tgoop.com/amenelectricaltechnology/2113
Last Update:
የኤሌክትሪክ ስራ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሒደት ---ክፍል-2
======================
3. የፅሁፍና የተግባር ምዘናውን ያለፉ ሰርተፊኬት ይረከባሉ። ያላለፉ ደግሞ ሰነዳቸው ይመለስላቸዋል፡፡
4. አመልካቾች በፈተናው ውጤት ላይ ጥርጣሬ ካላቸው ጥያቄያቸውን ላረመው አካል በማቅረብ ውጤቱ ተመርምሮ ፈጣን ምላሽ ይሰጣቸዋል፡፡
4. ለኤሌክትሪክ ሥራ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማመልከት መቅረብ ስለሚገባቸው መረጃዎችና ማስረጃዎች
I. ማን ኛውም የኤሌክትሪክ ሥራ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚቀርብ አመልካች መጠኑ 3X4 የሆነ ከ6 ወር ወዲህ የተነሳው 2 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ማቅረብ አለበት፡:
II. የኤሌክትሪክ ሥራ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማግኘት ከሚቀርብ ማመልከቻ ጋር እንደደረጃዉ መቅረብ የሚኖርበት የትምህርት ማስረጃ
ሀ) በኤሌክትሪካል ምህንድስና ፣ ኤሌክትሪካል/ኤሌክትሮኒክሰ ቴክኖሎጂ ፣ በኤሌክትሮ ሜካኒካል ምህንድስና ወይም
ለ) የኤሌክትሪክ ሙያ ከማስተማር ጋር የሚያያዝ ትምህርት ማስረጃ (BEd) ወይም
ሐ) በየደረጃው ከሚገኙ የሙያና ቴክኒክ ሥልጠና ኮሌጆች የኤሌክትሪክ ትምህርት ደረጃ ማስረጃ ወይም እዉቅና ካለዉ ተቋም የተገኘ የ60 ሰዓት ሥልጠና ምስክር ወረቀት ወይም የደረጃ 1 (Level 1) ሲኦሲ/COC/ ምስክር ወረቀት
5. የኤሌክትሪክ ሥራ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማግኘት ከሚቀርብ ማመልከቻ ጋር የሚቀርብ የሥራ ልምድ ማስረጃ ከዚህ በታች በተመለከተው መሠረት ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ የሥራ ልምድ ተብሎ ይያዛል፡:
ሀ) የሥራ ልምድ ማስረጃው ከኤሌክትሪክ ሥራ ጋር የተያያዘ ሥራ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ሲስተም ግን ቦታና ኦፕሬሽን ፣ ምርመራ/ፍተሻ፣ የምህንድስና ስሌቶች አጠቃቀም፣ በቁጥጥር ማረጋገጥ፣ ንድፍ ማውጣት/ማዘጋጀት፣ የኤሌክትሪክ ሥራዎች ማማከር፣ የኤሌክትሪክ ኃይሌ ሲስተም ሥራ እቅድ አደረጃጀት፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችና መሳሪያዎችን ኢንስታሌሽን ፣ የህንጻ፣ ኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክ መስመር መዘርጋት፣ በኤሌክትሪክ ዕቃዎች ጥራት ፍተሻና ምርመራ፣ የኤሌክትሪክ መለኪያ መሳሪያዎች ንጽጽር እና ጥገና (calibration and repair)፣ የኤሌክትሮ ሚካኒካል ሥራ ወይም ኤሌክትሮ ሚካኒካል ሥራ ጥገናና እድሳት፣ የባዮሜድካል ዕቃዎችና መሣሪያዎች ተከላና ጥገና ፣ ቲዎሪና ተግባርን በማጣመር ማስተማርን የሚያረጋግጥ ከሆነ ቀጥተኛ የሆነ የሥራ ልምድ ተደርጎ ይያዛል፡:
ለ) የአመልካቹ የሥራ ልምድ ማስረጃ ከላይ በተመለከተው አግባብ ከኤሌክትሪክ ሥራ ጋር በቀጥታ ያልተያያዘ ሲሆን የሥራ ልምደ ቀጥተኛ ያልሆነ ተብሎ በግማሽ ይያዛል፡:
6. አመሌካች በግል ወይም በራሱ ስም በተመዘገበ ድርጅት የሚሰራ በሆነ ጊዜ የሥራ ልምድ ማስረጃውን “ከክንዋኔ ዝርዝር” እና ኮንትራት ውል ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡:
7. የደረጃ 1 የኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን አመልካች ሥራ ልምድ ማስረጃው ከላይ በተመለከተው መሰረት ባልሆነ ጊዜ አመልካች ለደረጃው ማመልከት የሚችለው የደረጃ “2” የኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን ብቃት ማረገጋገጫ ምስክር ወረቀት ወስዶ ቢያንስ 2 ዓመት ወይም የደረጃ “3” ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ወስዶ ቢያንስ 4 ዓመት የሥራ ልምድና የሥራ ልምዱ ከላይ ከተመለከቱት ሥራዎች ቢያንስ ባንዱ መስራቱን የሚያስረዳ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነ ው፡:
8. የአገልግሎት ክፍያ
በኢነርጂ ደንብ ቁጥር 447/2011 ዓ.ም አንቀጽ 20 መሰረት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትን በተመለከተ ባለሥልጣኑ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚፈጸሙ የአገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ዝርዝር ክፍያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል ፡፡
ለደረጃ 1 አጠቃላይ የአገሌግሎት ክፍያ ብር 606.64
ለደረጃ 2 አጠቃላይ የአገሌግሎት ክፍያ ብር 485.31
ለደረጃ 3 አጠቃላይ የአገሌግሎት ክፍያ ብር 363.98
ለደረጃ 4 አጠቃላይ የአገሌግሎት ክፍያ ብር 242.66
ክፍል-2
ከነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን የተወሰደ
#ማሳሰቢያ
1. የብቃት መረጋገጫ ለማውጣት ከመሄዳችሁ በፊት በ online ማመልከት አለባችሁ።
2. ቢሯቸው የሚገኘው ጉርድ ሾላ ወይም ላምበረት መነሀሪያን አለፍ ብሎ
በማዕድን ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።
BY Amen Institute of Technology Official®
Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2113