tgoop.com/abduftsemier/2210
Last Update:
#እንስት_አናብስቶች
በአለም ላይ እልፍ ሴት የአላህ ወሊዬችና ሱፊዎች ሞልተዋል ከነዚህም ውስጥ
;አኢሻ በዑኒይ: አኢሻ ማኑብያ: ሰይዳ አሚና: ሳሚሀ አይቨርዲ: ሃፀይ ባባጃን: ሶከህና ማጋት: ቼማልኑር ሳርጉት: ጃሀኖቲን ኡቪሲይ: ላላ ዘይነብ: የናይጄሪያዋ ሰይዳ ሳራ: እነዚህ ከባህር ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።
ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ሴት በሀዘን ተውጣ ሲቲና ነፊሳ ዘንድ መጣችና... "ያ ሰይደቲ ልጄ ለንገድ ከወጣ ወር አልፎታልና እስካሁን አልተመለሰም ጭንቅ ቢለኝ ነው ወደ አንቱ ጋር ምመጣው ዱኣ አደርጉለት" ስትል ተማፀነች ሲቲ ነፊሳም ትንሽ እንደቆዩ አብሽሪ ልጅሽኮ አልጠፋም እዛው ቤትሽ ታገኚዋለሽ" አሏት.. እናቲቱም በእናት አንጀቷ ወደ ቤቷ ብትመለስ ልጇን አገኘችው የናፍቆቶን አቅፋ ከሳመችው ቡሀላ.. "እንዴት ከወራት መንገድ ባንዴ ልትከሰት ቻልክ" ብላ ጠየቀችው.. ልጁም እንዲህ ሲል መለሰ "እናቴ ሆይ በመንገድ ላይ ሳለሁ ታስሬ ነበር እናም ድንገት ጠባቂው መጥቶ በሩን ከፈተለኝ.. ከዚያም ንፋስ መጣና ካለሁበት አንስቶ እዚህ ቤቴ አመጣኝ" እናት በመገረም "እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ ልጄ?" ብላ ጠየቀችው... እርሱም "በቅድሚያ ከሀዋው ላይ ኻቲፍ እንዲህ ብሎ ሲጣራ ሰማሁኝ" 'ኢፍተህ ለሁ ፊ ሲጅኒ ፈኢነሁ ቢ ሸፈአቲ ሰይደቲ ነፊሳ' (ከታሰረበት በሩን ከፍታቹ አስወጡት ሰይደቲ ነፊሳ ዋስ ሆነውታልና).. ይህንን ድምፅ እንደሰማ ጠባቂው መጥቶ እንደከፈተለት ነገራት።
ከእለታት አንድ ቀን ሰይድ ሀሰነል በስሪይ ሲቲ ራቢያን ከሀይቅ ዳር አገኞት ሰይድ ሀሰነል በስሪም 'ራቢያ ሆይ.. ነይ ውሃው ላይ ሁለት ረከዐ እንስገድ አሏት" ራቢያም "ለምን ማንም ማድረግ የሚችለውን ታደርጋለህ" ብላ አየር ላይ መስገጃዋን አንጥፋ 'ባይሆን ና እዚህ እንስገድ አለቻቸው.. ሀሰነል በስሪም መቃማቸው እሷ ጋር አለመድረሱን ተረዱ.. ሰይዳ ራቢአ እንዲህ ስትል አስደናቂ ንግግር ተናገረች "ሀሰን ሆይ አንተ የፈፀምከው አሳዎች የሚያደርጉትን ነው.. እኔ የፈፀምኩት ዝንቦች የሚያደርጉትን ነው"
@abduftsemier
@abduftsemier
BY Abdu & Hasu
Share with your friend now:
tgoop.com/abduftsemier/2210