥልጠና  ኮሌጆች  የኤሌክትሪክ  ትምህርት ደረጃ  ማስረጃ  ወይም  እዉቅና  ካለዉ  ተቋም የተገኘ  የ60 ሰዓት  ሥልጠና  ምስክር  ወረቀት  ወይም  የደረጃ 1 (Level 1)  ሲኦሲ/COC/  ምስክር  ወረቀት 
5. የኤሌክትሪክ  ሥራ  ብቃት  ማረጋገጫ  ምስክር  ወረቀት ለማግኘት  ከሚቀርብ  ማመልከቻ  ጋር  የሚቀርብ  የሥራ  ልምድ  ማስረጃ ከዚህ  በታች  በተመለከተው  መሠረት ቀጥተኛና  ቀጥተኛ  ያልሆነ  የሥራ  ልምድ  ተብሎ  ይያዛል፡: 
ሀ)  የሥራ  ልምድ  ማስረጃው  ከኤሌክትሪክ  ሥራ  ጋር  የተያያዘ  ሥራ፣ የኤሌክትሪክ  ኃይል  ሲስተም  ግን  ቦታና  ኦፕሬሽን ፣ ምርመራ/ፍተሻ፣  የምህንድስና  ስሌቶች  አጠቃቀም፣ በቁጥጥር ማረጋገጥ፣  ንድፍ ማውጣት/ማዘጋጀት፣     የኤሌክትሪክ  ሥራዎች ማማከር፣ የኤሌክትሪክ  ኃይሌ  ሲስተም  ሥራ  እቅድ  አደረጃጀት፣  የኤሌክትሪክ እቃዎችና  መሳሪያዎችን  ኢንስታሌሽን ፣ የህንጻ፣ ኢንዱስትሪያል  ኤሌክትሪክ  መስመር  መዘርጋት፣ በኤሌክትሪክ  ዕቃዎች  ጥራት  ፍተሻና  ምርመራ፣ የኤሌክትሪክ  መለኪያ መሳሪያዎች ንጽጽር  እና  ጥገና (calibration and repair)፣ የኤሌክትሮ ሚካኒካል  ሥራ  ወይም ኤሌክትሮ ሚካኒካል  ሥራ ጥገናና  እድሳት፣ የባዮሜድካል  ዕቃዎችና  መሣሪያዎች  ተከላና ጥገና ፣ ቲዎሪና ተግባርን  በማጣመር  ማስተማርን  የሚያረጋግጥ ከሆነ ቀጥተኛ  የሆነ  የሥራ ልምድ  ተደርጎ  ይያዛል፡:
ለ) የአመልካቹ  የሥራ  ልምድ ማስረጃ  ከላይ  በተመለከተው  አግባብ  ከኤሌክትሪክ  ሥራ  ጋር  በቀጥታ  ያልተያያዘ  ሲሆን  የሥራ ልምደ  ቀጥተኛ  ያልሆነ  ተብሎ  በግማሽ  ይያዛል፡: 
6. አመሌካች በግል ወይም  በራሱ  ስም  በተመዘገበ  ድርጅት  የሚሰራ  በሆነ  ጊዜ  የሥራ  ልምድ ማስረጃውን  “ከክንዋኔ ዝርዝር” እና  ኮንትራት  ውል  ሰነድ  ጋር  አያይዞ  ማቅረብ  ይኖርበታል፡: 
7. የደረጃ  1 የኤሌክትሪክ  ኢንስታሌሽን  አመልካች  ሥራ  ልምድ  ማስረጃው  ከላይ  በተመለከተው  መሰረት  ባልሆነ  ጊዜ  አመልካች  ለደረጃው  ማመልከት  የሚችለው  የደረጃ “2” የኤሌክትሪክ  ኢንስታሌሽን  ብቃት  ማረገጋገጫ  ምስክር  ወረቀት ወስዶ ቢያንስ  2 ዓመት ወይም  የደረጃ “3” ብቃት  ማረጋገጫ  ምስክር  ወረቀት  ወስዶ  ቢያንስ  4 ዓመት  የሥራ  ልምድና  የሥራ  ልምዱ ከላይ  ከተመለከቱት  ሥራዎች  ቢያንስ  ባንዱ  መስራቱን  የሚያስረዳ  ሆኖ  ሲገኝ  ብቻ  ነ ው፡:
8. የአገልግሎት ክፍያ
በኢነርጂ  ደንብ ቁጥር 447/2011 ዓ.ም  አንቀጽ 20 መሰረት የብቃት ማረጋገጫ  ምስክር  ወረቀትን  በተመለከተ ባለሥልጣኑ ለሚሰጣቸው  አገልግሎቶች  የሚፈጸሙ የአገልግሎት  ክፍያ  እንደሚከተለው  ዝርዝር  ክፍያ  መሰረት  ተፈጻሚ  ይሆናል ፡፡
ለደረጃ 1 አጠቃላይ  የአገሌግሎት  ክፍያ  ብር 606.64
ለደረጃ 2 አጠቃላይ  የአገሌግሎት  ክፍያ  ብር 485.31
ለደረጃ 3 አጠቃላይ  የአገሌግሎት  ክፍያ  ብር 363.98
ለደረጃ 4 አጠቃላይ  የአገሌግሎት  ክፍያ  ብር 242.66
ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የተወሰደ
#ማሳሰቢያ
1. የብቃት መረጋገጫ ለማውጣት ከመሄዳችሁ በፊት በ online ማመልከት አለባችሁ።  http://WWW.eservice.gov.et
2. ቢሯቸው የሚገኘው ቦሌ ወሎ ሰፈር ካድኮ ግሩፕ ሕንፃ
ነው
3. ከፈተና በፊት በቂ የተግባር ልምምድ ማድረግ ከፈለጉ ደግሞ #አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩትን ምርጫዎ ያድርጉ❗️
2025/06/16 15:57:41
Back to Top
HTML Embed Code: