tgoop.com/amenelectricaltechnology/3028
Last Update:
#የፍሪጅ_የማቀዝቀዣ_ዑደት #Fridge_Refregiration_Cycle
==================
👉በማቀዝቀዣው ውስጥ ያለው ሲስተም #ኮምፕረሰር/ Compressor ፣ #ኮንደንሰርር_ኮይል /Condenser coil፣ #የእንፋሎት_ኮይል/Evaporator coil፣ #የማስፋፊያ/ካፕላሪ ቱቦ (Capillary tube/ expansion valve) እና #የሙቀት_መለዋወጫ (heat exchanger/Thermostat) እና #ተያያዥ_ቱቦዎችን ያካትታል።
👉ከኮምፕረሰር የማቀዝቀዣ ጋዝ (refrigerant gas) በማስወጫ ቱቦዎች(discharge tube) በኩል ይወጣ እና ወደ ኮንደንሰር ኮይል ውስጥ ይገባል። ይህ የሚከናወነው ደግሞ ኮፕረሰር ውስጥ ያለው ሞተር ኮምፕረሰሩን ሲያስነሰው ነው።
👉ጋዝ ኮንደንሰር ኮይል ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ የማቀዝቀዣው ጋዝ (refrigerant gas) የሙቀት መጠን (Temperature) እና ግፊት (pressure) በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል .ምክንያቱም ከኮንደንሰር ማስወጫ ቱቦዎች(discharge tube) አጥገብ የሚገኘው የመስፋፋት ቱቦ (Capillary tube) የማቀዝቀዣ ጋዙ እንደፈለገ እንዲያልፍ አያደርገውም።
👉ከኮንደንሰር ኮይል ወለል ላይ ሙቀት (heat) ወደ ከባቢ አየር በመሰራጨት የሞቆውን ሪፍሪግራንት ጋዝ ያቀዘቅዘዋል።
👉ማለትም ሪፍሪግራንት ጋዙ ከፍሪጁ ውስጥ ያገኘውን ሙቀት ወደ ከባቢ አየር ይለቀውና ወደ ፈሳሽ (liquid) ይቀየራል።
👉ይህ ፈሳሽ ደግሞ ኮንደንሰር ኮይሉን ለቆ ወደ ተስፋፊ ቱቦ ወይም capillary tube /expansion valve ይገባል።
👉ይህ ካፒላሪ ቱቦ እንደ ፍሪጁ ሞዴል ርዝመቱ እና የውስጥ ዲያሜትሩ በጥንቃቄ የተሰራ ሲሆን ወደ ኢቫፖሬተር ቱቦ የሚያልፈውን የፈሳሽ መጠን የሚወስን ይሆናል።
👉ፈሳሹ ማቀዝቀዣ (liquid refrigerant) ትንሽ መጠን ካለው ካፕላሪ ቱቦ(capillary tube) ወጥቶ ወደ ትልቁ ትነት ኮይል (Evaporator coil) ውስጥ ሲገባ በድንገት የቱቦው መጠን ስለሚጨመር ዝቅተኛ ግፊት ይኖረዋል።
👉እናም ፈሳሹ ሪፍሪግራንት ወደ ቅልቅል ሪፍሪግራንት (mixed refrigerant /gas & Liquid) ይቀየራል።
👉ይህ ፈሳሽ እና ጋዝ የቀላቀለ ውህድ በኢቫፖሬተር ኮይል ሲያልፍ ሙቅ ከሆኑት የምግብ አይነቶች ሙቀትን በመሳብ ምግቦችን ሲያቀዘቅዝ በሂደት ግን እራሱን ወደ ጋዝነት (ሪፍሪግራንት ጋዝ) ይለውጣል።
👉ይህ ሪፍሪግራንት ጋዝ ኢቫፖሬተር ኮይልን ለቆ ወደ ኮምፕረሰር ኮይል በመግባት ዑደቱን ይደግመዋል።
👉ይህ አጠቃላይ ሂደት ዑደት(cycle) ይባላል።
👉የቀዝቃዛ መቆጣጠሪያው (ቴርሞስታት) ፍሪጅ ውስጥ ያለውን ቅዝቃዜ ምን ያህል ቀዝቃዛ እንደሆነ ያሳያል ከዚያም የማቀዝቀዣውን ዑደት መቆጣጠር ይችላል።
👉በፍሪጅ ውስጥ ያለውን የሙቀት መጠን ለመጠበቅ #በማብራት ወይም #በማጥፋት ይቆጣጠራል።
👉#ለሌሎችም_ያጋሩ❗️
👉ልዩነታችን ግልፅ ነው ይመዝገቡ❗️ይሰልጥኑ❗️ልዩነት ፈጣሪ ባለሙያ ይሁኑ❗️ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️
ልዩነታችን ብቁ ባለሙያ ማድረጋችን ብቻ አይደለም የሥራ ባለቤት ማድረጋችንም ነው❗️
✅#አድራሻ፦
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)
✅#ለተጨማሪ_መረጃ፡
👇
0939555510
0991156969
#አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩት
BY Amen Institute of Technology Official®
Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/3028
