tgoop.com/SadatTextPosts/932
Last Update:
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِنَّ لِلَّهِ مَلَائِكَةً سَيَّاحِينَ فِي الْأَرْضِ يُبَلِّغُونِي مِنْ أُمَّتِيَ السَّلَام﴾
“የህዝቦቼን ሰላምታ ለእኔ የሚያደርሱ በምድር ተንቀሳቃሽ የአላህ መላኢካዎች አሉ።”
📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 6853
*****
ከደጃል ፈተና ለመጠበቅ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“ከምዕራፍ አልካህፍ የመጀመሪያ አስር አንቀፆችን በጭንቅላቱ የሸመደደ ከደጃል ፈተና ይጠበቃል።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 809
*****
ማሰታወሻ
ሱረቱል ካህፋ መቅራት አንረሳ
*****
እህቴ ተጠንቀቂ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿أيما امرأةٍ استعطرتْ فمرتْ على قومٍ ليجدوا من ريحِها فهي زانيةٌ﴾
“ሽቶ ተቀብታና መዓዛው እንዲያውዳቸው አስባ በሰዎች አጠገብ የተላለለፈች ማንኛዋም ሴት ዝሙተኛ ነች።”
📚 ነሳዒ ሶሂህ ብለውታል: 5141
*****
ጌታችን ይገረማል!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إنّ ربَّك ليَعْجَبُ من عبدِه إذا قال: ربِّ اغفر لي ذنوبي، وهو يعلمُ أنّهُ لا يغفرُ الذنوبَ غيرِي.﴾
“ጌታችሁ እንዲህ ብሎ በሚናገረው ባሪያ ይገርማል። ‘ጌታዬ ሆይ ለወንጀሌ ምህረትን አድርግልኝ’ እሱም ያውቃል ከኔ ውጪ ወንጀልን የሚምር እንደሌለ።”
📚 ሶሂህ አልጃሚ: 2069
*****
አትቆጣ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿ليسَ الشَّدِيدُ بالصُّرَعَةِ، إنَّما الشَّدِيدُ الذي يَمْلِكُ نَفْسَهُ عِنْدَ الغَضَبِ.﴾
“ጀግና ማለት ታግሎ የሚጥል ሳይሆን በንዴት ግዜ እራሱን የሚቆጣጠር ነው።”
📚 ቡኻሪ (6114) ሙስሊም (2609) ዘግበውታል
*****
ለልጆች የሚደረግ መለኮታዊ ጥበቃ!
ከኢብኑ አባስ (رضي ﷲ عنهما) ተይዞ: እንዲህ ይላል፦
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ለሀሰንና ለሁሰይን እንዲህ እያሉ ጥበቃ ያደርጉላቸው ነበር፦
﴿أُعِيذُكُمَا بِكَلِمَاتِ اللَّهِ التَّامَّةِ مِنْ كُلِّ شَيْطَانٍ وَهَامَّةٍ ، وَمِنْ كُلِّ عَيْنٍ لَامَّةٍ﴾
“ምሉዕና ፍፁም በሆኑት የአላህ ቃላት ከሰይጣናት ሁሉና ከእኩይ ሰው (ተንኮል) እንዲሁም ጎጅ ከሆነ ዓይን ሁሉ እጠብቃችኃለሁ፡፡”
📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል: 2060
*****
«🔹በካፊሮች በዓል እንኳን አደረሳችሁ ማለት አይፈቀድም ምክንያቱም ያሉበትን ክህደት ( ኩፈራችውን) መደገፈ ነው ።
(فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِینَ * وَدُّوا۟ لَوۡ تُدۡهِنُ فَیُدۡهِنُونَ * وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافࣲ مَّهِینٍ)
አስተባባዮችንም አትታዝዙ፡፡ ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡
*****
የጁሙአ ልዩ ሰጦታ
ከጃቢር رضي الله عنهእንደተላለፋው ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዎል
የጁሙአ ቀን አንዲት ሰአት አለች በዛ ሰአት الله ሚጠይቅ
ሙስሊም አይኖርም የጠየቀውን
ቢሰጠው እንጂ የመጨረሻዋ ሰአት ተጠባበቋት ከአስር በኋላ
አብዳውድ ዘገበውታል
በዱአ በርቱ እኔንም እንዳትረሱኝ አደራ
*****
እህቴ ተጠንቀቂ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿أيما امرأةٍ استعطرتْ فمرتْ على قومٍ ليجدوا من ريحِها فهي زانيةٌ﴾
“ሽቶ ተቀብታና መዓዛው እንዲያውዳቸው አስባ በሰዎች አጠገብ የተላለለፈች ማንኛዋም ሴት ዝሙተኛ ነች።”
📚 ነሳዒ ሶሂህ ብለውታል: 5141
*****
ማስታወሻ፡
ቀኑ ጅምአ ነው በግዜ ተገኝ እንዲሁም ስለዎት እንብዛ الله ይረዳን
*****
ይገረማል!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إنّ ربَّك ليَعْجَبُ من عبدِه إذا قال: ربِّ اغفر لي ذنوبي، وهو يعلمُ أنّهُ لا يغفرُ الذنوبَ غيرِي.﴾
“ጌታችሁ እንዲህ ብሎ በሚናገረው ባሪያ ይገርማል። ‘ጌታዬ ሆይ ለወንጀሌ ምህረትን አድርግልኝ’ እሱም ያውቃል ከኔ ውጪ ወንጀልን የሚምር እንደሌለ።”
📚 ሶሂህ አልጃሚ: 2069
*****
📖አያተል ኩረስይን ም ማንበብ!!!
የالله መልክተኛ صلى الله عليه وسلم አያተል ኩረስይን ከግዴታ ከሰላት ቦሃላ የቀራ ጀነት ከመግባት ምንም አይከለከለውም ሞት እንጂ
📚ሲልሲለቱ አሰሂህ 972
*****
አላህ ለወንጀሉ ምህረት ያደርግለታል…
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“ዑዱውን ለሰላት አሳምሮና በተሟላ መልኩ ያደረገ፤ ከዛ ለግዴታ ሰላት ጉዞ አድርጎ በመስጂድ ውስጥ ከሰዎች ጋር ወይም በጀምዓ ( በመስጅድ) የሰገደ። አላህ ለወንጀሉ ምህረት ያደርግለታል።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 232
*****
መከራ የገጠመውን ሰው ሲያዩ የሚባል ዱዓ
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“መከራ ያገኘውን ሰው የተመለከተ ከዛም ይህን ዱዓ ‘አንተን ከሞከረህ ነገር ለጠበቀኝ ከፍጡራኖቹ ከብዙዎች ላላቀኝ አላህ ምስጋና ይገባው’ ያለ። መከራው አያገኘውም።”
📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 2737
*****
♠እሬቻ እንደ ኢስላም ?
1 የሸረክ ተግባረ የሚፈፀምበት
2 ከእስልምናችን ጋር በጣም የሚገጭ
✔ ማንኛውም ሙስሊም የሆነ ሰው ወደዚህ ቦታ ከመሄድ ሊቆጠብ ይገባል።
✔ ወላጆች ልጆቻችሁን ልታስተምሩና ልትከለክሉ ይገባል።
✔ዳዒዎች በተለይም የኦሮምኛ ቋንቋ የምትችሉ ልታሰጠነቅቁ ይገባል ። ፡الله ይጠበቅን
*****
🔰ከቀናቶች በላጬ የጁምአ ቀን ነው።
ረሱልም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾
“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”
📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል: 1531
*****
#የሰደቃ ትሩፋት!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿داوُوا مَرضاكُمْ بِالصَّدقةِ﴾
“በሽተኞቻችሁን በሰደቃ አክሙ።”
📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 3358
*****
ሶላት!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“በትንሳኤ ቀን አንድ ባሪያ በቅድሚያ ከሚጠየቅባቸው ሥራዎች አንዱ ሰላቱ ነው። እሱ ከተስተካከለ ሌሎች ስራዎቹም የተስተካከሉ ይሆናሉ። እሱ ከተበላሻ ሌሎች ስራዎቹም የተበላሸ ይሆናሉ።”
📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 413
*****
ለቅሶዋችሁ በበዛ ነበር!
BY Sadat_Text_Posts
Share with your friend now:
tgoop.com/SadatTextPosts/932