tgoop.com/amenelectricaltechnology/2461
Last Update:
✅#የፍሪጅ_ኮምፕረሰር_እና_መፍትሄው
✅#Compressor_problem_and_solution
====================
👉ስለ ፍሪጅ ኮምፕረሰር ብልሺት ከማየታችን በፊት ኮምፕረሰር ምንድን ነው የሚለውን እናያለን።
👉ኮፕረሰር አንድ ፍሪጅ ካሉት 5 ዋና ዋና ክፍሎች ማለትም ኮንደንሰር፣ ኢቫፖሬተር ፣ ካፕላሪ ቱዩብ ፣ ፊልትሮ ማካከል ዋናው እና የፍሪጁ ወሳይ ክፍል ነው።
👉 ዋናው የስራ ድራሻውም አነስተኛ ግፊት ያለው ጋዝ ተቀብሎ ከፍተኛ ግፊት በመፍጠር ወደ #ኮንደንሰር መላክ ነው። የፍሪጁን ሲስተም ስራ የሚያስጀምረውም ኮምፕረሰር ነው።
👉ኮምፕረሰር ከተበላሸ ወይም ፓወር ካልደረሰው ፍሪጁ ሊጀመር/ሊነሳ አይችልም።
👉ኮምፕረሰር ኤሌክትሪካል እና ሜካኒካል ክፍሎች አሉት።
#ኤሌክትሪካል_ክፍሉ ሞተሩ ሲሆን ሞተሩም ዋና ጥቅል (main Winding)-አነስተኛ ሪዚዝታንስ ያለው እና ረዳት ወይም አጋዥ ጥቅል (Auxiliary Windings)-ከፍተኛ ሪዚዝታንስ ያለው እንዲሁም ኦቨርሎድ ሪሌይ(Overload relay) እና ማስጀመሪያ ሪሌይ(Starting Relay) ናቸው።
#Overload_relay-የሞተራችን ጥቅል(Winding) የሚጠብቅ መሳሪያ ነው።
#Starting_relay- ሞተሩ ሲጀምር የሪዚዝታንስ መጠኑን በመጨመር ሞተሩ ሲነሳ የነበረውን ከረንት በመቀነስ ያለምንም ጉዳት ለማስነሳት እና ከተነሳ ብኋላ በመክፈት ያለምንም ችግር ሞተሩ #በዋናው_ጥቅል እንዲሰራ የሚያደርግ መሳሪያ ነው።
👉#ሜካኒካል ክፍሎቹ ደግሞ የጋዝ መሙያወቹ(Charging ) እና የጋዝ ማስዎጫ(Discharging) ናቸው።
👉 ይህንን ያህል ካልን የኮምፕረሰር ብልሽቶች ምን ምን ናቸው? መፍትሄውስ? የሚለውን እናያለን።
#ብልሺቶች
1. #ኮምፕረሰሩ_አይነሳም/#Compressor_is_not_start
✅መፍትሄ
👉ኮምፕረሰር የማይጀምረው በነዚህ 3 ዋና ዋና ምክንያቶች ነው።
ሀ. #ኤሌክትሪክ-ፓወር_ካላገኘ
✅#መፍትሄ➖የኤሌክትሪክ ፓወር መኖሩን ማረጋገጥና እንዲያገኝ ማድረግ።
ለ. #የኦቨርሎድ_ሪሌይ እና #የስታርቲን_ሪሌይ ብልሽት
✅#መፍትሄ➖እነዚህ ከተበላሹ አረጋግጦ በራሳቸው ሳይዝ መቀየር ።
ሐ. #የጥቅል(Wending) መበላሽት
✅#መፍትሄ➖ኮምፕረሰር መቀየር።
2. #ኮምፕረሰር_በተደጋጋሚ_እየጀመረ_ይጠፋል
#Compressor_Frequently ON/OFF
ሀ. #ኮፕረሰሩ_ስታክ_ሲያደርግ
✅መፍትሄ➖ኮምፕረሰር መቀየር
ለ. #የፍሪጁ_የጋዝ_መተላለፊያ_መስመር ሲዘጋ
✅#መፍትሄ➖ፊልትሮ በመቀየር ይስተካከላል።
ሐ. #አንዱ_ጥቅል(winding) ክፍት ከሆነ
✅#መፍትሄ➖ኮምፕረሰር መቀየር
መ. #ስታርቲንግ_ሪሌይ_ከተበላሸ
✅መፍትሄ➖ስታርቲንግ ሪሌይ መቀየር
3. #ከፍተኛ_የሆነ_ድምፅ_የሚያሰማ ከሆነ
#High_Noise
ሀ. #የፍሪጁ_አቀማመጥ ሳይስተካከል ሲቀር
✅#መፍትሄ➖የተስተካከል ቦታ ላይ አመቻችቶ ማስቀመጥ
ለ.
. #የፍሪጁ_የጋዝ_መተላለፊያ_መስመር ሲዘጋ
✅መፍትሄ➖ፊልትሮ በመቀየር ይስተካከላል።
ሐ. #ሜክኒካል_ብልሺት
✅መፍትሄ➖ኮምፕረሰር መቀየር
#ማሳሰቢያ
👉ኮምፕረሰር ስንቀየር በነበረው ኮምፕረሰር የፈረስ ጉልበት(horse power) መሆን አለበት።
👉ስታንዳርድ የሚባሉት ኮምፕረሰሮች የፈረስ ጉልበት የሚከተሉት ናቸው።
1/3hp, 1/4hp,1/5hp, 1/6hp 1/8hp እና 1/10hp ናቸው።
👉ኮምፕረሰር በምንቀይር ጊዜ የፍሪጁ የጋዝ መተላለፊያ መስመሩ ተፀድቶ ጋዝ መሞላት አለበት።
👉#በግል_ወይም_በቡድን_የሙያ_ስልጠና_ለመሰልጠን_በሚከተሉትን_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል❗️
👇👇👇👇👇
0991156969
0118644716
" #ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
🔹🔸🔹 #ለወዳጅዎም_ያጋሩ!🔸🔹
🔹🔸🔹🔹 #እናመሰግናለን!🔹🔸
BY Amen Institute of Technology Official®
Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2461
