Telegram Web
Audio
ወንድሜ ሰይጣን
ደራሲ - ካህሊል ጂብራን
ተርጓሚ - ጲላጦስ
ተራኪ-የአማርኛ መፅሀፍት የዩቲብ ቻናል
@zephilosophy
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
ወንድሜ ሰይጣን ደራሲ - ካህሊል ጂብራን ተርጓሚ - ጲላጦስ ተራኪ-የአማርኛ መፅሀፍት የዩቲብ ቻናል @zephilosophy
ሰይጣንም ለቄሱ እንዲህ አለ

"እኔ ከሞትኩ በችጋር እንደሚሞቱ አይገነዘቡምን? ዛሬ እኔን እንድሞት ጥለውኝ ቢሄዱ ነገ ምን ሰርተው ይኖራሉ? ስሜ ከምድረ ገፅ ድራሹ ቢጠፋ እርስዎ በምን አይነት ሙያ ህይወትዎን ይገፋሉ? ለአስርታት ዓመታት በነዚህ መንደሮች እየተዘወዘወሩ ሰዎችን በወጥመዴ ውስጥ እንዳይወድቁ ሲያስጠነቅቁ ኖረዋል፡፡ እነሱም ለምክሮዎት እና ለአስተምህሮትዎት ውለታ ለመክፈል ሲሉ ደክመው ለፍተው ከሚያገኙት ገንዘብ እና ጥሪት ሲለግሱዎት ቆይተዋል፡፡

ነገ እኔ ክፉ ጠላታቸው መሞቴንና ከዚህ ወዲያ እንደማልኖር ካወቁ ከእርስዎ ዘንድ ምን የሚገዙት ምክርና አስተምህሮ ይኖራቸዋል? ሰዎቹ ከኃጢያት በአስተማማኝ ሁኔታ ስለሚድኑ የዕለት ጉርስዎትን የሚያገኙበት ሥራዎትም ከእኔ ጋር ይሞታል፡፡ እንደ አንድ ቄስነትዎ የሰይጣን መኖር በራሱ የእኔን ጠላት ቤተ-ክርስቲያንን እንደፈጠረ አያውቁምን? ከአማኞች ኪስ ውስጥ የወርቅና የብር ሳንቲሞችን እያወጣ በናንተ በሰባኪዎች እና በወንጌላዊያን ኪስ ውስጥ የሚጨምረው ምስጢራዊ እጅ ይሄ ከጥንት ጀምሮ የነበረው ግጭታችን መሆኑን አያውቁምን?

በርግጠኝነት ክብርዎትን፣ ቤተ-ክርስቲያንዎትን ቤትዎትንና እንጀራዎትን እንደሚያሳጣዎ እያወቁ እንዴት እኔን በዚህ ቦታ እንድሞት ትተውኝ ይሄዳሉ?››

ከድርሰቱ የተቀነጨበ

@zephilosophy
ይቅርታህን እንካ፣ ይቅርታህን አምጣ!!

ሜርቭ ከተማ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የኻያምን በከተማው መገኘት የተቃወመው ዋና ቃዲ ተነሳና፣ ጣቱን ቀስሮ፣

በእግዚአብሔር የማያምን ፈላስፋ፣ ስለሃይማኖት ጥያቄ አስተያየት መሰንዘር የሚገባው አይመስለኝም» አለ፡፡

ዑመር የመታከት ፈገግታ አሳየውና፣

በእግዚአብሔር የማያምን ብለህ እንድትኮንነኝ ማ መብት ሠጠህ? የተናገርኩትን ካዳመጥህ በኋላ እንኳን ቢሆን ባማረብህ፡፡»

«የምትለውን መስማት አያሻኝም!» በኃይለ ቃል ተቃወመው:: «ይኽን ግጥም የተቀኘኸው አንተ አይደለህም ? ፦

ሠራህና አዳምን ከተልካሻ ጭቃ፣
አቆምህና እባብን ለሄዋን ጠበቃ፣
አንተ ባጠፋኸው እሱን ልትቀጣ?
ይልቅ፣ ይቅርታህን እንካ፣ ይቅርታህን አምጣ! -

እንዲህ ያሉ ቃላትን የሚሰነዝር ባለቅኔ ከሀዲ እንጅ አማኝ ይባላል?»

ዑመር ራሱን ነቀነቀ።
«ባላምንበት እኮ፣ እግዜር መኖሩን ባላቅ እኮ፣ አላናግረውም፡፡»

«ታዲያ እንደዚህ እየዘረጠጥክ ነው የምታናግረው ?» ቃዲው አፈጠጠበት።

«ለናንተ ቃዲዎችና፣ ለሡልጣኖች ነው የሽቁጥቁጥ ቋንቋ የሚያስፈልገው። ለፈጣሪ አይደለም። አላህ ታላቅ ነው! እንደሰው ይሉኝታና ግብዝነት የለበትም። ማሰብ እንድችል አርጎ ነው የፈጠረኝ። ስለዚህም አስባለሁ፡፡ የሀሳቤንም ፍሬ ነገር ሳላሞካሽ አቀርብለታለሁ።

የተሰበስበው ሁሉ በአድናቆት አጉረመረመ። ቃዲው ተቆናጥሮ ተነሳና፣ በሆዱ እየዛተ ምንም ሳይናገር ተቀመጠ፡፡ ልዑሉ ከልቡ ፈንድቆ ከሳቀ በኋላ የሃይማኖት ሰዎችን ደሞ እንዳያስቀይም ሰጋ። ወዲያው ገፁን አኮሳትሮ ፀጥ አለ። ሊቃውንቱ ነገሩ አለማማሩን ሲመለከቱ፣ አንድ ባንድ እጅ እየነሱ ወጡ፡፡
__
መፅሀፍ- ዑመር ኻያም ልበወለዳዊ የሕይወት ታሪኩና ሩብአያቶች
ትርጉም ፦ በተስፋዬ ገሠሠ
ገጽ 138/139

@zephilosophy
"መልካም ምግባሩን እንደ ክት ልብሱ የሚለብስ እሱ ዕርቃኑን ቢሆን ይሻለዋል"
ካህሊል ጂብራን

አንድ በዕድሜ የገፋ ካህንም አሉ
‹‹ስለ ሃይማኖት ንገረን?››

እሱም አለ፡-
‹‹በዚህ ቀን ስለ ሌላ ነገር ተናግሬያለሁን? ሀይማኖት ሁሉንም ተግባራት እና ሁሉንም ዕቅዶች አይደለምን?...

‹‹ደግሞስ ተግባር እና ፅድቅ ያልሆነ፤ ነገር ግን እጆች ድንጋይ ሲጠርቡ ወይም ማዳወሪያውን ሲጨብጡ- ያ ዘወትር ከነፋስ ውስጥ የሚመነጨው ነገር አስገራሚና አስደንጋጭ አይደለምን?...

‹‹እምነቱን ከተግባሮቹ ወይም እምነቱን ከሙያዎቹ ሊነጥል የሚቻለው ማን ነው?...
ይህ ለእግዚአብሔር፣ ይህ ደግሞ ለእኔ ለራሴ፤ ይህ ለነፍሴ፣ ይህ ደግሞ ለስጋዬ›› እያለ እምነቱን ከፊት ለፊቱ ሊነጣጥለው የሚቻለውስ ማን ነው?...

‹‹መልካም ምግባሩን እንደ ክት ልብሱ የሚለብስ እሱ እርቃኑን ቢሆን ይሻለዋል፡፡ ነፍስና ፀሐይ በቆዳው ላይ ቀዳዳዎችን አይቀዱምና...

‹‹ባህርዩንም በሥነ-ምግባር ትምህርት የሚወስን እሱ የምትዘምር ነፍሱን በሽቦ አጥር ውስጥ አስሯታል፡፡ በሽቦዎች እና በብረቶች በኩል ደግሞ ነፃ ዝማሬ አይመጣም

"ማምለክን ሲፈልጉት የሚዘጋ፣ ሲፈልጉትም የሚከፈት- መስኮት አድርጎ የሚያይ እሱ ገና መስኮቶቹ ከዳር እስከ ዳር የሚያደርሱትን የነፋሱን ቤት አልጎበኝም፡፡

‹‹የዕለት ተዕለት ህይወታችሁ ቤተ መቅደሳችሁ እና ሀይማታችሁ ነው:: ወደ ውስጥ በዘለቃችሁ ቁጥርም ሁሉን ነገራችሁን ይዛችሁ ግቡ፡፡

ማረሻችሁን፣ ብረት ማቅለጫችሁን፡ መዶሻችሁንና ክራራችሁንም ጭምር ያዙ፡፡ አስፈላጊ በመሆናቸው እና ደስ እንዲያሰኟችሁ የሰራችሁዋቸውን ነገሮች በሙሉም ወደዚያ ውሰዱ

‹‹በቀን የሃሳብ ህልማችሁ ውስጥ ከከፍተኛ ስኬታችሁ በላይ ከፍ ልትሉም ሆነ ከውድቀታችሁ በበለጠ ዝቅ ብላችሁ ልትወድቁ ትችላችሁን? እናም ሁሉንም ሰዎች ከእናንተ ጋር ውሰዱዋቸው፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ተስፋ ካደረጉት በላይ ከፍ ብላችሁ ልትበሩ ወይም ተስፋ ከቆረጡባቸው በታች ዝቅ ብላችሁ ራሳችሁን ትሁት ልታደርጉ አትችሉምና

‹‹እግዚአብሔርን ማወቅ ከፈለጋችሁ እንግዲያውስ የምስጢራት ፈቺ (ተርጓሚ) አትሁኑ፡፡ ከዚያ ይልቅ በዙሪያችሁ ስትመለከቱ ምስጢሩን ከልጆቻችሁ ጋር ሲጫወት ታዩታላችሁ....

‹‹ወደ ህዋም ተመልከቱ፡፡ በደመናው ውስጥ ሲራመድ በመብረቁ ውስጥ እጆቹን ሲዘረጋ እና ዝናብ ሆኖ ሲወርድ ታዩታላችሁ...
ሲነሳ እና በዛፎቹ ውስጥ ሆኖ እጆቹን ሲያውለበልብላችሁ ታዩታላችሁ።

@zephilosophy
"በምሽት የምትዘምር ወፍ የሌሊቱን ፀጥታ ቅር ታሰኛለችን? የምታበራ ትልስ ብትሆን በብርሃኗ ክዋክብትን ቅር ታሰኛለችን?"
ካህሊል ጂብራን

ከዚያም ከተማውን በየአመቱ አንድ ጊዜ እየመጣ የሚጎበኝ ባህታዊ ወደ ፊት መጣ:: አለውም፡-
‹‹ስለ ደስታ ንገረን?››

እሱም መለሰለት ደስታ የነፃነት መዝሙር ነው፤ይሁንና በራሱ ነፃነት አይደለም፡፡

‹‹የጽኑ ምኞቶቻችሁ ማበብ (መፍካት) ነው፡፡ ግን ደግሞ የፈኩት (ያበቡት) ምኞቶቻችሁ ፍሬ አይደለም..
‹‹ወደ ከፍታ የሚጣራ ጥልቀትም ነው ደስታ:: ይሁንና ጥልቀቱንም ሆነ ከፍታውን አይደለም..
‹‹በፍርግርግ ብረት በተሰራ ጎጆ ውስጥ የተያዘ እና የሚዘረጋ ክንፍም ነው፡፡ ነገር ግን የታጠረ ስፍራ አይደለም...

‹‹አዎን! በእውነቱ ደስታ የነፃነት መዝሙር ነው፡፡በልበ ሙሉነት እንድትዘምሩት እመኝላችኋለሁ፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን በመዘመር ልቦቻችሁን እንድታጡ አልመኝም....

‹‹ከወጣቶቻችሁ አንዳንዶቹ ደስታን ሁሉን ነገር እንደሆነ አድርገው በመቁጠር በብርቱ ያስሱታል፡፡ በዚህም ይወቀሳሉ፤ ይኮነናሉ፡፡ እኔ ግን አልፈርድባቸውም።፡ አልገስፃቸውምም። የበለጠ እንዲፈልጉት አደርጋቸዋለሁ እንጂ...
‹‹እነሱም ደስታን ያገኙዋታል፡፡ የሚያገኙዋት ግን ብቻዋን አይደለም፡፡ ሰባት እህቶች አሉዋትና:: ከሁሉም በዕድሜ ትንሿ ከደስታ ከራሱ እንኳን በጣም ውብ ነች...

"ስሮችን ለማግኘት ብሎ መሬትን ሲቆፍር የተደበቀ ሀብት ስላገኘው ሰው አልሰማችሁምን?...

"ከአዛውንቶች ጥቂቶቹ በደስታ ያሳለፉዋቸውን ጊዜያት በመጠጥ ስካር እንደፈፀሙዋቸው ስህተቶች በማሰብ ደስታዎቻቸውን በፀፀት ያስታውሷቸዋል፡፡ ይሁንና ፀፀት የአዕምሮ ማጨለሚያ እንጂ ቅጣቱ ራሱ አይደለም...
‹‹በመሆኑም የበጋውን መኸር እንደሚሰበስቡ ሁሉ የደስታ ጊዜያቶቻቸውንም ውለታ በማመስገን ማስታወስ ይገባቸዋል...
‹‹እንደዚያም ሆኖ መፀፀት መጽናናትን የሚሰጣቸው ከሆነ ይፅናኑ ተዋቸው...

‹‹ደግሞም በመካከላችሁ ደስታን ለመፈለግ እጅግ ወጣት የሆኑና ለማስታወስም ዕድሜያቸው የገፋባቸው አሉ፡፡ መንፈሱን እንዳይንቁ ወይም እንዳይበድሉ ሲያስቡ በሚያድርባቸው ኃይለኛ ፍርሃት የተነሳ ደስታን ለመፈለግም ሆነ ለማስታወስ አይሹም፡፡ የደስታ ጊዜያትንም በሙሉ ይሸሻሉ።

‹‹ ይሁንና ከዚያ በፊት ባሳለፉት ህይወታቸው ውስጥ ደስታቸው አለ፡፡ ደግሞም እነሱም ቢሆኑ በሚንቀጠቀጡ እጆቻቸው ስሮቹን ለማግኘት መሬትን ቢቆፍሩ የተደበቀ ሀብትን ያገኛሉ፡፡

‹‹የሆነስ ሆነና ንገሩን እስኪ?! ማን ነው እሱ መንፈሱን ቅር ሊያሰኝ የሚችል?....
‹‹በምሽት የምትዘምር ወፍ የሌሊቱን ፀጥታ ቅር ታሰኛለችን? የምታበራ ትልስ ብትሆን በብርሃኗ ከዋክብቱን ቅር ታሰኛለችን?...

‹‹ደግሞስ የምታነዱት እሳት ነበልባል ወይም ጢስ ለነፋስ ሽክም ይሆንባታልን?.... መንፈሱንስ ልክ በዘንግ ልታውኩት እንደምትችሉ የረጋ የገንዳ ውኃ ይመስላችኋልን?...

‹‹አብዛኛውን ጊዜ ለራሳችሁ ደስታን በመንፈጋችሁ በስብዕናችሁ ጓዳዎች ውስጥ ታከማቻላችሁ እንጂ ሌላ ምንም ነገር  አታደርጉም....

‹‹ዛሬ የተረሳ የመሰለን ነገን ይጠብቅ እንደሆነስ ማን ያውቃል?..
‹ አካላችሁም እንኳን ቢሆን ውርሱን እና ህጋዊ ፍላጎቱን ያውቃልና አይታለልም፡፡ አካላችሁ የነፍሳችሁ ክራር ነውና...

‹‹እናም ከውስጡ ጣፋጭ ጣዕመ ዜማን ወይም አዋኪ ድምፆችን ይዞ እንዲወጣ ማድረግ የእናንተ ፋንታ ነው....
‹‹አሁን እንግዲህ በልባችሁ በደስታ ውስጥ መልካም የሆነውን መልካም ካልሆነ እንዴት እንለያለን?› ብላችሁ ጠይቁ...

‹‹ወደ እርሻ መሬታችሁ እና ወደ አትክልት ስፍራችሁ ሂዱ፡፡ እዚያ ከአበቦች ማር መሰብሰብ ለንብ ደስታን እንደሚሰጣት ትማራላችሁ፡፡ አበባውም ቢሆን ለንቧ ማሩን በመስጠቱ ደስታን እንደሚያገኝ አስታውሱ...
‹ለንቧ አበባ የህይወት ምንጯ ነው፡፡ ለአበባው ደግሞ ንቧ የፍቅር መልዕክተኛው ነች...
‹‹እናም ለንቧም ሆነ ለአበባው ደስታን መስጠትና መቀበል መሰረታዊ ፍላጎትና እና ታላቅ ትፍስህት ነው..
<<የኦርፋሌስ ህዝቦች ሆይ! እንደ አበቦቹ እና ንቦቹ ሁሉ ደስ በሚሉዋችሁ ተግባራት ውሰጥ ደስ እየተሰኛችሁ ኑሩ፡፡>>

መፅሀፍ -የጥበብ መንገድ
ደራሲ -ካህሊል ጂብራን

@zephilosophy
የኢትዮጵያ ሕዝብ ግንባሩ አንድ በሆነና...
*
የአንዳንድ ሰው ዕጣ ያሳዝናል፡፡ በቅርቡ ‹ለከበደ ሚካኤል ጎረቤታቸው ነበርኩ፤ የሚገንዛቸው ጠፍቶ እኔ ነኝ የገነዝኳቸው› ካለኝ ጨርቁን የጣለ ዱርዬ ጋር እያወራሁ ነበር፡፡ ከበደ ሚካኤል በንጉሡ ዘመን እንደ ተርቲመኛ ቤተመንግስት የሚመላለሱ፣ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሽልማት ድርጀት የሥነፅሁፍ ተሸላሚ በብዙዎች የሚደነቁ ነበሩ፡፡ ደርግ መጣና ቤታቸውን ወርሶ አጎሳቆላቸው፡፡ 17 ዓመቷን ሙሉ የወዳጅ ሆቴል ክፍል ተጠግተው ተወጧት፡፡ ኢህአዴግ ሲገባ ቤታቸውን ቢመልስም ዝናቸው ግን እየደበዘዘ ሄደ፡፡ ከበደ ዘመን መቀየሩን፣ የፊውዳል ሕብረተሰብ በአንድ አዳር መጤውን አውሮፓዊ ቴክኖሎጂ ሰራሽ ‹ፖፕ ከልቸር› መላበስ መቋመጡን ያወቁት አይመስልም፡፡ እና አንድ ቀን አንድ ወዳጃቸውን ጠየቁ...
"ከተማው ስለኛ ምን ያወራል?"
"ምንም አያወራም፡፡ እረስቶዎታል።" ቢላቸው...
ከበደ በቁጭት
"ምናለ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግንባሩ አንድ በሆነና በፈነከትኩት" አሉ ይባላል፡፡ (ግንባሩ አንድ በሆነ - የእርሳቸው ቃል ለአደባባይ ጸያፍ ብትሆንብኝ መንፈሱን በከፊል ለመግለጽ የተካኋት ናት፡፡)

የኢትዮጵያ ሕዝብ ‹ሾርት ሜሞሪ› መሆኑን የሚያውቀው አብይ አህመድ ብቻ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዚያ ተማሪ በጎች መሆኑን ምናውቀው ግን እኔና እግዜር ብቻ ሳንሆን አንቀርም፡፡ ከበደ ሚካኤልም አያውቁ ይሆናል፡፡
በአንድ የገጠር ትምህርት ቤት የሚያስተምር የሒሳብ መምህር አንድ ቀን ከተማሪዎቹ መካከል በትርፍ ጊዜው በጎችን የሚያግድ ታዳጊ ልጅ ቀርቦ ጠየቀ፡፡ 

‹‹ልጅ በበጎችህ ማደሪያ ውስጥ አስር በጎች አሉህ እንበል፡፡ ከአስሩ በጎችህ አምስቱ ከማደሪያቸው ዘለው ቢወጡ በበጎቹ በረት ምን ያህል በጎች ይቀራሉ?››

‹‹ምንም!››
መምህሩ ተገርሞ ‹‹ያልኩህ አልገባህም፡፡ አስር በጎች አሉህ፡፡ አምስቱ ከበረቱ ዘለው ቢወጡ በበረቱ ውስጥ ስንት በጎች ይቀራሉ?››

‹‹ምንም!›› አሁንም ተማሪው ተመሳሳዩን መልስ ሰጠ፡፡
መምህሩ በብስጭት ‹‹እንዴት ይሄን መቀነስ ያቅትሃል?››
ተማሪው ሲመልስ
‹‹መምህር ሂሳቡን መቀነሱን አንተ ልታውቅበት ትችላለህ፡፡ የበጎቼን ጸባይ የማውቀው ግን እኔ ነኝ፡፡ እንኳን አምስቱ አንዲቷን ብቻዋን ዘላ ከወጣች ሁሉም ይከተሏታል እንጂ ሞት ቢመጣ በረት ውስጥ አይቀሩም፡፡››

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዚህ ተማሪ በጎች ይመስለኛል፡፡  አስርሺዎችን ማሳመኑ ከሆነልህ ሚሊዮኑ ያንተ ነው፡፡ ሚሊዮኑ አዝማሚያውን አይቶ ነገር ወደቀናው ተጠግቶ ለማደር ተሰልፎ የሚጠብቅ ‹ቁጥር› ነዋ፡፡ አንዳንዱ የሚያደንቅህ በስማ በለው ነው፡፡ እንጂ የነፍስ መቃተት ሀቀኝነት ተሰምቶት አይደለም፡፡ በሌላ ቀን እንዲሁ ፌቡ ላይ የአሉ ወሬ ለቃቅሞ ጥንብ እርኩስህን ያወጣዋል፡፡ የላመ የጣመ በማንኪያ መዋጥ የለመደ አዕምሮ መጠየቅ አይወድማ፡፡ የተማረው ያልተማረው፣ የሚያነበው የማያነበው... ብዙው ቀለም የሌለው ስርዝ ድልዝ ነገር አለው፡፡ እውነት ይፈውሳል አይደል? ስለምን ይሸፋፈናል? እውነት ምኑ ይቀባባል?

እኔ ግን ሀገርን፣ ትውልድን፣ ዘመንንና ግለሰብን እንደምን ታውቀዋለህ? እንደምንስ ትመዝነዋለህ ብትለኝ በጀግኖቹ እልሃለሁ፡፡ የዚህን ዘመን፣ የዚህን ትውልድ ጀግኖች ብንጠይቅ ስንት አምታታው ማኛ አክቲቪስት፣ ጯሂ ታዛቢ ነኝ ባይ፣ ዩቱበር፣ ቲክቶከር ይጠራልን ይሆን? ለመሆኑ አንድን ሰው የምናደንቀው ሰውየው የሚደነቅ ስለሆነ ወይስ ሌሎች ስላደነቁት?

ጥቂት ቀልብ ገዝቻለሁ በሚለው ወገን ስንኳ የአስተሳሰብ ዝንፈት ሥር ሰዶ አንዳንድ pseudo intellectuals የትውልዱን ሁሉ ዳፋ ተሸክመው የሚሻግሩ ተደርገው ሲንቆንጳጰሱ ትመለከታለህ፡፡ ብዙው ነገር እንደተንጋደደ ግልጽ ነው፡፡ 

የትኛውንም ኅብረተሰብ ንቃት ለመመዘን ወንዞቹን አትዩ፡፡ መንገዶች፣ ግድቦች፣ አደባባዮች፣ ድልድዮችም... በችሮታ ሲገነቡ አይተናል፡፡  ይልቁንስ የየትኛውንም ኅብረተሰብ የንቃት ደረጃ የሚበየነው አሰላሳዮቹን (thinkers) የሚይዝበት መንገድ ነው፡፡ ኅብረተሰብ አሰላሳዮቹን በሚይዝበት አኳኋን በዚያ የየንቃት ደረጃው (collective consciousness) ይመዝናል፡፡ ማኅበረሰብ አሰላሳዮቹን በሚይዝበት መንገድ የወደፊት ዕጣው - የባርነት ወይስ የአርነት - የሚለውን መገምገም ቀላል ነው፡፡

ከያዕቆብ ብርሃኑ የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ

@zephilosophy
የዮጋ ንፅህና

ምንጭ ፦የጣፋጭ ህይወት ሳይንሳዊ ጥበብ(ኦሾ)
ትርጉም ፦ አስክንድር

በእርግጥ ይህ ነገር እንግዳና አመክኗዊ ያልሆነ (illogical) ይመስላል፡፡ ይሁንና ተፈጥሮ ራሷ እንግዳና አመክኗዊ ናት፡፡ ለምሳሌ ሰማዩ ወሰን የሌለውና ሊደረስበት የማይችል (infinite) ቢሆንም፣ ነፀብራቁን ግን በአንዲት ትንሽዬ ኩሬ ውስጥ እናስተውለዋለን። በእርግጥ ሙሉ በሙሉ በዚች ትንሽዬ ኩሬ አሊያም በፊት መስተዋት ላይ አይንፀባረቅም፡፡ ይሁንና በራሷ ሙሉ የሆነችው የተወሰነችዋ ክፍልም የአጠቃላዩ አካል ናት፡፡

የሰው ልጅ አእምሮም ልክ እንደ ፊት መስተዋት ነው፡፡ ንፁህ ከሆነ፣ ይህ የማይደረስበት ወይም ወሰን የሌለው (infinite) ያልነው ነገር እላዩ ላይ ይንፀባረቅበታል፡፡ በእርግጥ ይህ ነፀብራቅ ግን ወሰን የሌለው (infinite) አይሆንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የሱ አካል ወይም የሱ ክፋይ ይሆናል፡፡

የዚህ ወሰን የሌለው (infinite) ክስተት አካል የሆነው ክፍል ከአጠቃላዩ ጋር እኩል ነው፡፡ ምክንያቱም ይህን ወሰን የሌለውን ነገር መከፋፈል አንችልም። ክፍልፋይ ናቸው ብለን የምናስባቸው ነገሮች በሙሉ ስህተት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ህንድ ውስጥ ያለውን ሰማይ የህንድ ሰማይ፣ እንግሊዝ ውስጥ ያለውን ደግሞ የእንግሊዝ እያልን ልንከፋፍል አንችልም፡፡ ሰማይ የትም አይጀመርም፤ የትም ደግሞ አያልቅም፡፡

አእምሮአችሁንም በተመለከተ የሆነው ነገር የዚህ ተመሳሳይ ነው፡፡ 'አእምሮአችሁ' የሚለው ራሱ ስህተት ነው፡፡ አእምሮም ሆነ ነፍስ የማይደርስበትና ወሰን የሌለው (infinite) ያልነው አካል ናቸው፡፡ ውስን (finite) መስለው መታየታቸው ግን እውነት ሳይሆን ቅዠት ነው፡፡ ይህ የሆነው ራሳችንን እንደዛ አድርገን ስለምናስብ ብቻ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ደግሞ የምናስበውን ነገር ነው የምንሆነው፡፡ ቡድሀም “የምታስቡትን ሁሉ ትሆናላችሁ" እያለ ለረጅም አመታት እየደጋገመ ያስተምር ነበር፡፡ እናም ይህን በራሳችሁ ላይ ያስቀመጣችሁትን ውስንነትና ገደብ ጥሳችሁ በማለፍ ወሰን የለሽ (infinite) ለመሆን ጣሩ፡፡

ዮጋ በአጠቃላይ የሚያስተምረንም ይህን ወሰን፣ ይህን ገደብ እንዴት አልፈን መሄድ እንደምንችል ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ገደብ ወይም ወሰን እኛው እራሳችን የፈጠርነው እንጂ በእርግጥ ያለ አይደለም፤ ዝም ብሎ ሃሳብ ነው። ለዚህም ነው በአእምሮአችን ሃሳብ ከሌለ፣ ወሰን ወይም ገደብ የለሽ የምንሆነው፡፡ ይህ ሲሆን ታዲያ መለኮታዊ ሃይል ወደ እኛ ይወርዳል፡፡ ማሰብ ሰው ሲያደርግ፣ ከማሰብ በላይ ደግሞ መለኮታዊ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በታች ግን እንሰሳ ያደርጋል።

በአጠቃላይ ሃሳብ የሌለበትን ሁኔታ (non-thought) ለጥቂት ጊዜያት እንኳን ማሳካት ከቻልን፣ ያበጀነው ወሰንና ገደብ ሲናድ ማስተዋል እንጀምራለን፡፡ ለዚህም ነው የዮጋውን ሊቅ ፓታንጃሊን ሳይንሳዊ ነው የምንለው፡፡ ምንም አይነት ሃይማኖትም ሆነ እምነት አይጠይቀንም፡፡ ሙከራውን ለመስራት ጥረት እንዲኖረን ብቻ ነው የሚጠይቀን፡፡ መንገዶቹም የተጠላለፉና የተጠማዘዙ ሳይሆኑ አጭርና ግልጽ ናቸው፡፡ እናም እያንዳንዷን ዝርዝር በጥንቃቄ መከተል ይገባቸኋል። ከመስመሩ ከወጣችሁ ግን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ልትጓዙ ትችላላችሁ።

ፓታንጃሊ ከሳይንሳዊነቱ ባሻገርም ተጠየቃዊ (logical) አካሄድን የሚከተል ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የሚጀመረው አጠቃላይ ከሰውነታችን ነው፡፡ ከዛም የህይወታችን ሁለተኛው ደረጃ (layer) ወደ ሆነው የአተነፋፈስ ስርአት (breathing) ይሻገራል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ሃሳቦቻችን (thoughts) ይመለከታል፡፡ ይህ ሳይንሳዊ ዘዴ በቅድሚያ መጀመር ያለበት ከሰውነታችን ነው፡፡ ሰውነታችን ሲቀየር የአተነፋፈስ ስርዓታችን ይቀየራል፡፡ የአተነፋፈስ ስርዓታችን ደግሞ ሲቀየር አስተሳሰባችን ይቀየራል፡፡ አስተሳሰባችን ሲቀየር ደግሞ እኛ እንቀየራለን።

የቲቤት ነዋሪዎች ከተናደድክ ሩጥ ይላሉ፡፡ የግቢህን ዙሪያ ሁለቴ በሶምሶማ ሩጥ፡፡ ከዚህ በኋላ ንዴትህ የት እንደገባ ለራስህም ይገርምሃል፡፡ ይህ የሚሆነው ስንሮጥ የአተነፋፈስ ስርዓታችን ስለሚቀየር ነው፡፡ የአተነፋፈስ ስርዓታችን ሲቀየር ደግሞ የአስተሳሰባችን ሁኔታም እንደ ነበረው አይሆንም ይቀየራል፡፡

በእርግጥ መሮጡ የግድ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡ ዝም ብለን አንድ አምስት ጊዜ ያክል በጥልቀት ተንፍሰን ...አየር ወደ ውስጥ አስገብተንና ወደ ውጭ አስወጥተን ንዴታችን የት እንደ ሄደ ማየት እንችላላለን፡፡ ንዴታችንን በቀጥታ ማስወገድ ይከብደናል፡፡ ነገር ግን ስሜታችን፣ አካላዊ ሁኔታችንን መቀየር፣ ከዛም በመጨረሻም ንዴታችን ይቀየራል፡፡ ይህ ሳይንሳዊ ሂደትን የተከተለ ነው፡፡ ለዚህም ነው ፓታንጃሊ ሳይንሳዊ ነው የምለው፡፡

ወደ ቡድሃ ዘንድ ብትሄድ ግን ‹‹ንዴትህን ወዲያ ጣለው!›› ነው የሚልህ። ፓታንጃሊ ግን ይህን አይልም፣ በቀላሉ ነው የሚያስረዳህ፡፡ ተናደድክ ማለት ለዚህ ንዴትህ አመቺ የሆነ የአተነፋፈስ ስርዓት አለህ፡፡ እናም ይህን የአተነፋፈስ ስርዓት እስካልወጥክ ድረስ፣ ንዴትህ አያባራም ይልሃል፡፡ በእርግጥ በሌላ በራሳችን መንገድ ታግለን ንዴትን ልናሸንፈው እንችል ይሆናል፡፡ ያ ግን አድካሚና አላስፈላጊ መስዋትነት ነው፡፡

እዚህ ላይ ግዙፉ አካላችን ሲሆን ትንሹ ደግሞ አእምሮአችን ነው፡፡ ስለዚህ ከትንሹና ከረቂቁ ከመጀመር ከአጠቃላይ ከአካላችን መጀመሩ የተሻለ ነው በሚል ነው፡፡ ለመጨበጡ የሚረዳውም ይኸው በመሆኑ ፓታንጃሊም ከሰውነት አቋም (posture) ይጀምራል፡፡

በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ብዙም ባናስተውለው አእምሮአችን አንድ የተለየ ባህሪ እያሳየ ከሆነ፣ ሰውነታችን በበኩሉ ከዚህ ባህሪ ጋር ተያያዥ የሆነ ሁኔታ (posture) ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ከተናደደ፣ ዘና ብሎና ተረጋግቶ አይቀመጥም፡፡ ከንዴት ባህሪው ጋር የሚሄድ የፊት መለዋወጥ፣ የደም ስር መገታተር ወዘተ ባህርያትን ያሳያል፡፡

በአንፃሩ አንድ ሰው በፀጥታ ከተቀመጠ፣ የሰውነቱ አቋምና የጡንቻዎቹ ባህሪ የተለየ ነው የሚሆነው፡፡ ለምሳሌ ሙሉ በሙሉ ፀጥ ካልክ፣ እንደ ቡድሃ በአርምሞ ትቀመጣለህ፣ አሊያም በዝግታ ትጓዛለህ፡፡ ይህን ስታደርግም ደስ የሚል ፀጥታ ወደ ልብህ ሲገባ ይሰማሃል፡፡ ወይም ደግሞ እንደ ቡድሃ በአንድ ዛፍ ስር አረፍ በልና በፀጥታ ተቀመጥ። የአተነፋፈስ ስርዓትህ ሲቀየር ይሰማሃል፡፡ የተረጋጋና ሰላማዊ አተነፋፈስ፡፡ አተነፋፈስህ ደግሞ የተረጋጋና ሰላማዊ ሲሆን፣ አእምሮህ ፈታ ዘና ማለት ይጀምራል፡፡ ጭንቀትና ሃሳብ ጥለውህ ሄደው ደስ የሚል ፀጥታ ወደ ሰውነትህ ሲገባና ሲወጣ ይሰማሃል።

በመሆኑም ፓታንጃሊ ሳይንሳዊ ነው። ከዚህም አልፎ ፓታንጃሊ የሰውነታችንን ሁኔታ (posture) ለመለወጥ ከፈለግን፣ አመጋገባችንን እንድንቀይር ይመክረናል፡፡ ለምሳሌ ስጋ ተመጋቢዎች ከሆናችሁ፣ እንደ ቡድሃ ልትቀመጡ አትችሉም ይለናል፡፡ በአንፃሩ አትክልት ተመጋቢዎች ከሆንም፣ አንደዛው የተለየ የሰውነት ሁኔታ ይኖረናል። ወደ ሰውነታችን የሚገባ ነገር ሁሉ በአካላችንና በባህሪያችን ላይ ይንፀባረቃልና፡፡

@zephilosophy
@zephilosophy
Is Yoga a Religion?

Yoga is not a religion. It is an old discipline from India. It is both spiritual and physical. Yoga uses breathing techniques, exercise and meditation. It helps to improve health and happiness. Yoga is the Sanskrit word for union. Patanjali was a pioneer of classical yoga ,who wrote the Yoga Sutra. He defined yoga as "the cessation of the modification of the mind" .

These scriptures provide a framework for spiritual growth and mastery over the physical and mental body. Yoga sometimes interweaves other philosophies such as Hinduism or Buddhism, but it is not necessary to study those paths in order to practice or study yoga.

It is also not necessary to surrender your own religious beliefs to practice yoga.

@zephilosophy
የአብዮት አያቶች
ደራሲ- ስብሃት ገብረእግዚኣብሄር

አብዮት <<አበየ>> (እምቢ አለ) ከሚለው የግእዝ ግስ የተወሰደ ነው፡፡ አብዮት ሁለት ክፍል አለው፣

 ክፍል አንድ፦ ቁዋሚ ሆኖ የቆየውን ስርዓት <<እምቢዮ>> በዚህ ስርዓት አልተዳደርም ይሉና ያንን ስርዓት ያፈርሱታል።

 ክፍል ሁለት፦  ያንን የፈረሰውን ስርዓት የሚተካ አዲስ ስርዓት ይዘረጋሉ።

እንደምንሰማው በሰማየ ሰማያት ከሊቃነ መላዕክት ሁሉ በላይ የነበረው ሳጥናኤል የመጀመሪያ አብዮታዊ ነው።

ግን የአብዮትን አንዱን ግማሽ ማለትም እምቢታቸውን ብቻ እንደፈፀመ እነ ቅዱስ ሚካኤል በጦር ድል ስለመቱት ተይዞ ከሰማየ ሰማያት ተወረወረ፤ ሰባት ቀን ከሰባት ሌሊት ሙሉ ሲወድቅ ሰንብቶ ሲኦል ውስጥ በእሳት ሰንሰለት ታስረ።

ከሼክስፒር ቀጥሎ ታላቁ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ገጣሚ ብለው እንግሊዞች የሚኮሩበት ጆን ሚልተን <<ገነት ጠፍታ>> በተባለው ዝነኛ ድርሰቱ፤ ሳጥናኤልን በሲኦል እንዲህ ያሰኘዋል፤
<<በመንግስተ ሰማያት ከማገልገል በገሀነም መንገስ ይሻላል።» አብዮታውያን ቢሸነፉም <<ወይኔ! ምነው እምቢታው በቀረብኝ ኖሮ!>> አይሉም፤ <<እንደገና እድል ቢገጥመኝ እንደገና እዋጋለሁ።» ይላሉ እንጂ።

በመጀመሪያው የአብዮት ግማሽ ማለትም የቆየውን ስርዓት እምቢ በማለቱ አብዮታውያን ሁሉ ይመሳሰላሉ። የሚለያዩት በሁለተኛው ክፍል ነው፡፡ አንዳንዶቹ ከዚያ ካፈረሱት ስርዓት የተሻለ አዲስ ስርዓት በመዘርጋታቸው በህዝባቸው ይወደዳሉ፤ ላገራቸው አንዳንዴም ለሰው ልጆች ሁሉ የሚበጅ ስራ ሰርተው ያልፋሉ።በዚህ ፅሁፋችን የምንጠቅሰው ጥሩውን አብዮት የፈፀሙትን ጀግኖች ብቻ ይሆናል። እነዚህን አብዮታውያን <<ጥንታውያን አብዮታውያን>> እና <<ዘመናውያን አብዮታውያን>> ብለን በሁለት እንከፍላቸዋለን።

  ጥንታውያኑ አብዮታውያን አብዛኛዎቹ የተነሱት በአምላካቸው ስም እና ስለ ሃይማኖትና ግብረገብ መሻሻል ጉዳይ ሲሆን፣ እነሱም መምህራን ነበሩ። ዘመናዊያኑ ግን የሚነሱት በህብረተሰቡ ስም እና ስለ ኢኰኖሚ አቋም እንደዚሁም ስለ መንግስታዊ አስተዳደር መሻሻል ጉዳይ ሲሆን፣ እነሱም ደራሲያንና የፖለቲካ ሰዎች ናቸው፤ጥንታውያን አብዮታውያን የሚመሳሰሉበት አለ፤ አብዮታቸው ይወለዳል፤ ያድጋል፤ ያረጃል።

የአብዮት ልደት፦ አንድን አብዮታዊ የዘመኑ ግፍ ጭቆና እና ግብዝነት ያንገፈግፈዋል።
<<አይሆንም!>> ብሎ ይነሳል። የዘመኑ ሁናቴ የተስማማቸው ወገኖች ሊያጠፉት ይነሳሉ። ስደት፣ ጭንቀት አንዳንዴም ሞት ይደርስበታል። (ለምሳሌ ኢየሱስንና መሐመድን እናስታውስ)

የአብዮት እድገት፦ አብዮታዊው ቢሞትም ተከታዮቹ በሀሳቡ እየገፉበት ይሄዱና የዱሮው ስርዓት ይሸነፋል ፤ ይቀየራል። አዲስ የተሻላ ስርዓት ይዘረጋል። <<የተሻለ >>ስንል ጭቆና የተቀነሰበት፣ ፍትህ የበዛበት ማለታችን ነው።

የአብዮት ማርጀት፦ ታድያ የሚያሳዝነው ነገር፣ ያ የቀድሞው ስርዓት ይሰራው የነበረው ግፍ ቀስ እያለ ይመለሳል፤ ግን አሁን ግፉ የሚሰራው በዚያ በአብዮታዊው ስም ነው፡፡ ያንን ግፍና ጭቆና ለማስወገድ መከራ ያየው የተሰደደው የተገደለው ሰውዬ አሁን ስሙ ለዚያው አይነት ግፍና ጭቆና መፈፀሚያ መሳሪያ ይሆናል። ደሞ ሌላ አብዮታዊ ተነስቶ <<አይሆንም>> እስኪል ድረስ።

አንድን አብዮታዊ በትክክል ለመገመት፤ እሱ ሲወለድ ባገሩ የነበረው ስርዓት እንዴት ያለ ነበር? እሱ የዘረጋው አዲስ ስርዓትስ ከቀድሞው ስርዓት በምን የተለየ ነበር? ለሚሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ማግኘት ይኖርብናል።
አዲሱ ስርዓት ለሀገሩ ሰዎች ምን ጥቅም ሰጠ? በአዲሱ ስርዓት እየተመሩ ምን ምን የሚያስመሰግን ወይም የሚያኩራ ነገር ሰሩ? አዲሱ ስርዓት ከሀገሩ ድንበር አልፎ በጠቅላላው ለሰው ልጆች የሰጠው ጥቅም አለወይ? ለምሳሌ ምን ምን ጥቅም ሰጥቷል?

  የአብዮታውያንን ታሪክ ስንመለከት አንዱን ከሌላው ማነፃፀር ይጠቅማል፣ እገሌና እገሌ በዚህ በዚህ ሲመሳሰሉ በዚህ በዚህ ግን ይለያያሉ ብንል አንዳንድ ነጥብ ያብራራልን ይሆናል። ያለንበት ዘመን የአብዮት ዘመን በመሆኑ አብዮትን በይበልጥ ለማወቅ ሊረዳን ይችላል። ማወዳደር እገሌ ከእገሌ ይበልጣል ማለት ግን ጊዜ ከማጥፋት ሌላ ትርፍ የለውም።
ለምሳሌ ከሙሴና ከመሐመድ ማን ይበልጣል? የሚለው ጥያቄ ፍሬ ቢስ ነው። የኖሩበት ዘመን የተለያ፤ የኖሩበት አገር የተለያየ፤ የተነሱበት ጉዳይ የተለያየ፤ ታዲያ በምን ልናወዳድራቸው ነው?

1) አብዮት በእስራኤል ፦ ከሙሴ እስከ ኢየሱስ
ሀ/ሙሴ፦ የዛሬ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ዓመት ነገደ እስራኤል በግብፅ በባርነት ሲኖሩ፤ በፈርኦን ቤተመንግስት እንደ ልዑል ሆኖ ያደገው ሙሴ <<ሕዝቤን ልቀቅ>> ሲል ከፈርኦን ጋር ተሟገተ። ምድረ ግብፅ ላይ በተከታታይ አስር ልዩ ልዩ መአት አወረደ። በመጨረሻም የምድረ ግብፅን በሙሉ (የሰውንም የከብቱንም) የበህር ልጅ በአንድ ሌሊት ገደለ፡፡ ያን ጊዜ ፈርኦን ህዝበ እስራኤልን ለቀቃቸው። ከሄዱ በኋላ ግን ቆጨው። ፈርኦን ፈረሰኛውንና ባለሰረገላውን አስከትቶ ህዝበ እስራኤልን ሊይዛቸው ተከተላቸው፡፡ ቀይ ባህር አፋፍ ሲደርሱ ደረሰባቸው ሙሴ ቀይ ባህርን እንደ መጋረጃ ከፈተው፤ ህዝበ እስራኤል ተሻገሩ።የፈርኦን ሰራዊት ተከተለ የተከፈተው ባህር መሀል ላይ ሲደርስ ግን ሙሴ ባህሩን ወደ ጥንቱ ቦታው መለሰው፡፡ ፈርኦን ከነሰራዊቱ ተዋጠ። የሙሴ አብዮት የመጀመሪያው ክፍል በዚህ አለቀ፡፡

ሁለተኛው የአብዮቱ ክፍል አርባ ዓመት ሙሉ በሲና በረሃ መንከራተትን ይጠይቃል፡፡ አርባ አመት ሲያልቅ ግን ነገደ እስራኤል አስርቱ ቃላትን ተቀብለው ሲያበቁ - በስንት ጦርነት አገራቸው ገቡ። ዛሬም ከሶስት ሺ ሁለት መቶ አመት በኋላ እስራኤላውያን የሚኖሩት ሙሴ በሰጣቸው ስርዓት ነው፡፡

ክርስትና እና እስልምና ከሙሴ የሚቀበሉት ብዙ መሰረታዊ እምነት ስላለ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ቢያውቀውም ባያውቀውም በአስተሳሰብና በአኗኗር የሙሴ የልጅ ልጅ ልጅ.... ነው።

ይቀጥላል...

@zephilosophy
የአብዮት አያቶች
..የቀጠለ

ለ/ ኢየሱስ፦ ከላይ እንዳልነው አንድ ታላቅ አብዮት የቀድሞውን ጨቋኝ ስርዓት አፍርሶ የተሻለ አዲስ ስርዓት ዘርግቶ ካለፈ በኋላ፣ በጊዜ ብዛት ያ አዲስ ስርዓት ተራውን ያረጃል፤ ይበሰብሳል፡፡ አንዳንድ ወገኖች መጠቀሚያ ያደርጉታል። የሙሴን ስርዓትም ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን የተባሉ <<ምሁራን >> ወገኖች ስላበላሹት ኢየሱስ የተባለ መምህር ተነስቶ አዲስ ስርዓት አስተማረ፡፡ ኢየሱስ የፍቅርና የሰላም መምህር ነበረ፡፡ ሁለት ልብስ ያለው አንዱን ለሌላው ይስጥ፤እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ ፤ የሚጠሉዋችሁን ውደዱ ሲል አስተማረ። ሰንበት ለሰው ልጅ ተሰራ እንጂ የሰው ልጅ ለሰንበት አልተሰራም ሲልም የሰውን ልጅ ከፍተኛነት አወጀ፡፡ ለእምነቱ ተሰቀለ። በኢየሱስ ስም አዲስ ስርዓት ተዘረጋ። በእስራኤል ሳይሆን በውጭ አገር። ኢየሱስም ራሱ <<ነብይ በገዛ አገሩ አይከበርም>> ብሎ ነበርና።) ያ ኢየሱስ ያስተማረው ስርዓት ደሞ ተራውን ሲያረጅ፤ የፍቅርና የሰላም መምህር በሆነው በኢየሱስ ስም ጦርነት ማድረግ፤ በኢየሱስ ስም ሰውን በእሳት ማቃጠል መጣ።

2/ አብዮት በሀገረ ህንድ፦
ቡድሀ ከሁለት ሺ አምስት መቶ አመት በፊት ጋውታማ ቡድሀ ሲወለድ ጥንታዊው የሂንዱ ሃይማኖት አርጅቶ መንፈሱ ተረስቶ መልክና ባዶ ስርዓት ብቻ ሆኖ ቀርቶ ነበር። ለአማልክቱ መስዋዕትን ማቅረብ የሚችሉት ብራህሚን የተባሉት ቄሶች ብቻ በመሆናቸውና በራህሚንነትም በችሎታ ወይም በብቃት ሳይሆን በትውልድ የሚወረስ በመሆኑ፣ የሂንዱ ሃይማኖት የአንድ ወገን (መደብ) መጠቀሚያ ሆኖ ነበር። ልዑል ጋውታማ ቡድሀ ይህንን ባዶ የሃይማኖት ገለባ ወድያ አስወግዶ አዲስ ሃይማኖት አወጀ። መልዕክቱ ባጭሩ <<ደህንነትህ ባንተ በራስህ እጅ ነው- ራስህን ታድናለህ እንጂ ሰውም አያድንህ አማልክትም አያድንህ>> የሚል ነበር፡፡

ቡድሀና ኢየሱስ በብዙ ነገር ይመሳሰላሉ፡፡ በታሪክ ዓይን ስናያቸው የሚመሳሰሉበት አንዱ ነገር እነሱ የመሰረቱት ስርዓት አሁን በገዛ አገራቸው ብዙ ተቀባይ የለውም፤ በውጭ አገር ግን ብዙ ሚልዮናት ህዝብ ይከተላቸዋል።

3/ አብዮት በቻይና፣ ኮንፊሺየስ

ኮን ቹ አውሮፓውያን ኮንፉሽየስ እያሉ የሚጠሩት ከሁለት ሺ አምስት መቶ ዓመት በፊት የኖረ ቻይናዊ መምህር ነው፡፡ ኮን ከጥንታውያን አብዮታውያን እጅግ የተለየ ነው። ሌሎቹ በአምላክ ወይም በአማልክት ስም ሲነሱ ኮን ቹ የተነሳው በሰው ልጅ ስም ነበር። ሌሎቹ የሃይማኖት አስተማሪዎች ወይም መሪዎች ሲሆኑ ኮን ቹ የማህበራዊ ኑሮ እና የመንግስታዊ አስተዳደር አስተማሪ ነበር። ኮን ቹ ማስተማር ሲጀምር ጥንት ታላቅ የነበረችው ቻይና ወድቃ ነበር። በብዙ ጥቃቅን አገሮች የተከፋፈለች፣ አገሮቹ እርስ በርስ እየተዋጉ የሚከርሙባት፤ ተራው ሰው ጠባቂና መሪ በማጣቱ ለመጣው ሽፍታ እየገበረ በፍርሃትና በጭንቀት ተውጦ የሚኖርባት የወንበዴ አገር ሆና ነበር።
መምህር ኮን ቹ ወደ ጥንታዊው ስርዓት እንመለስ እያለ እያስተማረ ካገር አገር እየዞረ የሀገር አስተዳደርን ጥበብና የማህበራዊ ኑሮን ስርዓት እየሰበከ እድሜውን ሙሉ አሳለፈ፣ ከሞተ በኋላ ነው የመምህር ኮን ቹ ሀሳቦች ቀስ እያሉ በመላ ቻይና የተሰራጨት። በኮን ቹ ሀሳቦች እየተዳደረች ቻይና ወደር ወደ ሌለው ስልጣኔ ገነባች። ስልጣኔው አረጀ፤ የሰው ልጅ መብቶች ተረሱ፤ በኮን ቹ ሀሳቦች ስም የቻይና ህዝብ ይጨቆን ጀመር፤ ማኦ ዜዶንግ እና ጓደኞቹ ተነስተው አዲስ አብዮት እስኪያውጁ ድረስ።

4/ አብዮት በአረብ መሀመድ

ከመሐመድ በፊት አረቦች 360 ጣኦት የሚያመልኩ፤ እርስ በርስ ሲዋጉ የሚኖሩ ጥቃቅን ጉሳዎች ነበሩ። ነብዩ መሀመድ በአንድ አምላክ የሚያምኑ በህግና በመፋቀር የሚኖሩ አንድ ጠንካራ ህዝብ አደረጋቸው፡፡ መሀመድ ላገሩ ሰዎች በሰላም ጊዜ ግሩም አስተዳዳሪ፤ በጦርነት ጊዜ ጀግና የጦር አዛዥ፤ ከዚያም በላይ ተወዳጅ የሃይማኖት መምህር ነበር።
መሰረቱ የመሀመድ አብዮት የሆነው እስላማዊው ስልጣኔ ከዓለም ታላላቅ ስልጣኔዎች አንዱ ነው።


መፅሀፍ - እፍታ ቅፅ-5
ደራሲ- ስብሀት ገ/እግዚአብሔር

@zephilosophy
ሐይማኖተኝነት ለምኔ? ለምናችሁ? ለምናችን?
‹‹I think, therefore I am›› (Renè Descartes)
‹‹If God is not exist, it is necessary to invent him.›› (Voltair)
‹‹God is dead. God remains dead. And we have killed him.›› (Friedrich Nietzsche)
‹‹There are Truths, but not Thruth›› (Albert camus)
                         (ያዕቆብ ብርሃኑ)
                     **---*---*        
     
ደጃዘማች ግርማቸው ተክለሃዋሪያት በአባታቸው ፊታውራሪ ተክለሃዋሪያት ተክለማሪያም አውቶባዮግራፊ መጽሐፍ በከተቡት መቅድም ላይ ‹‹ወደ ውጭ ሀገር ለትምህርት ስሄድ ‹ልጄ ትክክለኛውን መለየት ስለማይቻል ሐይማኖት እንዳትቀይር፡፡ ሀገርና ሐይማኖት አይቀየርም፡፡ ነገር ግን በእናንተ ዘመን ፆምም ሊቀር ይችላል› አሉኝ ›› በሚል ዘመኑን የቀደመ ሃሳብ እንዳጋሯቸው ይነግሩናል፡፡

በእርግጥ በዚህ ዘመን ሐይማኖተኝነት በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ውስጥ እንደገባ ማየት ይቻላል፡፡ በመካከለኛው ዘመን በጥብቅ ይመለክባቸው የነበሩት የእስፓኝ፣ የጣሊያንና የሆላንድ አንዳንድ ገዳማት ዛሬ እንደቀልድ ማኪያቶ የሚጠጣባቸው ካፍቴሪያዎች ሆነዋል፡፡ ሌሎችም ሐይማኖታዊ ግልጋሎታቸው ተገድቦ የስደተኞች ጊዚያዊ ማረፊያ የሆኑ አሉ፡፡ ምን ይሄ ብቻ ባለፉት 50 ዓመታት በሚያስደነግጥ ፍጥነት ሐይማኖት አልባነት እየተንሰራፋ ይገኛል፡፡ pew international research center ባደረገው ጥናት መሰረት በአሜሪካ ከ1980- 2000 እ.ኤ.አ ከተወለዱ(millenias የሚሏቸው) ውስጥ 26 በመቶ የሚሆኑት ኢ­አማኒ(aethist) ናቸው፡፡በሌላ አንድ ጥናት ከዚሁ ጋር ተቀራራቢ የኢ-አማኒ ቁጥር በእንግሊዝና ዌልስም እንደተመዘገበ ይገለፃል፡፡ዛሬ ዛሬ ይሄ እውነት ጥብቅ አማኞች እንደሆንን በሚታሰበው በእኛ ሀገር እንኳን በይፋ መታየት ጀምሯል፡፡ ይህ ሂደት በዚህ ፍጥነት ከቀጠለ እንደ ሳይንቲስቶች አባባል ትንንሽ ጣዖቶችን ደምስሰው የመጡት ሐይማኖቶች ከአንድ ትውልድ በኋላ ከምድረገፅ ሊጠፉ ይችላሉ፡፡

ሐይማኖተኝነት ለምናችን? ፕሌቶ በጻፋት the last days of Socrates የተሰኘች መጽሐፍ ላይ አንድ ደቀመዝሙሩ ሶቅራጥስን ‹‹እኛ በሞራል መመራት ከቻልን ሐይማኖት ለምን ያስፈልገናል?›› ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ሶቅራጥስም ‹‹እኔና አንተ ለሞራላችን ስልምንገዛ ላያስፈልግን ይችላል፡፡ ሆኖም ተርታው ህዝብ ግን ሞራሉን እንዲያስጠብቅለት እግዚአብሔር ያስፈልገዋል›› ብሎ ይመልስለታል፡፡ አዎ የእግዚያብሔር መኖር ወይም አለ ብሎ ማሰብ ሕይወታቸውን በተስፋ የሚሞላላቸው እልፍ አዕላፋት ናቸው፡፡ እውነትስ ይሄ ህዝብ ድንገት እግዚያብሔር የለም ቢባል መጠለያ አልባ እርቃኑን መቅረቱ አይደለምን? በቻይና የባህል አብዮት(cultural revolution) ዘመን የሆነውን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ እዚህ ጋ ነው የፈረንሳያዊው ፈላስፋ ቮልቴር አስማት የሆነችብኝ አባባል ብቅ የምትለው ‹‹If God not exist, it is necessary to invent him.››  አዎ ሐይማኖቶች የሚሰጡንን የሞራል ልዕልና ሊተካ የሚችል ሌላ ሂደት እስካልፈጠርን ድረስ አደጋው ከባድ የሚሆን ይመስለኛል፡፡

ሐይማኖቶች ለሰው ልጆች ምን አበረከቱ? ይሄን ሀሳብ ለመተንተን ሺህ ገፆች አይበቁም፡፡ ነገር ግን በአንድ ቃል ሐይማኖቶች ለሺህ ዓመታት ለሰው ልጆች በተስፋ ማጣት ውስጥ ተስፋ ሲሰጡ አሳልፈዋል፡፡ በዚያው ልክ ሰላምና ፍቅርን ቢሰብኩም ቅሉ የጥላቻ መንስዔዎች፣ የጦርነት ምክንያቶች፣ የእልቂት ሰበቦችም ነበሩ፡፡ ሶሻሊዝም በተለይ የክርስትናውን ዓለም ከመሰረቱ አሽመድምዶ እንደሄደ ይታመናል፡፡ ነገር ግን ለለውጥ በሩን ዝግ ያደረገው የእስልምናው ዓለም እንኳን በግሎባላይዜሽን አስፈሪ ውሽንፍር ለለውጥ መንገዳገዱ የሚቀር አይመስልም፡፡ ሁሉንም ጊዜ የህይወትን ቅዠቶችን ሁሉ እያፈከረ ሲያልፍ የሚፈታው ይሆናል፡፡

@zephilosophy
የመጨረሻው ፈተና

‹‹ኢየሱስ እየመራቸው፣ ቡድኑ ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ ጀመረ፡፡ ሙሉዋ ጨረቃ ከሞአብ ተራሮች ተነሳች፡፡ ፀሐይም ከይሁዳ ተራሮች ጀርባ ጠለቀች፡፡ ለቅፅበት ሁለቱ ታላቅ የሰማይ ላይ ዕንቁዎች ቆም ብለው እርስበርስ ተያዩ፡፡ አንዱ ሲወጣ፣ ሌላኛው እየሰጠመ፡፡

ኢየሱስ በጭንቅላቱ ለይሁዳ ምልክት አሳየው፣ ከጎኑ እየሄደ ነው፡፡ ሁለቱ የሚለዋወጡት ምስጢር አላቸው፡፡ በሹክሹክታ ነው የሚያወሩት፡፡ አልፎ አልፎ ኢየሱስ ጭንቅላቱን ዝቅ አድርጎ፣ አልፎ አልፎ ይሁዳ፡፡ ልክ የእያንዳንዱ ቃል የወርቅ ቁራጭ ይመስል፣ እያንዳንዱ በጥንቃቄ የሌላኛውን ምላሽ ቃላት ይመዝናል፡፡

“አዝናለሁ ይሁዳ የኔ ወንድም ግን በጣም አስፈላጊ ነው” አለ፡፡ ኢየሱስ
“በፊት ጠይቄሃለሁ መምህር - ሌላ መንገድ የለም?”

“የለም ይሁዳ የኔ ወንድም፡፡ እኔ ራሴ ሌላ መንገድ ቢኖር ደስ ይለኝ ነበር፣ ተስፋ በማድረግ እስካሁን ስጠብቀው ነበር - ግን በከንቱ ነው፡፡ በፍጹም ምንም ሌላ መንገድ የለም፡፡ የዓለም ፍፃሜ እዚህ ነው፡፡ ይህ ዓለም፣ ይህ የሰይጣን መንግስት፣ ይጠፋል፡፡ የእግዚአብሔር መንግስትም ይመጣል፡፡ እኔ አመጣዋለሁ፡፡ እንዴት? በመሞት፡፡ ምንም ዓይነት ሌላ መንገድ የለም፡፡ አትርበድበድ ይሁዳ የኔ ወንድም፣ በሦስት ቀናት ውስጥ እንደገና እነሳለሁ” አለ፡፡

“ይሄንን የምትነግረኝ ልታጽናናኝና ልቤን ሳይከፋው እንድከዳህ ለማድረግ ነው፡፡ ፅናት አለህ ብለኸኛል - ይህን ያልከው እኔን ልታበረታኝ ነው፡፡ በፍጹም፣ ወደቁርጡ ጊዜ ስንቃረብ … በፍጹም፣ መምህር ልቋቋመው አልችልም!” አለ

“ትችላለህ ይሁዳ የኔ ወንድም፡፡ ፈጣሪ አንተ ያጣኸውን ያህል ብርታት ይሰጥሃል፡፡ ምክንያቱም አስፈላጊ ስለሆነ - ለኔ መሞት አስፈላጊ ሲሆን፣ የአንተም እኔን መካድ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁለታችን ዓለምን ማዳን አለብን፡፡ እርዳኝ” አለው፡፡

ይሁዳ አንገቱን ደፋ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጠየቀ “አንተ በኔ ቦታ ሆነህ ጌታህን ካድ ብትባል ታደርገዋለህ?” አለው፡፡
ኢየሱስም ለረጅም ጊዜ አብሰልስሎ በመጨረሻም “በፍጹም! እኔ የማደርገው አይመስለኝም፡፡ ለዚህም ነው ፈጣሪ አዝኖልኝ ቀላሉን ተግባር የሰጠኝ - መሰቀሉን” አለ፡፡››

፨፨፨፨፨

መፅሀፍ -የመጨረሻው ፈተና
ደራሲ-ኒኮስ ካዛንታኪስ
ታሪካዊ ልብወለድ
- - - - -

©️የጥበብ መንገድ
"እውነት ምንድን ነው?"
ጲላጦስ

አንዳንዶች ፍልስፍና በዘመናችን እምብዛም የሚወደድ ሆኖ አለመገኘት ብቻ ሳይሆን እየተጠላም ነው ይላሉ፡፡

ሶቅራጥስ ራሱን አሳልፎ የሰጠላት፣ ፕሌቶም ፍልስፍናን ከማጣት ይልቅ ሞት ይሻላል በማለት ሁለት ጊዜ መስዋዕት ሆኖ የቀረበላት፧ ጳጳሳት ተከታዮችዋን ያሰሩባት፣ ያሰቃዩባት... ይህች «ፍልስፍና» «ለመሆኑ ምን ብታነሳ ነው ይህ ሁሉ የመጣባት?» ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

ተከታዮቿ የፍልስፍና ትልቁና የመጀመሪያ ጥያቄዋ «እውነት» ስለሆነ ነው፤ ይላሉ፡፡ «እውነት ምንድነው?» የሚለው ጥያቄ ፍልስፍና የተጣለችበት መሠረት ነው:: "በእርግጥ የምናየውን ነገር የምናየው፤ የምንሰማውን ነገር የምንስማው ፤ የምናሸተውን ነገር የምናሸተው ፤ የምንነካውን ነገር የምንነካው ወዘተ እውነት ስለሆነ ነው? ወይስ እውነት ነው ብለን ስለምናስብ?" በማለት ፈላስፎቹ ይጠይቃሉ፡፡

ይኸ ዓለም፡- «ለእያንዳንዱ ሰው እምነቱ የእሱ እውነት ነው» ይለናል፡፡ «እምነትህ እውነት ነው›› በሚለው በዚህ ዓለም ውስጥ ፈላስፎቹ ደግሞ «ማስረጃ ማቅረብ የማትችልበት እምነት እውነት ሊሆን አይችልም» ይላሉ።

ታላቁ ፈላስፋ ፍሬዴሪክ ኒቼ ፦«የምታምነው ለመኖሩ ማስረጃ ማቅረብ ካልቻልክ እምነትህ ውሸት ነው፤ አባቴ ለእኔ ያስተላለፈው እምነት አያቴ የነገረውን ነው ፤ አያቴም የቅድም አያቴን ይዞ ለአባቴ አስተላለፈው፤ እንግዲህ እኔ የምኖርበት እምነት አስቀድሞ ሌሎች የኖሩበትን እንጂ እኔ በማስረጃ አረጋግጬ ያገኘሁት አይደለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ለእምነትህ ማስረጃ የለህምና ውሸት ነው›› ይላል፡፡ ሌሎችም ፈላስፎች በዚህ ይስማማሉ፡፡

እንግዲህ ወደ «እውነት» ጥያቄ ስንመጣ ኒቼ ሊነሳ የሚገባው ፈላስፋ ይሆናል፡፡ እንደኒቼ እምነት
«እውነት በተገቢ ሁኔታ የተነሳችበት የተጠየቀችበት በአንድ ሰውና በእንድ ቦታ ብቻ ነው፤ ይኸውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እሱም በጲላጦስ ነው» ይላል፡፡ አናቶሊ ፍራንስም በዚህ አባባል «እስማማለሁ ብቻ ሳይሆን አምንበታለሁም» ይላል።

«ጲላጦስም፡- እንግዲህ ንጉሥ ነህን? አለው::

ኢየሱስም መልሶ፡-" እኔ ንጉሥ እንደሆንሁ አንተ ትላለህ እኔ ለእውነት ልመሰክር ተወልጃለሁ፤ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው፡፡"

ጲላጦስም፦ "እውነት ምንድር ነው? አለው"
                                                ዮሐ 18:38

እነሆ እኛም እንደ ጲላጦስ እውነት ምንድን ነው? ብለን እንጠይቃችኋለን

@zephilosophy
አሁን ላይ #እውነት ብላችሁ የምታምኑት ነገር ምንድ ነው?
anonymous poll

ቤተሰባችሁ (አካባቢያችሁ) የሰጣችሁን እምነት – 117
👍👍👍👍👍👍👍 33%

ሁሉንም እምነቶች መርምራችሁ የመረጣችሁትን እምነት – 84
👍👍👍👍👍 24%

ጠይቃችሁና አስባችሁ የደረሳችሁበትን ግንዛቤ – 53
👍👍👍 15%

እውነት ሊታወቅ እንጂ ሊታመን አይችልም – 51
👍👍👍 15%

በመገለጥ የተረዳችሁትን  ግንዛቤ – 45
👍👍👍 13%

👥 350 people voted so far.
ሌላም ጥያቄ አለኝ

ከዚህ poll እንደምናየው ስለ እውነት ያለን መረዳት የተለያየ እንደሆነ እና እዚህ ቻናል ላይ ለየት ያለ መረዳት ያላቸው ሰዎችም እንዳሉ አይተናል።

መልሳችሁ ሙሉ ይሆኑ ዘንድ እያንዳንዱን መልስ ስትመልሱ እንዚህንም ጥያቄዎች መመለስ ይኖርባችኋል።

1️⃣ሳትመረምሩ ከቤተሰባችሁ ያገኛችሁትን እምነት እንደ እውነት ተቀብሎ መኖር ከቻላችሁ ባህል እንጂ እውነት እንዴት ሊባል ይችላል።እውነታችሁን የወሰነው ውልደታችሁ እንጂ መረዳታችሁ ነው ልንል እንችላለን? አምላክ መርጦኝ ነው ካልችሁስ አምላክ ያለስራችሁ የሚመርጣችሁ ኢ-ፍትሀዊ አምላክ ሊሆን አይችልም።የሌላውንስ እውነት ሳትመረምሩ እንዴት ሀሰት ነው የማለት ድፍረቱን አገኛችሁ።

2️⃣ሁሉንም እምነቶች መርምራችሁ የመረጣችሁትስ ብትሆኑ አምናችሁ ነው የመረምራችሁት ወይስ መርምራችሁ ነው ያመናችሁት? ያመናችሁትን ለማረጋገጥ ከሄዳችሁስ እንዴት መረመራችሁ እንላለን?

3️⃣ጠይቃችሁና አስባችሁ የደረሳችሁትስ ብትሆኑ በአእምሮ ሊታወቅ የማይችለውን  እውነት አስባችሁ እንዴት አገኛችሁት? በየጊዜው የሚለዋወጠውን አእምሮን እንዴትስ አመናችሁት?

4️⃣በመገለጥ የደረሳችሁበትስ አምናችሁ ነው የተገለጠላችሁ ወይስ ተገልጦላችሁ ነው ያመናችሁት? የተገለጣችሁስ እውነት የገዛ ህልሞቻችሁ ምኞቶች ቢሆኑስ ደግሞስ የተገለጠላችሁን ካልኖራችሁ ወይም ካስመሳላችሁ እውነትን አገኛችሁ ማለት እንችላለን? ከሌሎቹስ በምን ተለያችሁ?

5️⃣ እውነት ሊታወቅ እንጂ ሊታመን አይችልም እውነትን ካወቅነው መሆን እንጂ  ማመን አያስፈልግም። ማመን ውስጥ ጥርጣሬ አለ ያላችሁስ። የማይታየውን ጥልቅ ሚስጢር  እንዴት አወቃችሁት? ካላወቃችሁትስ እንዴት ነው የምታውቁት?

እናንተም ሌሎች ጥያቄዎች መጨመር ትችላላችሁ።መልሶቻችሁንም ማብራራት ትችላላችሁ።

"ጥያቄዎች እውነት ላይ ባያደርሱንም የተሸከምናቸውን ውሸቶች አራግፈን እውነትን እንድናገኝ (እውነት እንድያገኘን) በር ይከፍትሉናል። በእርግጥ እውነት አደገኛ ነው በቆንጆ ህልሞችና በታሪክ ውስጥ ለኖሩ ሰዎች ሁሉ እውነት አደገኛ ነው❗️"

@zephilosophy
"ለዲሞክሪተስ እውነት አተሞች ብቻ ናቸው፤ ለፊዚክስ ባለሙያዎች እውነት ገና ያልተደረሰበት የሒሳብ ሕግ ነው፤ ለማርክሲስቶች እውነት ተጨባጩ ዓለም ነው ፤ ለሃሳባዊ ፈላስፎች እውነት ነባራዊ የሃሳብ ህግጋት ናቸው፤ ለፖለቲከኞች እውነት የተከታዮቻቸው ብዛት ነው፤ ለሃይማኖተኞች ግን እውነት እምነት ነው፡፡"

ብሩህ አለምነህ
@zephilosophy
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
"ለዲሞክሪተስ እውነት አተሞች ብቻ ናቸው፤ ለፊዚክስ ባለሙያዎች እውነት ገና ያልተደረሰበት የሒሳብ ሕግ ነው፤ ለማርክሲስቶች እውነት ተጨባጩ ዓለም ነው ፤ ለሃሳባዊ ፈላስፎች እውነት ነባራዊ የሃሳብ ህግጋት ናቸው፤ ለፖለቲከኞች እውነት የተከታዮቻቸው ብዛት ነው፤ ለሃይማኖተኞች ግን እውነት እምነት ነው፡፡" ብሩህ አለምነህ @zephilosophy
እውነትን ፍለጋ

በሃይማኖታዊ አስተሳሰብ የሰው አቅምና ምኞቱ የሚስተካከሉት በእምነት ውስጥ ሲኖር ብቻ ነው:: "እምነት" ይላል ቅዱስ ጳውሎስ ፤

"እምነት ምንም አይነት ተጨባጭ መረጃ በሌለን ነገር ፣ ተስፋ ባደረግነው ነገር ፣ እርግጠኛ የሚያደርገንና ነገንም የማያስረዳን ነው ፤ "
                                           ዕብራ 11፡1

ለሳይንሱ ግን እምነት ብቻውን የስንፍና መፈልፈያ፣ የንቃተ ህሊና ዝቅተኛ ደረጃ፣ተስፋ ለቆረጠ ሰው የሚሰጥ ሃሳባዊ ዳቦ ነው፡፡ ካርል ማርክስም  "ሃይማኖት የህዝቦች አደንዛዥ ዕጽ ነው፤" ይላል። ሰዎች ከጥንት ዘመን ጀምሮ በብዙ ነገሮች ሲያምኑ ነበር፤ አብዛኛው እምነታቸው የተፈጥሮኝ አደጋዎች መቆጣጠር ካለመቻላቸው የተነሳ የተፈጠሩ ነበሩ፡፡ ተፈጥሮን መቆጣጠር ሲችሉና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችንም እያበለፅጉ ሲሄዱ ግን የበፊት እምነቶቻቸው ከንቱ እንደነበር ደረሱበት፥ ስለዚህም የጦርነት፣ የአውሎ ንፋስ፣ የጎርፍ፣ የፍቅር፣ የፀሐይ... አምላኮቻቸውኝ ሁሉ ገደሏቸው::

እንደሌሎች የወቅቱ የዓለም ህዝቦች ሁሉ የብሉይ ኪዳን እስራኤላውያንም ሳይንሳዊ ዕውቀታቸው ዝቅተኛ ስለነበር እያንዳንዱን ተፈጥሯዊ ክስተት እነሱ ከአግዚአብሔር ጋር ባላቸው ግንኙነት ምክንያት የተፈጠሩ አድርገው ያስቡ ነበር፡፡ በዚህም ለምጽን ሀጢያተኛ ሰዎች ላይ የሚመጣ የእግዚአብሐር ቁጣ ያደርጉታል፤ አስቀድሞ የነበረውን የኖራ ዲንጋይ የሎጥ ሚስት ወደ ጨው ሃውልትነት ተቀይራ ነው ይላሉ፣ ተፈጥሯዊ የሆነውን የሴቶችን የወር አበባ የእግዚአብሔር እርግማን ነው ይሉታል፤ የፀሀይ ግርዶሹን የነቢዩ ኤልያስ ተአምር ነው ይላሉ፤ በራሱ ተፈጥሯዊ ሂደት የሚፈጠረውን ቀስተ ደመና ለኖህ የተሰጠው ቃል ኪዳን ነው ይላሉ፤ የተፈጥሮን ክስተቶች ሕጋቸውን፣ አመጣጣቸውንና አካሄዳቸውን ስለማያውቁ እግዚአብሔር የትየለሌ የሆነውን ፍጥረቱንና ሌሎች የዓለም ህዝቦችን ሁሉ ትቶ ከእነርሱ ጋር ብቻ በፈጠረው ግንኙነት ውስጥ እነዚህ ነገሮች እንደተከሰቱ ያምናሉ፡፡ ስፒኖዛ "የተፈጥሮን ክስተቶች ከራሳችን እምነትና ስሜት አንጻር ብቻ በተናጥል አንመልከታቸው፤" የሚለው እንደዚህ አይነት ስህተት ላይ እንዳንወድቅ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ እምነቶች ታዲያ ስህተት መሆናቸውን ያጋለጠው የሳይንስ እድገት ነው፡፡

በፊት ሁሉን ነገር የሚያንቀሳቅሰው እግዚአብሔር እንደሆነ ይታመን ነበር ፤ በኋላ ላይ ግን ጋሊሊዮና ኒውተንን የመሳሰለሉ ሊቃውንት Force, Gravity, Motion ... የመሳሰሉ የተፈጥሮ ህጎች ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በመንስዔ - ውጤት አንድ ጊዜ የተወሰኑ ቋሚ የተፈጥሮ ሕጎች መሆናቸውን ሲያስረዱ እግዚአብሔርም ከዓለም ጋር ያለው ግንኙነት (ጣልቃ ገብነት) ውስን እንደሆነ ግንዛቤ ተወሰደ። ስለሆነም ሰዎች ሁልጊዜ ከንቃት ህሊናቸው ኋላቀርነት የተነሳ ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ነገር በእግዚአብሔር የስልጣን ክልል ስር እያደረጉት በዚህ በኩል ያለው ሕይወታቸውን በእምነት ይሞሉታል፡፡ ስለሆነም ሰዎች በእምነታቸው ምክንያት ላለፉት ብዙ ዘመናት እየተታለሉ ኖረዋል፤ ወደፊት ለሚመጡትም አያሌ ዘመናት እየተታለሉ ይኖራሉም ነው - የሳይንሱ ስጋት። ስለዚህ እውነትን በማፈላለግ ሂደት ውስጥ የስሜት ህዋሶቻችን ላይም ሆነ እምነታችን ላይ ያለን ተስፋ የሞተ ነው::

ሃይማኖቱ ግን ይሄንን አባባል፣ "ወደ ቁሳዊ ህይወት ያደላ ጥራዝ ነጠቅ አመለካከት ነው፤" ይለዋል፤

"በምናየውና በቤተሙከራ በሚገኘው ነገር ብቻ ከተመካን ሕይወታችን ውስን፣ አመጣጣችንን በደንብ የማያስረዳ ፣ ቁሳውያን፣ ሞተን በስብሰን የምንቀር፣ ፈጣሪያችንን የሚያስረሳን፣ ግብረኃብነትንም የሚያጠፋ ነው" ይላል። "እምነት ግን ለዚህ ዓለም ሕግጋት ላልተገለጡ ሆኖም ግን የሕይወታችን መነሻም ሆነ መድረሻ የሆኑ ጉዳዮችን እንድናውቅና በእነርሱ እርግጠኛ እንድንሆን ያደርገናል ፤ " ይላል ሃይማኖት በበኩሉ።

ጀርመናዊው ፈላስፋ ኒቼ ግን "በሃይማኖት በኩል ለዚህ አለም የምንሰጠው ፍቺ ዘመኑ አልፎበታል" ይላል። አሁን ሃይማኖት አርጅቶ እየሞተ ነው፤ እየሞተ ባለ ነገር ደግሞ ዓለምን መተርጎም የራስ ሞትንም ያስከትላል፤ ከእውነትም አያደርስም። የአይሁድ - ክርስትና ሃይማኖት ከ2000 ለሚበልጡ ረጅም ዓመታት የዚህ ዓለምና ሞራላዊ እሴቶች መተርጎሚያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ይህ ሃይማኖት ስለዚህ ዓለምና ስለሰው ልጅ አመጣጥ እንዲሁም ማኅበራዊ ኑሮና የመጨረሻ የህይወት ግብ ላይ በሰጠው ትንታኔና ተስፋ የሰውን ልጅ ከተስፋ መቁረጥና ከስርዓት አልበኝነት ተከላክሎ እዚህ አድርሶታል፡፡

አሁን ግን በሳይንሳዊ አስተሳሰብ የዳበረ ንቃተ ህሊና፣ በቴክኖሎጂ የተፈጥሮን አደጋዎች መቆጣጠር የቻለ ንቃተ ህሊና፣ ማህበረሰባዊና ግለሰባዊ ደህንነቱን በዲሞክራሲና በሀብት ክምችት ማስጠበቅ የቻለ ንቃተ ህሊና የአይሁድ - ክርስትና - እስልምና ሀይማኖት መሰረት የሆኑትን "ፍርሃትን ጉስቁልናን፣ድንቁርናንና  እምነትን" እየገደላቸው ነው፡፡ የእነዚህ መሰረቶች መሸርሸርን ተከትሎ ብዙ ቁጥር ያለው ሰው በአይሁድ - ክርስትና - እስልምና ውስጥ የተሰበከው እግዚአብሄር ላይ ጥርጣሪያቸውን ማንሳት ጀምረዋል፡፡ ለዘብተኝነት የእንደዚህ አይነት የህይወት አኗኗር እንዱ መገለጫ ነው፡፡ ኒቼም የሚለው ይሄንኑ ነው።

"በየቀኑ ሰዎች ፣ ሁላችንም እግዚአብሄርን እየገደልነው (እየተውነው) ነው፤ በዚህም ምክንያት የአይሁድ - ክርስትና - እስልምና ሃይማኖት እንዲሁ በየቀኑ እየሞተ ነው፡፡ እሱ የተረጎመልን አለምም ከእርሱ ጋር አብሮ እየጠፋ ነው፡፡ በመሆኑም እየሞተ ያለ ሃይማኖት ወይም እምነት የዚህን ዓለም የመጨረሻ እውነት ሊነግረን አይገባም፤ ደግሞም አይችልም፡፡ ሃይማኖቱ የሰጠን እሴቶችም እንደገና መከለስ (revaluation of values) አለባቸው፡፡"

የወቅቱ የሮማ ካቶሊክ ፓትሪያርከ ቤኔዲክት 16ኛም ክርስትና ከህዝብ መድረኮች እየጠፋ መሆኑን አምነው፤ ሆኖም ግን ይህ ክስተት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን እንግሊዝን በመስከረም 2010 በጎበኙበት ወቅት መናገራቸውን ቢቢሲ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ዘግቦታል፡፡ ፓትሪያርኩ በዚሁ ንግግራቸው የአውሮፓ ስልጣኔና ዲሞክራሲ የተገነባው በክርስቲያናዊ ስነምግባርና አስተምህሮ ላይ መሆኑን በመጥቀስ፤ ሆኖም ግን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ግፊት ህዝቡ ውስጥ እየተስፋፋ ያለው ቅጥ ያጣ ቁሳዊነትና አምልኮተ ሸቀጥ የዲሞክራሲያችንን መሰረት እያናጋው መሆኑን ጠቅሰዋል:: Aggressive secularism and commodity feitishism are becoming threat to our democracy. በመሆኑም በሳይንስ መታበያችን ከጋራ ጥፋት በስተቀር ሌላ የምናተርፈው ነገር የለም፡፡

መፅሀፍ፦ ፍልስፍና ፩
ደራሲ ፦ ብሩህ አለምነህ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
"የስልጣን ጥማት - የነፍስ ካንሰር "
ኦሾ

ጥያቄ - ፖስቲከኞችን የምትቃወማቸው ለምንድነው?

ኦሾ፦

ፖለቲከኞችን አልቃወምም ለምን እቃወማቸዋለሁ? እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም፡፡ የእኔን ንግግር በተሳሳተ መንገድ የሚገነዘቡ ይኖራሉ፡፡ እኔ የምቃወመው የስልጣን ጥማት የሚባለውን በሽታ ነው፡፡ የሰውን ንቃትና ዕድገት በተመለከተ ትልቁ በሽታ ይኸው የስልጣን ጥማት ነው፡፡ ልክ እንደ ካንሰር ነው - የነፍስ ካንሰር፡፡ የስልጣን ጥማት በብዙ መንገድ መገለፅ ይችላል፡፡ ቀላሉ ፖለቲካ ነው፤ ምክንያቱም ፖለቲካ ብዙ ብልህነት አይጠይቅም፡፡ ፖለቲካ የሚፈልገው ዋና አላማን ከጐን አስቀምጦ ብዙሃኑን በውሸት መሙላት መቻል ነው፡፡ እናም ብዙሃኑ ይሰቃያል ድሃ፣ አላዋቂ ነውና፡፡ ብዙሃኑ ሰው የህይወት ምቾትን ይፈልጋል፤ እንደ ሰው መኖር ይፈልጋል በክብር፡፡ ፖለቲከኞች ደግሞ ይህን ተስፋ ይሰጡትና ይህን ተስፋ ለራሳቸው ይጠቀሙበታል ምክንያቱም አንዴ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ ውስጣዊ ደስታ ይፈጠርባቸዋል፡፡ ስነ ልቡናቸው ይህን እንዲያደርጉ ይገፋፋቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በመሰረቱ በውስጣቸው አቅመ ቢሶች ናቸው፡፡ ስለዚህም ስልጣኑን ይፈልጉታል፡፡ ድክመታቸው፣ ሃይል አልባነታቸው፣ አቅመ ቢስነታቸው ይሰማቸዋል፡፡ ስለዚህም ወደ ብዙሃኑ ጠጋ ብለው ፍላጐትህን አሟላለሁ በማለት ተስፋ ይሰጡትና ድርድር ይገባሉ፡፡ እናም ብዙሃኑ ስልጣን ይሰጣቸዋል፡፡

አንዴ ስልጣኑን ከጨበጡ በኋላ ግን ቃላቸውን ይዘነጋሉ፤ በእርግጥ ቃል ሲገቡም ከልባቸው አልነበረም፡፡ አንዴ ስልጣኑን ከያዙ በኋላ እውነተኛ ማንነታቸው ይገለጣል፡፡

ሎርድ አክተን ‹‹ስልጣን ያባልጋል፤ ሙሉ ስልጣን ደግሞ ጨርሶ ያባልጋል› ያለው ፍፁም ትክክል ነበር፡፡ ስልጣን ለምን እንደሚያባልግ፣ እንዴት ሊያባልግ እንደሚችል ግን አላወቀም ነበር፡፡ ስልጣን ፈላጊው ሰው የሙስናን ዘሮች ተሸክሞ ሳይቆይ አልቀረም፤ ነገር ግን ዘሮቹን ተግባር ላይ ለማዋል ስልጣን ያስፈልገዋል፡፡ አንዴ ስልጣኑን ከያዘ በኋላ ቀስ በቀስ ጭምብሉ ይወልቅና እርቃኑን ይቀራል፡፡

ፖለቲከኛ ምንም ሳይሆን ራሱን ከፍ አድርጐ የሚመለከት ሰው ነው፡፡ በውስጡ ባዶነት ይሰማዋል፤ ያን ባዶነት ደግሞ ይፈራዋል፡፡ ይህን ባዶነቱን እንዲረሳ ታድያ አንድ ሰው መሆን አለበት፡፡ ስልጣን ይህን ዕድል ይሰጠዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በመዳፉ ሲያስገባ ይታየዋል፡፡ ይሄ ጊዜም እሱ ማንም ሳይሆን አንድ የተለየ ሰው እንደሆነ ይሰማዋል፡፡ እናም በዚያው መንገድ ይቀጥላል፤ ስልጣኑን አላግባብ መጠቀም ይጀምራል፡፡ አንዴ ስልጣኑን ከያዘ በኋላ ከዚያ መውረድ አይፈልግም፡፡ ስልጣኑ ከሌለ ባዶነቱና አቅመ - ቢስነቱ ይገለጥበታል፡፡

በሀይማናተኞች ፣ በሙሁራኖች ፣ በደራሲዎች በሌሎች የጥበብ ሰዎች፣ በሰዓሊዎች ፣በዘፋኞች፣ በዳንሰኞች ወዘተ ውስጥም ታገኙታላችሁ፤ ግን ያው የስልጣን፣ የዝና ጥማት ነው፡፡

እናም እኔ ፖለቲከኞችን አልቃወምም የስልጣን ጥማታቸውን እንጂ፡፡ የስልጣን ጥማት ሌላ ምንም ሳይሆን ራስን ከፍ አድርጐ የማየት ነፀብራቅ ነው፡፡ በእናንተና በህልውና መካከል የሚገኘው እንቅፋትም ይህ ነው፡፡ የራስ ኩራታችሁ ከፍ ባለ ልክ የዚያኑ ያህል ከህልውና ትርቃላችሁ፡፡ ራስን ከፍ አድርጐ የመመልከት ነገር ከሌለ .. ግንኙነት፣ ውህደት ይኖራል፡፡

ይህን የራስ ኩራት ግን እንድትጥሉት አልፈልግም፡፡ የራስ ኩራት እንዴት ያለ አስቸጋሪና ብልህ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ራስን የመጣል አይነት ጨዋታም ሊጫወት ይችላል፡፡ ይሄን ጊዜ «ተመልከቱ፣ እንደኔ ያለ ትሁት፣ እንደኔ ያለ ኩራት የሌለበት ሰው በዓለም አይገኝም›› ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ ከዚያም ዞሮ በጓሮ በር ይመጣል፤ ትሁት፣ ኩራት የለሽ ሆናችሁ ሳለ አንድ የሆነ ፍፁም የተለየ ሰው መሆን ይኖርባችኋል፡፡ ልትጥሉት ከሞከራችሁ በጓሮ በር ተመልሶ እንደሚመጣ እነግራችኋለሁ፡፡ ጨዋታውን ከተገነዘባችሁ በቂ ነው፡፡ ስንት ጨዋታ እንደሚጫወትና በምን አይነት መንገድ እንደሚያታልላችሁ አስተውሉ፤ ንቁ ሁኑ፡፡ የራስ ኩራትን መንገዶች ሁሉ ካወቃችሁ መብራት ሲበራ ጨለማው እንደሚጠፋ ሁሉ ኩራታችሁም ይጠፋል፡፡

ይቀጥላል....

@zephilosophy
@zephilosophy
2025/05/12 17:43:49
Back to Top
HTML Embed Code: