AMENELECTRICALTECHNOLOGY Telegram 2045
አንብቡት ይጠቅማችኋል❗️
ይህን በጣም ጠቃሚ ምክሮች የያዘውን ልጥፍ ከ 3 ወይም ከ 4 አመት በፊት ለጥፈንላችሁ ነበር። እጅግ በጣም ጠቃሚ ምክር ነው ተግባራዊ ብታደርጉት ትጠቀሙበታላችሁ። አሁን ላይ ድግሪ ያልው ሰው በዝቷል ስራ ማግኘት የሚቻለው ራስላይ ልዩነት የሚፈጥር ነገር በመጨመር ነው። በሰሞኑ የስራ ማስታወቂያዎች ያየናቸው ነገሮች ደግመን እንድንለጥፍ አነሳስተውናል።

#እንዴት_በቀላሉ_ስራ_ማግኘት_ይቻላል
(#ለአዲስ_ተመራቂ_ተመሪዎች_ወይም_ስራ_ፈላጊዎች_ጠቃሚ ምክሮች)
=====================

👉በመጀመሪያ ስለተመረቃችሁ እንኳን ድስ አላችሁ❗️
👉በመቀጠል መቸም ተመርቆ ስራ መፈለግ ግድ ነውና ለመቀጠር የሚያግዟችሁን ጠቃሚ ምክሮች ላካፍላችሁ❗️
👉ከስንት አመት ትምህርት በኋል ወደ ስራ መምጣት የሂወታችን ሌላኛው አቅጣጫ ነው። ስለዚህ እንዴት ወደዚህ ምዕራፍ በቀላሉ መግባት እንደምንችል ያለኝን ልምድ አካፍላችኋለሁ መልካም ንባብ🙏
1. #አቅማችን_ማወቅ
👉ለፈተና ወይም ለቃለ-መጠይቅ ለመቅረብ ከሀገራችን የስራ አጥ ቁጥር አንፃር ከፍተኛ ውጤት እጅግ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ከፍተኛ ውጤት ስላለን ብቻ መቀጠር እንችላለን ማለት አይደለም። ቃለ-መጠይቅ ላይ ጎበዝ መሆን አለብን፤ የፅሑፍ ፈተናም ካለ በቀላሉ እንዴት ማለፍ እንችላለን ወ.ዘ.ተ የሚሉት ወሳኝ ናቸው። ውጤት መጀመሪያ ፈተና ላይ ለመቅረብ እድል ነው የሚሰጠን እድሉን መጠቀም ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው። ስለ ቃለ-መጠይቅ ሌላ ጊዜ በሰፊው እናያለን፤ እጅግ አስፈላጊ ስለሆነና ብዙ ሰወች ሁሉን ነገር አልፈው እዚህ ጋ ሰለሚሰናበቱ።
👉አቅማችን ማወቅ ሲባል ድግሪው ስላለን ብቻ ወይም ከፍተኛ ውጤት ስላለን ብቻ እንደ ትልቅ ስኬት መቁጠር ሳያስፈልግ ክፍተታችን ማወቅና መሙላት እጅግ አስፈላጊ ነው።
👉ከፍተኛ ውጤት ካለን ለፅሑፍ ፈተና እና ለቃለ-መጠይቅ እንዲሁም ተግባር ተኮር ስለሆኑ ነገሮች መዘጋጀት መልካም ነው።
👉ውጤታችን ዝቅተኛ ከሆነ ደግሞ የመጀመሪያው ትኩረታችን መሆን ያለበት የስራ ልምድ ላይ ነው። ለወራት ወይም ለአመታት በተመረቅንበት ዘርፍ ስራ ከሰራንና ህጋዊ የስራ ልምድ ካለን የተሻለ ቅጥር ስንፈልግ የስንት አመት የስራ ልምድ አለህ/ሽ እንጅ የዩኒቨርሲቲ ውጤትህ/ሽ ስንት ነው ተብሎ አይጠየቅም። ስለዚህ ስራ ሳንመርጥ ደሞዙ ምንም ይሁን ምን የምሰራው ስራ እኛ በተመረቅንበት ዘርፍ ከሆነ ያለማመንታት እንዲቀጠሩ እመክራለሁ። ልምድ ከያዙ ባኋላ ወደሚፈልጉት ስራ መምጣት ስለሚችሉ።
2. #ልዩነት_መፍጠር
👉ዲግሪ ያለህ አንተ/አንች ብቻ እንዳልሆክ/ሽ ታቃለህ/ሽ? በጣም ብዙ ሺወች አሉ። ስለዚህ አንተ ከሌሎች ተለይተህ መገኘት አለብህ። እንዴት?
🔘 በነፃ በመስራት
👉 ዩኒቨርሲቲ እያለህ በትርፍ ጊዜህ ካልሆነ ከተመረክበት ቀን ጀምሮ ያለክፍያ እራስክን ማስተማር። #ነፃ አገልግሎት በመስጠት ልምድ መያዝና እንዴት እንደሚሰራ ማወቅ ትችላለህ። ሰው ከፍሎ ይማራል፤ ስለዚህ እስከምትቀጠር ድረስ አትቀመጥ ከአንተ ዘርፍ ጋር የሚስማማ ድርጅት ወይም ግለሰብ መርጠህ አብረህ ስራ።
🔘 አጫጭር ስልጠናወችን መሰልጠንና የምስክር ወረቀት መያዝ እንዲሁም ክህሎትን በደንብ ማዳበር አሁን ላይ ወረቀት ብቻ ሳይሆን ክህሎት ነው የሚፈለገው።
🔘 የCOC ፈተና መፈተን
🔘ሌሎች በዘርፉ የሚሰጡ የብቃት
ማርጋገጫ የምስክር ወረቀቶች ካሉ ከሚመለከተው አካል መውሰድ
3. #ለገንዘብ_ሳይሆን_ለሞያ_መገዛት
👉ለገንዘብ ብለን እኛ ከተመረቅንበት ዘርፍ ውጭ ስራ ከጀመርን ወደ ተመረቅንበት ሙያችን የመመልስ እድላችን አነስተኛ ነው። ጊዜው በሄደ ቁጥር ምንም ያልሰራህበት ድግሪ እንዳልተማርክ ይቆጠራል የስራ ልምድህ  0 አመት ሲቀጥል የተመርከውንም ትረሰዋልህ። ስለዚህ ክፍያ ላይ ሳይሆን የምንሰራው ስራ ከተማርኩት ዘርፍ ጋር አብሮ ይሄዳል ወይ? የስራ ልምዴ ጠቃሚ ነው ወይ? የሚሉትን ማየት መልካም ነው።
👉ለትንሺ ጊዜ በዘርፋችን በትንሺ ብር ብንሰራ ከተወሰነ ጊዜ ባኋል ተፈላጊ ነን።
4. #ቃለመጠይቅ_ላይ_ብልህ_መሆን
👉አንዳንድ ድርጅቶች የፅሑፍ ፈተና የማይፈትኑ አሉ። ቃለመጠይቅ ብቻ አርገው የሚቀጥሩም አሉ።
👉አንዳንዶች ደግሞ የፅሑፍ ፈተና + ቃለመጠይቅ የሚያደርጉ አሉ።
👉ስለዚህ ቃለ-መጠይቅ ላይ ብልጥ መሆን እጅግ አስፈላጊ ነው።
5. #የቅጥር_ማስታወቂያ_የሚሰሩ_ድህረ_ገፆችን_መከታተል
👉ብዙ ማህበራዊ ሚዲያዎችና እንደ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ጋዜጦች፣ ሊንክዲን ወዘተ ሌሎችንም መከታተል።
6. #ስራ_አለመምረጥ
👉በተመረቅንበት ዘርፍ ከሆነ ከፍያው አነስተኛ ቢሆንም ያገኙትን እየሰሩ የተሻለ መፈልግ አስፈላጊ ነው።
👉በነገራችን ላይ አብዛኞች ድርጅቶ የሚያስቡት አዲስ ተመራቂ መቅጥር እየከፈሉ እንደማስተማር ነው የሚቆጥሩት። በቂ ልምድ ከያዘ በኋላ ደግሞ የተሻለ ፍለጋ ልምድ እንዲያገኝ ዕድል የሰጠውን መስሪያቤት ሳያገለግል ይወጣል። በዚህ የተነሳ አብዛኞች ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ ድርጅቱን መጥቅም የሚችል ሰራተኛ ነው የሚፈልጉት። ለዛ ነው አሁን ላይ በዜሮ አመት በብዛት ቅጥር የማይገኘው።
7. #ለመንግስት_መስሪያቤቶች_ቅድሚያ_መስጠት
👉የመንግስት ቤቶች ክፍያቸው ጥሩ እየሆነ ነው።
👉 ሌላው እንደ ትምህርት፣ቤት፣ መኪና እና  እድሎች እድሎችን ማግኘት እንችላለን።
8. #ሳቢ_የሆነ_ሲቪ_ማዘጋጀት_በየጊዜው_ማሻሻል
👉
የብዙ አመልካቾች ችግር ቆንጆ ሲቪ ማዘጋጀት አለመቻልና  በኢሜል የምናመለክት ከሆነ ዶክመንቶቻችን በሚገባ ማደራጀትና በአንድ pdf ማዘጋጀት አለብን።
👉እኔ የታዘብኩት ብዙዎች እያንዳንዱን የትምህርት ማስረጃ በፎቶ የሚልኩ አሉ እሱን እየለቀመ የሚያይ ቀጣሪ ድርጅት የለም።
👉 ብዙዎቻችን ሲቪ አንዴ ካዘጋጀን አናሻሽለውም ያለንን ልምድ በማካተት በየጊዜው መሻሻል አለበት።
👉የስራ ማስታወቂያው ላይ ከልተጠየቀ በስተቀት በድግሪ የተመረቀ ሰው ከ8-12ኛ ክፍል ያለው ወጤታችን አስፈላጊ አይደለም። የማይጠቅም ዶክመንት ባበዛን ቁጥር ቀጣሪው ድርጅት ላይ ስራ ማብዛት ነው።
9. #ለፈተና_ወይም_ለቃለ_መጠይቅ_ስለተጠራን መ/ት በቂ መረጃ መሰብሰብ

👉ከዚህ በፊት ድርጅቱ ወስጥ ተቀጥረው ከሚሰሩትና ከመ/ቱ ድህረ-ገፅ መረጃ መሰብሰብ።
👉ምንም ያህል ጎበዝ ነኝ ብትል/ይ መረጃ ያለው ሰው ይበልጥሃል/ሻል። ስለዚህ መረጃ ካለን አንድ እግራችን እንደገባ እንመን።
10. #ሁሉንም_መሞከር
👉የወጣው የቅጠር ማስታወቂያ ከኛ ዘርፍ ጋር ተመሳሳይ ከሆነ 1 ሰውም ይፈልግ ከዛ በለይ፣ ደሞዙ ትንሺም ይሁን ትልቅ መሞከር አለብን። ከተፈተን በኋላ የሚቀጥሯቸውን ሰወች ብዛት ቢጨምሩስ፣ ከተፈለገው 1 ሰው ያ አንድ ሰው እኔ/አንተ/አንች ብንሆንስ፣ ደሞዝ ቢሻሻልስ፣ የማናቃቸው ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ቢኖሩስ፤ ባይሆን እንኳን ልምድ እናገኝበታለን።
11. ታውቁታላችሁ! አልናገርም😁😁
መልካም ጊዜ🙏

👉#ስለምትከታተሉን_እናመሰግናለን🙏

👉#ለሚወዷቸው_ሁል_ያጋሩ❗️

🔹ለቴሌግራም ቻናላችን:-
                      👇
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAE2DpDe9fPGCTupqTg

#ለዩቱዩብ_ቻናላችን❗️
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw

#ለተጨማሪ_መረጃ፡
👇👇👇👇👇
0118644716
0991156969
0911585854
" #ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን❗️"
🔹🔸🔹#ለወዳጅዎም_ያጋሩ!🔸🔹
🔹🔸🔹🔹#እናመሰግናለን!🔹🔸🔹
👍3721🤩1

tgoop.com/amenelectricaltechnology/2045
Create:
Last Update:

BY Amen Institute of Technology Official®

Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2045

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

The Standard Channel 2How to set up a Telegram channel? (A step-by-step tutorial) best-secure-messaging-apps-shutterstock-1892950018.jpg 3How to create a Telegram channel? How to create a business channel on Telegram? (Tutorial)
from us

Telegram Amen Institute of Technology Official®
FROM American