tgoop.com/Tserezmut/849
Last Update:
ሰላም ዋላችሁ?
ብዙዎቻቹ እንደጠየቃችሁኝ የዛሬው ቅዳሴ ይለያል ወይ ላላችሁት ምነው ተለየብኝ ላላችሁት ለመመለስ መጥቻለሁ መልካም ቆይታ።
የዛሬው ቅዳሴ ተለይቶ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሁላችሁም እንደምታውቁት 14 የቅዳሴ አይነት አለ ።
ሁሉም አንድ ሆነው ልዩነትም አላቸው ።
ለምሳሌ ቅዳሴ ሐዋርያት ሐዋርያትን የሚነካ
ቅዳሴ ማርያም ደሞ ማርያምን የሚገልፅ
ቅዳሴ እግዚእ ደሞ የጌታ ቅዳሴ ነው።
እናም ዛሬ መጋቢት 10 በዓል ስለሆነ መስቀልን የሚነካ መሆን አለበት ።
ስለዚህ ስለ መስቀል በብዛት የተረከው ወይም የደረሰው በቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው ስለዚህ ።
የዮሐንስ አፈወርቅን ቅዳሴ ዛሬ ይቀደሳል ማለት ነው። እንጂ ሌላ የተጨመረ ወይም የተቀነሰ አዲስ ነገር የለም።
2 ተኛ ጥያቄያቹ ደሞ የ የ የ ይላሉ ምን ማለት ነው በቅዳሴው ላይ ብላቹህኛል።
ተሳስታቹሀል
የ ሳይሆን ዬ ነው የሚሉት ትርጉሙም ወየው (ወይኔ) እንደማለት ነው።
3 ተኛ ጥያቄያቹ ደሞ ሠራዊቱስ የለያል ወይ ?
አዎ ይለያል የዮሐንስ አፈወርቅ ሰራዊት አለ እሱ ነው የሚባለው።
ስለጠየቃችሁኝ አመሠግናለሁ
ዲ/ን ፍቅረ አብ መለስኩላቹ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል ውስጥ
ሌላም ጥያቄ ካላቹ በዚህ ጠይቁን
👇👇👇👇👇
@serate_bte_krstian
@serate_bte_krstian
@serate_bte_krstian
BY ፀረ ዝሙት
Share with your friend now:
tgoop.com/Tserezmut/849