tgoop.com/SPMMC/2856
Last Update:
የማህፀን በር ካንሰር የምንለው ወደ ካንሰር ከማደጉ በፊት በቀላሉ የመታከም እድል ያለው እና ችላ ያልነው ቀላል ምልክት እንደነበር ያውቃሉ?
ይህ ወር የማህፀን በር ካንሰር ላይ ያለንን መረዳት ለማሳደግ የምንሰራበት አለም አቀፍ ቀን ነው፡፡
በዚህ ክፍልም የማህፀን በር ጫፍ ምንነትን ሰው አውቆ ነገር ግን የሚዘናጋባቸውን ዋና ዋና ምልክቶች፣ ደረጃዎች እና ህክምናዎች በዝርዝር እናያለን፡፡
ከዚህ በፊት ስለምንነቱ በበቂ ሁኔታ የተሰራ ሲሆን አሁንም ግን ብዙዎች ስለ ቅድመ ምልክቶቹ ባለማወቃቸው ወይም ችላ በማለታቸው የተነሳ ካንሰር እስከሚሆን ድረስ ተዘናግተው ይቆያሉ፡፡
ይህን በሽታ ደግሞ ዋና መከላከያ ዘዴ ቀላል የምንላቸው ምልክቶች ላይ ቀድመን መገኘት ነው፡፡
የፊታችን ጥር 20 ማክሰኞ ዕለት በምናዘጋጀው ዝግጅት ላይ በዘርፉ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ጋር በመሆን በዚህ ርዕስ ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦችን፣ ቀድመን ማወቅ እና መለየት ያለብን ምልክቶችን እና ምን አማራጭ እንዳለን በጥልቀት እናያለን፡፡ እንዳያመልጣችሁ!
መቼ፡ ማክሰኞ ጥር 20
የት፡ ሳችሞ ማዕከል አሜሪካን ኤምባሲ
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ እስከ 10፡00 ሰዐት
አሁኑኑ በዚህ ማስፈንጠሪያ በመመዝገብ ቦታ ይያዙ፡ https://forms.gle/Xcau9mkVJubba7Bu8
ይህን ዝግጅት ከሳችሞ ማዕከል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ በመሆኑ እና ተሳታፊዎችም የአባልነት ማረጋገጫ ስለሚያስፈልጋቸው ከዚህ በታች ያለው ሊንክ ላይ መመዝገብዎንም ያረጋግጡ፡፡
https://bit.ly/SatchmoCenterMembership
በዕለቱ ሲመጡ መታወቂያዎን እና ስልኮን ይያዙ፡፡
ላፕቶፕም ሆነ ታብሌቶችን ወደ ኤምባሲው ግቢ ማስገባት እንደማይቻል ከወዲሁ በትህትና እናሳውቃለን፡፡
BY St.Paul's Hospital Millennium Medical College

Share with your friend now:
tgoop.com/SPMMC/2856