tgoop.com/amenelectricaltechnology/2408
Last Update:
✅#አስደሳች_ዜና
=======
👉 #አሜንን_ከመረጡ_በብዙ_እጥፍ_ያተርፋሉ❗️
👉ድርጅታችን አሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ ከ8 ዓመት በላይ በኤሌክትሪክ ስራ ዘርፍ ተሰማርቶ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ የተሳተፈና አመርቂ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን በቅርብ ደግሞ ከነፃ የመስመር ላይ ስልጠና ባሻገር በአካል የአጭር ጊዜ ስልጠና #በማሰልጠንና_በማስቀጥር ለብዙ ወጣቶ የስራ ዕድሎችን የፈጠረ መሆኑ የሚታወቅ ነው አሁን ደግሞ #ከተቋማችን_ለሰለጠኑ_ባለሙያዎች_ብቻ_ትልቅ_እድል ይዞ መቷል❗️
👉ከዚህ በፊት በ 20 ዙሮችና በግል ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች በሚኖሩበት አካባቢ የጥገና ስራዎች ወደ ድርጅታችን ሲመጡ በቀጥታ ለባለሙያዎች በማስተላለፍና ተጠቃሚ ለማድረግ አስቦ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ከዚህ ቀን ጀምሮ ባለሙያዎች ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጀውን በአካል ቢሮ በመምጣት በመሙላት የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ስንገልፅ በደስታ ነው❗️
👉የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ምንም አይነት ክፍያ የማይጠይቅ ሲሆን ነገር ግን የደንበኞቻችን ደህንነት ለመጠበቅና ሐላፊነት ለመውሰድ ይረዳን ዘንድ ባለሙያዎች የሚከተሉትን መረጃዎች ማቅረብ አለባቸው፦
1. የአዲስ አበባ መታወቂያ ኮፒ
2. አንድ ጉርድ ፎቶ
3. ለዚህ አላማ የተዘጋጀውን ፎርም ሞልቶ መፈረም(ለስራ በሄዱበት ቤት ያልተገባ ተግባር ወይም የስራው ዲሲፕሊን ከሚፈቅደው ድርጊት ውጪ ቢፈፅሙ ተጠያቂ የሚያደርግ ውል)
👉ከየዙሩ ለ 2 ባለሙያዎች ብቻ(40) #አገልግሎታቸውንና_መገኛ ቦታቸውን እንዲሁም #ስልክ_ቁጥራቸውን በቪዲዮ ለማስተዋወቅ እድል የምንሰጥ ሲሆን መስፈርቱም፦
1⃣. ስማቸውንና ስልክ ቁጥራቸውን ቀድመው የላኩ፣
2⃣. የቀረፃ ቀን ዘወትር እሁድ ከ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ስለሆነ ቢሮ ተገኝቶኣ መቀረፅ የሚችል፣
3⃣. አገልግሎቱን በቅንነት ለመስጠት ቁርጠኛ የሆነ @electricexpert
#ማሳሰቢያ፦
1⃣. አንድ ባለሙያ የቀረፃ ቀን ቀጠሮ ተሰቶት በቀጠሮው ቀን ባይገኝ #ሁለተኛ እድል አይሰጠውም❗️
2⃣. የግል መረጃቸውን ለመስጠት ዘወትር #ከሰኞ- #ቅዳሜ በስራ ሰዓት በመምጣት መስጠት ይችላሉ❗️
3⃣. ድርጅታችን ለስራ ልኳችሁ ለሚፈጠሩ አላስፈላጊ ድርጊቶች እንደ ንብረት መጥፋት፣ ከሙያ ክፍተት ለሚበላሹ እቃዎች ወዘተ ባለሙያዎች ተጠያቂ ናቸው❗️
4⃣. ድርጅታችን አሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ ደንበኛቻችን ከማስደሰትና ለባለሙያዎች የስራ ዕድል ክውመፍጠር ውጪ ከሁለቱም ወገን ምንም አይነት ክፍያ አይጠይቅም❗️
5⃣. ባለሙያዎች የዚህ እድል/ስራ በሙሉ ሰዓት ወይም በትርፍ ሰዓት ሊሰሩት ይችላሉ❗️
6⃣. የድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑት ከተቋማችን የሰለጠኑ ባለሙያዎች ብቻ ናቸው❗️
አሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ
"ወጣቶች ስለሆንን የወጣቱን ችግር/ፍላጎት በሚገባ እንረዳለን ፤ መፍትሄ ነው ያልነውንም ያለገደብ እንሰጣለን❗️"
BY Amen Institute of Technology Official®
Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2408