tgoop.com/amenelectricaltechnology/2633
Last Update:
✅.#ስታር_ዴልታ_ሞተር_ማስጀመሪያ_ዘዴ/#Star_Delta_Motor_starting_Method
=========
👉ከዚህ ቀደም 4ቱን የተለያዩ የሞተር ማስጀመሪያ ዘዴዎችን አይተናል። ዛሬ ደግሞ ስለ ስታር- ዴልታ ሞተር ማስጀመሪያ ዘዴ እናያለን። ይህ የማስጀመሪያ ዘዴ የተለመደ እና በብዛት ስለምንጠቀምበት በጥልቀት ለማየት እንመክራለን።
👉ስለ ስታር-ዴልታ የሞተር ማስጀመሪያ ከማየታችን በፊት ግን ስታር ኮኔክሽን እና ዴልታ ኮኔክሽን ምንድን ናቸው? የሚሉትን እናያለን። መልካም ቆይታ🙏
🔸ስታር /Star & ዴልታ/Delta
👉ስታር እና ዴልታ ከስማቸው እንደምንረዳው ስማቸው ቅርፃቸው ያመለክታል።
👉ስታር / Star connection የምንለው 3 ፌዝ ያላቸውን ሰርኪዩቶች አንደኛውን ጫፍ አንድ ላይ በማሰር የጋራ ኒውትራል ነጥብ(Neutral point) በመፍጠር መብረቅን ለመከላከል ከመሬት ጋር ማሰር የሚያስችል ዘዴ ነው።
👉ይህ ዘዴ የ "Y" ቅርፅ ያለው ሲሆን "star" ወይም "wye" Connection ብለን ልንጠራው እንችላለን።
🔸ዴልታ/Delta Connection
👉ዴልታ ኮኔክሽን የምንለው ደግሞ የሦስት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ሲሆን 3 ፌዝ ያላቸውን ሰርኪዩቶች የንዱን መጀመሪያ ከ ሌላኛው መጨርሻ (end-to- start) በማገናኘት የምንፈጥረው ዘዴ ነው።
👉በመቀጠል ስለሁለቱ ባህሪ ወይም ተመሳሳይነት እና ልዩነት እናያለን።
#Star Vs #Delta_Connection
🔸 #ስታር/ #Star
1. አራት የኤሌክትሪክ ዋየሮች ሲኖሩት 3ቱ ፌዞች ሲሆኑ አንዱ ኒው ትራል ነው።
2. የመስመር ከረንት(Line current) እና ፌዝ ከረንት(Phase current) እኩል ናቸው። IL=Ip
3. ፌዝ ቮልቴጁ(Phase Voltage/220V) በ√3 ሲባዛ የመስመር ቮልቴጁን(Line Voltage/380V) ይሰጠናል። VL= √3*Vp
4. ፌዝ ቮልቴጁ አነስተኛ ስለሆነ አነስተኛ የፕላስቲክ ሽፋን(Insulation cover) ይጠቀማል።
5. 3- ፌዝ 4-ኤሌክትሪክ ገመድ ያላቸውንም ሆነ 3-ፌዝ 3-ኤሌክትሪክ ገመድ ያላቸውን ሲስተሞች ይቀበላል።
6. ፍጥነቱ አነስተኛ ነው ምክንያቱ ደግሞ ፌዝ ቮልቴጁ(220v) አነስተኛ ስለሆነ ነው።
7. ብዙ ጊዘ ሲነሱ አነስተኛ ከረንት(low starting current) ለሚፈልጉ እና እረጅም እርቀት ላላቸው አገልግሎቶች እንጠቀመዋለን።
8. ሁለት የተለያዩ መጠን ያላቸውን ቮልቴጆች(220V & 380V) እንድንጠቀም ያስችለናል።
🔹#ዴልታ/ #Delta
1. ሶስት ኤሌክትሪክ ወየሮች ብቻ አሉት(ኒውትራል የለውም)።
2. ፌዝ ከረንት(Phase Current) በ√3 ሲባዛ የመስመር ከረንት(Line current) ይሰጠናል። IL= √3*Ip
3. የመስመር ቮልቴጅ(Line Voltage) እና ፌዝ ከረንት(Phase Voltage) እኩል ናቸው። VL=Vp
4. ፌዝ ቮልቴጁ ከፍተኛ ስለሆነ ከፍተኛ የፕላስቲክ ሽፋን(Insulation cover) ይጠቀማል።
5. 3-ፌዝ 3-ኤሌክትሪክ ገመድ ያላቸውን ሲስተሞች ብቻ ይቀበላል ምክንያቱም ኒውትራል የለውም።
6. ፍጥነቱ ከፍተኛ ነው ምክንያቱም ፌዝ ቮልቴጁ(380v) ከፍተኛ ስለሆነ ነው።
7. ብዙ ጊዘ ሲነሱ ከፍተኛ ቶርክ (high starting torque) ለሚፈልጉ እና አጭር እርቀት ላላቸው አገልግሎቶች እንጠቀመዋለን።
8. 380V ቮልቴጅ ብቻ ያስጠቅማል።
ወ.ዘ.ተ
✅#ሼር #ሼር #ሼር
✅ #የአጭር_ጊዜ_ሙያ ስልጠና_ከፈለጉ ይደውሉ❗️
0991156969
0118644716
#አድራሻ፦
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)
👉#ስለምትከታተሉን_እናመሰግናለን🙏
👉#ለሌሎችም_ያጋሩ❗️
"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን!"
🔹🔸🔹ለወዳጅዎም ያጋሩ!🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹እናመሰግናለን!🔹🔸🔹
BY Amen Electrical Technology Official®

Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2633