tgoop.com/amenelectricaltechnology/2467
Last Update:
🔹🔸🔹#መጥፎ_የህንፃ_የኤሌክትሪክ_መስመር_ዝርጋታ_ምልክቶች/#Signs_of_bad_Wiring
=========================
👉 በሀገራች ልክ ያልሆነ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ለሰው ሂወት መጥፋትም ሆነ ለንብረት ውድመት እንደዋና ምክንያት የሚጠቀስ ይጠቀሳል። ለዚህ ደግሞ እንደ ዋና ምክንያት የሚጠቀሰው በተለይ ለህንፃ የኤሌክትሪክ ስራዎች ትኩረት አለመስጠት እና የሚሰራውን ሙያተኛ የሙያ ሁኔታ ግምት ውስት አለማስገባታችን ነው።
👉ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በትክክል ያልተሰራ የህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ምልክቶች ሲሆኑ መስተካከል ያለባቸው ናቸው።
1. #ከመጠን_በላይ_የኤሌክትሪክ_ገመድ_የበዛበት_ፓኔል/ #Overloaded_Electrical_panel
👉ከምናስበው በላይ የተዝረከረኩ የኤሌክትሪክ ገመዶች ፓኔላችን ወይም ዲስትሪቢውሽን ቦርድ ላይ ካሉ ልክ አይደልም።
👉ግልፅ የሆነ አስተሳሰር እና እርዝመታቸውም በልክ መሆን አለበት።
2. #መብራቶች_የሚርገበገቡ_ወይም_ፈዛዛ_ከሆኑ / #Blinking_or_dim_lights
👉ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚርገበገቡ መብራቶችን ችላ ይላሉ። መብራቶች ሙሉ ለሙሉ ካልጠፉ የሚርገበገቡ ወይም የደበዘዙ ሌላው ቀርቶ እዝዝ.. የሚል ድምፅ ድምፅ የሚያሰሙ መብራቶች እንዲታዩ አይደረግም።
👉ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች ያረጁ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ፣ ኤሌክትሪክ ገመዶች እርስበርስ የታሰሩበት ቦታ የላላ ወይም ከመጠን በላይ የሆነ ጭነት ስለሚሆን በብቁ ሙያተኛ ታይተው መፍትሄ መስጠት አለበት።
3. #ብሬከር_ቶሎ_ቶሎ_የሚመልስ_ከሆነ/#Tripping_Circuit_Breaker
👉ብሬከሮች የተሰሩት የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ችግር ሲኖር እንዲመልሱ ተደርጎ ነው።
👉የሚሰጡት ምላሽም በጣም ፈጣን ሲሆን በኤሌክትሪክ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን እሻት ለማስቀረት ሀይሉን ያቋርጡታል።
👉እነዚህ ሰርኪዩቶች በተደጋጋሚ የሚመልሱ ከሆነ መስመሩ መታየት ይኖርበታል።
4. #እዝ_የሚል_ድምፅ__ወይም_የሚነዘር_ከሆነ/ #Buzzing_Sound_or_Electric_Shock
👉እዝ የሚል ድምፅ ካለ ኤሌክትሪክ ከረንት በዙሪያው ባሉ ሌሎች የኤሌክትሪክ ሽቦች መካከል ወይም አጠገቡ በሚገኙ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ በሆኑ እቃዎች ይፈሳል ማለት ነው።
👉ይህ ምልክት የሚያሳየው የኤሌክትሪክ ዝርጋታው መታየት እንዳለበት ነው።
👉ይህ ምልክት ከጊዜ በኋላም ሊከሰት ይችላል።
5. #የቃጠሎ_ሽታ/ #Burning_Odor
👉ይህ ምልክት ብዙ ጊዜ የሚታይ ችግር ሲሆን የኤሌክትሪክ ገመዶች በጣም ሲሙቁ ይከሰታል።
👉በዚህ ጊዜም ቶሎ መፍትሄ ካልተሰጠው የኤሌክትሪክ ሽቦው የውጨኛው ክፍል ይቀልጥ እና ፌዝና ኒውትራል ይገናኙ እና ሾርት ሰርኪዩት፣ የመብራት መቋረጥ ወይም እሳት ሊከሰት ይችላል።
6. #ማብሪያ_ማጥፊያዎች_እና_ሶኬቶች_ከሞቁ / #Hot_outlets_or_Switches
👉 ሶኬቶች ወይም ማብሪያ ማጥፊያዎች አይሞቁም። ነገር ግን የሚሞቁ ከሆነ ልክ ስላልሆነ ብሬከር አጥፍቶ የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመጥራት መሰራት አስፈላጊ ነው።
#ስለምትከታተሉን_እናመሰግናለን❗️
#ማንኛውንም_የኤሌክትሪክ_ስራ_ለማሰራት_ወይም_የሙያ_ስልጠና_ለመሰልጠን_የሚከተሉትን_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል❗️
👇👇👇👇👇
0118644716
0991156969
"#ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
🔹🔸🔹#ለወዳጅዎም_ያጋሩ!🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹እናመሰግናለን!🔹🔸🔹
BY Amen Institute of Technology Official®
Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2467
