tgoop.com/alpha_software_enginering/82
Last Update:
ትክክለኛ ያልሆነ ስለኮዲንግ ሚነገሩ myths part 1
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1) ኮድ ላይ ኮመንት መጻፍ አያስፈልግም!!
ይሄ ፍፁም ስሕተት የሆነ መረጃ ነው ኮመንቶች ለአንድ ፕሮግራም መስተካከል የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያደርጋሉ። ሌሎች ሰዎችም በቀላሉ እንዲረዱት ያደርጋል።
2) ፕሮግራሚንግ ለመማር በጣም ውድ የሆኑ ጥራት ያላቸው ነገሮች የግድ አስፈላጊ ናቸው!!
በዋናነት ኮድ ለማድረግ ጥራት ያላቸው መሳሪያዎች የራሳቸው የሆነ አውንታዊ አስተዋፅዖ ቢኖራቸውም ፕሮግራሚንግ ለመማር ከስማርት ፎን ጀምሮ ማንኛውንም ኮምፒውተር መጠቀም ይቻላል።
3) የተሳካ ስራ ልታገኝ አትችልም ግዴታ የኮምፒውተር ሳይንስ ድግሪ ከሌለህ!!
ይሄ ፍፁም ውሸት ሲሆን ብዙ በዚህ ዘርፍ ያሉ ምሁራን በዋናነት ራሳቸውን ያስተማሩ ኦንላይን ሪሶርስ እና ቡትካምፖችን ጆይን ያረጉ ናቸው። ስለዚህ የኮምፒውተር ሳይንስ ዲግሪ ግዴታ አይደለም።
4) ሁሉም ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ተመሳሳይ ናቸው!!
እያንዳንዱ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ የራሱ የሆነ ጥቅም እና ችሎታ አለው ስለዚህ ሁሉም አንድ አይነት አይደሉም።
5) ሁሉንም የፕሮግራሚንጉ ህጎች እና syntax ማወቅ የግድ ነው!!
ሁሉም ዴቨሎፐሮች ሪፈረንስ እየተጠቀሙ ነው ዴቨሎፕ ሚያደርጉት መሰረታዊ ሲንታክሶችን ብቻ ማወቅ በቂ ነው።
6) ኮድ ለማድረግ የማትስ እወቀትህ ከፍተኛ መሆን አለበት!
ኮዲንግ ሎጂካል አስተሳሰብ እንጂ ማቲማቲካል ፎርሙላን በብዛት አይጠቀምም ስለዚህ ግዴታ ከፍተኛ እውቀት አያስፈልግክም ምክንያታዊ አስተሳሰብ እንጂ።
7) አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ የሰውን ልጅ ይተካል*!
የፕሮግራሚንግን አፈጣጠር በእነዚህ ማሽኖች መቀየር ቢቻልም የማሰብ ችሎታ ችግርን የመፍታት እና ውሳኔ የመስጠትን ችሎታ ፍጹም ከሰው ልጅ ውጪ ሊያደርጉት ስለማይችሉ ይሄም ትልቅ ስሕተት ነው።
Share with Your Friends
@Alpha_software_enginering
For any Question
@Alpha_software_engineering
BY Alpha software engineering tutorial
Share with your friend now:
tgoop.com/alpha_software_enginering/82