tgoop.com/amenelectricaltechnology/2810
Last Update:
✅#የደህንነት_ካሜራ_ስርዓት(CCTV Camera System) ማለት ምን ማለት ነው❓
==
👉CCTV(Closed Circuit Television) ስርዓት አንድና ከዛ በላይ የሆኑ የደህንነት ካሜራዎች (Security cameras) ኔትወርክን ሪከርድ ከሚያደርግ መሳሪያ እና ከማከማቻ መሳሪያ(Storage device) የሚገናኝበት ስርዓት ነው።
👉ከተለመደው ቴሌቪዥን የሚለየው ለክትትልና ለደህንነት ሲባል በይፋ ለህዝብ የማይሰራጭበት የቲቪ ስርዓት ነው።
*⃣ #ጠቀሜታዎቹ
የሚከተሉት ዋና ዋና ጠቀሜታዎች አሉት።
1. ደህንነትን ለማረጋገጥና ወንጀልን ለመከላከል(Security & Crime Prevention)
👉በመኖሪያ ቤቶች፣ በንግድ ቤተቶች; ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ወዘተ ሊፈጠሩ የሚችሉ ዝርፊያን፣ ስርቆትና ሌሎች ወንጀሎችን ለመከላከል ይረዳል።
2. ለትራፊክ ቁጥጥር(Trafic Monitoring)
👉 መንገዶችና አውራ ጎዳናዎች ላይ የሚከሰቱ የትራፊክ እንቅስቃሴዎ ለመቆጣጠር።
3. የኢንዱስትሪ ቁጥጥር ለማድረግ(Industrial Surveillance )
👉የፋብሪካዎችና
የመጋዝኖችን ደህንነት ለመጠበቅ ይጠቅማል።
4. ሩቅ ከሆነ ቦታ ቁጥጥር ለማድረግ(Remote Monitorinግ)
👉ሞባይል ወይም ኮምፒዩተር በመጠቀም ሩቅ ከሆነ ቦታ ሆነው የሥራ፣ የንግድና የመኖሪያ ቦታዎን እንቅስቃሴ መቆጣጠር መቻል።
5. ለምርመራ የሚውል ማስረጃ ለመሰብሰብ (Evidence Collection for Investigations)
👉 ማስረጃ ለመሰብሰብ የወንጀል ተጠያቂዎችን ለመለየት ያገለግላል።
6. የአእምሮ ሰላም (Peace of Minde)ይሰጣል
👉የቤት ባለቤቶች ንብረታቸው 24 ሰዓት ቁጥጥር እንደሚደረግለት ስለሚያውቁ የበለጠ ደህንነት እንዲሰማቸው ያደርጋል።
ክፍል 1---
👉#ስልጠና_ለመሰልጠን_ከፈለጉ_ይደውሉ❗️
BY Amen Electrical Technology Official®

Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2810