tgoop.com/amenelectricaltechnology/2748
Last Update:
✅#ብሬከር_እየመለሰ_ሲያስቸግረን_ማድረግ_ያለብን_ምንድን_ነው❓
=======
↪️ዛሬ የቤታችሁ የኤሌክትሪክ ብሬከር እየመለሰ በሚያስቸግራችሁ ጊዜና የባለሙያ ድጋፍ በቅርበት ማግኘት በማትችሉበት ወቅት ያለምንም መሳሪያ እንዴት ችግሩን መለየትና ጊዚያዊ መፍትሄ መስጠት እንደምትችሉ እናያለን❗️
↪️ከታች ቪዲዎው ላይ እንደምታዩት #የማሰልጠኛ_ተቋማችን መብራቶች ላይተው ጠፍተዋል❗️ሶኬት ግን እየሰራ ነው❗️
↪️ስለዚህ መብራቶች ብቻ ለይተው ቀጠፉ ችግሩ ያለው የመብራቱ ሰርኪዮት ላይ ነው ማለት ነው። በዚህም መሰረት ዲስትሪቢውሽን ቦርዳችን ስናይ አንደኘዋ የመብራት መቆጣጠሪያ ብሬከር መልሳ እናገኛታለን❗️
ለመመለስ ስንሞክር ሾርት ሰርኪዩት ስለተፈጠረ (ከፍተኛ የሆነ የከረንት ፍሰት ስላለ ፌዝና ኒውትራል ሲገናኝ የሚፈጠር) ብሬከሩ ወዲያውኑ ይመልሳል❗️ይህንን ችግር ያለምንም መሳሪያ ለመፍታት የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች እንከተላለን፦
1⃣. በዚህ ጊዜ በቀጥታ ማድረግ ያለብን ቤታችን ውስጥ ያሉትን ማብሪያ/ማጥፊያዎች በሙሉ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ መመለስ ነው።
2⃣. በሁለተኛ ደረጃ የመለሰውን ሰርኪዩት ብሬከር እንመልሳለን(ON)❗️
አሁን ብሬከሩ እንደቀድሞው እየመለሰ አያስቸግረንም❗️ምክንያቱም ተገናኝተው የነበሩት የፌዝና የኒውትራል ገመዶች በማብሪያ/ማጥፊያ አማካኝነት ስለሚለያዩ ነው❗️ይህ የሚሆነው ግን ኒውትራሉ ከፌዝ ጋር የተገናኘው ከማብሪያ/ማጥፊያ በኋላ ከሆነ ነው❗️
2⃣. አሁን ተራ ቁጥር አንድ ላይ የመለስናቸውን ማብሪያ/ማጥፊያዎች በሙሉ ቀድሞ ውደነበሩበት እንመልሳለን❗️በዚህ ጊዜ ችግሩ ያለበትን ክፍል ማብሪያ/ማጥፊያ ስንመልስ ብሬከራችን ይመልሳል ማለት ነው❗️ስለዚህ በቀላሉ ችግሩ የትኛው ክፍል እንደሆነ ለየን ማለት ነው❗️
4⃣. አሁን ባለሙያ ካልሆንን የዚህን ክፍል ማብሪያ/ማጥፊያ መልሰን OFF ላይ አድርገን ብሬከራችን ስንመልሰው ሌሎቹ ክፍሎች መብራት ያገኛሉ ማለት ነው❗️ባለሙያ እስከሚሰራው ይህ ክፍል ማብሪያ/ማጥፊያው ሳይነካ ጨለማ ሆኖ ይቆያል ማለት ነው።
5⃣. ይህ ክፍል በባለሙያ የሚሰራ ሲሆን ችግሩ ያለበት ክፍል ገብተን ፌዝና ኒውትራል የተገናኘብትን ቦታ ፈልገን እናላቅቀዋለን ማለት ነው❗️እንዲሁም ውደፊት እንደዚህ አይነት ክስተት እንዳይፈጠርብን በሚገባ በኤሌክትሪክ ፕላስተር( insulation Tape) ጫፋቸውን እናስራቸዋለን።
እንደ አስፈላጊነቱ መልቲሜትር ልንጠቀም እንችላለን❗️ለጥንቃቄ ሲባል መብራት ማጥፋታችንና አስፈላጊውን የኤሌክትሪክ አደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን መጠቀማችን እንዳይረሳ❗️
↪️አሁን ስራችን ጨርሰናል ማለት ነው❗️የስራችን ውጤት ማየት ነው❗️
🔄 #ከወደዱት_ለሌሎችም_ሼር_ማድረግዎን_እንዳይረሱ❗️
👉ልዩነታችን ግልፅ ነው ይመዝገቡ❗️ይሰልጥኑ❗️ልዩነት ፈጣሪ ባለሙያ ይሁኑ❗️ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️
👉በአጭር ጊዜ ስልጠና የረዥም ጊዜ ህልምዎን ያሳኩ❗️
ልዩነታችን ብቁ ባለሙያ ማድረጋችን ብቻ አይደለም የሥራ ባለቤት ማድረጋችንም ነው❗️
↪️#ቪዲዎውን_ለማየት
👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMkKNFet9/
✅#አድራሻ፦
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)
✅#ለተጨማሪ_መረጃ፡
👇
0991156969
0939555510
#አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩት
BY Amen Electrical Technology Official®

Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2748