tgoop.com/amenelectricaltechnology/3067
Last Update:
✅#ጀነሬተርህ_ያለምንም_ችግር_ከአሥር_ዓመት_በላይ_እንዲያገለግልህ_ትፈልጋለህ? መልስህ አዎ ከሆነ እስከመጨረሻው ተከተለኝ! ቤተሰብ መሆንና ለሌሎች #ሼር ማድረግም እንዳይረሳ፦
ጀነሬተር ከ10 ዓመት በላይ ያለምንም ችግር እንዲያገለግልህ ማድረግ ያለብህ ወሳኝ ነገርትሮች፦
1⃣. #ጀነሬተሩን_ንፁህና_ደረቅ_ቦታ_ማስቀመጥ
👉አንዳንድ ቦታ ጀነሬተር እርጥብ ቦታ ላይ ወይም ለዝናብና ለሙቀት ተጋላጭ የሆነ ቦታ ላይ ጀነሬተር ተቀምጥ ወይም ተተክሎ ይታያል ነገር ግን በከፍተኛ ደረጃ ለዝገት ፣ ናፍጣው ወይም ቤንዚኑ እንዲተን፣ ባትሪው ቶሎ እንዲበላሽና ሌሎችን ጉዳቶች ሊያስከተል ስለሚችል ንፁህና ደረቅ ቦታ ማስቀመጥ ይገባል።
2⃣. #ዘይትና_ፊልትሮ_በየጊዜው_መቀየር
👉ልክ እንደ ሚኪና ዘይት የጀነሬተርም ዘይት በጊዜ ሂደት ቅባትነቱን ያጣል።
👉ስለዚህ ጀነሬተራችን ከ50-100 ሰዓት ከሰራ በኋላ ዘይት በመቀየር ጀነሬተራችን ላይ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት መቀነስ የምንችል ሲሆን እንዲሁም ፊልትሮ በመቀየር ወደ ኢንጅኑ ቆሻሻ እንዳይገባ ማድረግ እንችላለን።
3⃣. #ጥራት_ያለውና_ንፁህ_ነዳጅ_መጠቀም
👉በጀነሬተር ታንክ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተቀምጦ የሚቆይ ነዳጅ በጥቂት ወራት ውስጥ ሊበላሽ ይችላል ስለዚህ ስለዚህ ንፁህና ጥራት ያለው ነዳጅ በመጠቀም ጀነሬተራችን ከብልሽት መታደግ እንችላለን❗️
4⃣. #ያለሥራ_የተቀመጠ_ጀነሬተር_ከሆነ_ቢያንስ_በወር_አንዴ_ማስነሳት
👉የጀነሬተር ተንቀሳቃሽ ክፍሎችና የነዳጅ ሲስተሙ ካልሰሩ የመድረቅና የመጣበቅ ባህሪ ስላላቸው ጀነሬተሩ ሥራ ላይ ከልሆነ በወር አንድ ጊዜ ለ15 ደቂቃ ያክል አስነስቶ ማሰራት ያስፈለጋል።
5⃣. #አየር_ማስገቢያና_ማስወጫውን_ማፅዳት፦
👉ቆሻሻ አየርና አቧራ የአየር ዝውውርን በመዝጋት ከፍተኛ ሙቀት ሊፈጥር ስለሚችል የአየር ማስገቢያውንና ጭስ ማውጫውን በየጊዜው መፈተሽና ማፅዳት አስፈለጊ ነው❗️
6⃣. #ጀነሬተሩን_ትክክለኛው_አቅሙ_ላይ_ማሰራት፦
👉ጀነሬተራችን ከአቅም በላይ ወይም ከአቅም በታች ማሰራት የኢንጅኑን ቆይታ ያሳጥረዋል።
👉ጀነሬተራችን ከአቅም በላይ እንዲሰራ ከተደረገ ከፍተኛ ሙቀት ፣ የቮልቴጅ መውረድና ኤሌክትሪካል ብልሽት ያስከትላል።
👉ጀነሬተራችን ከአቅም በታች እንዲሰራ ከተደረገ ደግሞ ኢንጅኑ ነዳጁን ሙሉ ለሙሉ ስለማያቃጥለው ጭስ ማውጫው አካባቢ እርጥበት በመፍጠር ጀነሬተራችን ነዳጅ እንዲያባክን፣ ከፍተኛ ጭስ እንዲኖረውና ቀዳዳዎች እንዲደፈኑ ያደርጋል።
👉ሥለዚህ ጀነሬተራችን ከሬትድ ካፓሲቲው ዝቅተኛው ከ 30% ያላነሰ እና ከፍተኛ ከ70% ያለበለጠ ቢሆን ጀነሬተራችን ያለምንም ችግር እንዲሰራ ይረዳናል።
👉 #አድቫንስድ_የጀነሬተር_ጥገና_እና_ዝርጋታ እንዲሁም #ሞተር_ኮንትሮል_ሲስተም_የተግባር_ስልጠና መሰልጠን ከፈለጉ ነገ ሐሙስ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ላይ የሚጀመር ሲሆን ቆይታው ለ 2 ወራት ነው❗️
#ተጨማሪ_ትምህርታዊ_ቪዲዮዎችን_ለመከታተል❗️
👇👇👇👇
Website: www.amenelectrical.com
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
✅#አድራሻ፦
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)
✅#ለተጨማሪ_መረጃ፡
👇
0991156969
0939555510
#አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩት
https://vm.tiktok.com/ZMAYnB9Rn/
BY Amen Institute of Technology Official®
Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/3067
