tgoop.com/amenelectricaltechnology/2526
Last Update:
✅ #የኤሌክትሪክ_መኪና_ከመግዛትዎ_በፊት_ማወቅ_ያለብዎ_ወሳኝ_ነጥቦች
======================
👉በሐገራችን ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሺከርካሪዎች በስፋት እየገቡ እንደሆነ ይታወቃል። ነገር ግን እነዚህን ተሽከርካሮዎች ከመግዛታችን በፊት ከሌላው አለም በተለየ መልኩ ልናስብባቻው የሚገቡን ነጥቦች እንዳሉ በተለያዩ ቤቶች ለሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ለመዘርጋት ስንሄድ አስተውለናል እንደሚከተለው እናያቸዋለን❗️
1. የቤታችን ኤሌክትሪክ ቆጣሪ መኪና ቻርጅ የማድረግ አቅም አለው ወይ❓
👉እንደሚታወቀው በሀገራችን ኢትዮጵያ የሀይል እጥረት እንዳለ ይታወቃል። በዚህም የተነሳ ለመኖሪያ ቤት የሚፈቀደው ነጠላ ፌዝ 25A ነው። በዚህም የተነሳ ብዙ ቤቶች ምጣድ ለኩሶ ተጨማሪ ስቶቭ፣ ውሃ ማሞቂያና የመሳሰሉትን በተመሳሳይ ሰዐት ከተጠቀሙ የቆጣሪው ብሬከር እየመለሰ እንደሚያስቸግር የታወቀ ነው። በዚህ ላይ የመኪና ቻርጀር ከተጨመረበት ቆጣሪው እየመለሰ መጠቀም አይቻልም። ለመኪና ቻርጀር ከ 20A ብሬከር እና ከዛ በላይ የምንጠቀም ሲሆን ቻርጅ ማረግ ከፈለግን ራሱን ችሎ አንድ ቆጠሪ ስለሚፈልግ ከላይ ያሉትን እቃዎች እጥፍተን ቻርጅ ማረግ እንዳለብን መረዳት ይኖርብናል።
👉ስለዚህ 25A ቆጣሪ ያለው መኖሪያ ቤት ላይ ከ20A በላይ የሆኑትን #ፋስት_ቻርጀሮች መጠቀም እንደማንችልና በመደበኛው ቻርጀር ብቻ እንደሚጠቀሙ መረዳት ይኖርብዎታል።
2. የቤታችን ኤሌክትሪክ Ground/Protective Earth ተሰርቶለታል ወይ❓
👉Ground/Protective Earth የሰውን ህይዎት ወይም ንብረቶቻችን ከኤሌክትሪክ አደጋ የሚከላከል ወሳኝ የደህንነት ጉዳይ ቢሆንም ከባለሙያ የግንዛቤ ችግር ወይም ችልተኝነት የተነሳ ብዙ ትላልቅ ህንፃዎች ሳይቀሩ ያለ Ground/Protective Earth ተሰርተው ይገኛሉ። በውጪው አለም እነዚህንና መሰል የኤሌክትሪክ ደህንነት(Electrical Safety) ሳያካትቱ የተገነቡ ቤቶች አገልግሎት እንዳይጀምሩ፣ በለቤቱም እነዚህንና መሰል ጉዳዮችን ሳያሰራ መሸጥም ሆነ ማከራየት አይችልም።
👉የኛ አገር ግን ቁጥጥር ስለማይደረግ ስራውን በሚሰራው ባለሙያ ስለሚወሰን እንዲሁም ባለሙያ ሲመረጥም ቸልተኝነቱ ስላለ እጅግ በጣም ብዙ ቤቶች Ground/Protective Earth የላቸውም።
👉አብዛኞቹ ቻርጀሮች ደግሞ ለመኪናው ደህንነት ሲባል Ground/Protective Earth ካላገኙ እንዳይሰሩ ተደርገው የተመረቱ ናቸው።
3. የኤሌክትሪክ መኪና ብግዛ የት ነው ቻርጅ የማደርገው❓
👉 በሀገራችን ኢትዮጵያ እንደሌሎች ሀገሮች የኤሌክትሪክ ስቴሽኖች ገና አልተቋቋሙም። ስለዚህ ተከራይተው ለሚኖሩና የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ለሚኖሩ ሰዎች መኪናቸውን ቻርጅ ለማድረግ የሚያስችል ምቺ ሁኔታ እንደሌለ መረዳት አስፈላጊ ነው።
4. ዝርጋታውን የሚሰራ ብቁ ባለሙያ እንዴት አገኛለሁ❓
👉የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጀር መስመር መዝርጋቱ ቀላልና ማንኛውም ባለሙያ የሚዘረጋው ቢሆንም የብሬክር
መጠን፣ የገመድ መጠን፣የሶኬት ወዘተ በትክክል መምረጥ የሚችልና ከመኪናዎች ጋር ትውውቅ ያለው በቁ ባለሙያ ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነ በሚሊዮን የተገዛ መኪና ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል።
✅ #የመኪና_ቻርጀርና ሌሎች #የኤሌክትሪክ ስራዎችን #በጥራትና_በተመጣጣኝ ዋጋ ማስራት ከፈለጉ ይደውሉ❗️
👇👇👇👇👇
0118644716
0991156969
"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን❗️"
🔹🔸🔹#ለወዳጅዎም_ያጋሩ❗️🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹#እናመሰግናለን❗️🔹🔸🔹
BY Amen Institute of Technology Official®
Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2526
