tgoop.com/Optimisticbatch/3334
Last Update:
የ12ኛ ክፍል ፈተና ወረቀት እስከ አርብ ድረስ ተጓጉዞ ይጠናቀቃል‼️
🎲የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከየካቲት 29 ቀን 2013 ጀምሮ የሚሰጠዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወረቀት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እስከ መጪዉ አርብ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ተጓጉዞ እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።
🎲የፈተናዎች ኤጀንሲ ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ጋር ባደረገዉ ስምምነት መሰረት ፈተናዎቹ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተጓጓዙ መሆናቸዉን የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ቱሬ ተናግረዋል፡፡
🎲በጥብቅ ቁጥጥር በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ አጃቢነት በተቀመጠዉ አቅጣጫ እና የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተጓጓዘ ነዉ ብለዋል፡፡
🎲አያይዘዉም ፈተናዎቹ ወደ ክልል ከተሞች ሲደርሱ የየክልሎቹ ፖሊስ እና ልዩ ሀይል ጥብቅ ቁጥጥር እና እጀባ አድርገዉ ወደ ዞኖች እንደሚያደርሱም ተናግረዋል፡፡
🎲እስካሁን እየተደረገ ያለዉ የማጓጓዝ ሂደትም ሰላማዊ ነዉ ፤ ምንም አይነት ችግር አልገጠመም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
🎲የጸጥታ ስጋት አለባቸዉ የተባሉ ቦታዎች ላይም ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ በመከላካያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ታጅቦ እንደሚጓጓዝ ገልጸዋል፡፡
🎲በመላዉ ሀገሪቱ ፈተናዉ እስከ መጪዉ አርብ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ተጓጉዞ እንደሚጠናቀቅ ዶክትር ዲላሞ ማረጋገጣቸውን አሃዱ ሬድዮ ጣቢያ 94.3 (Ahadu FM RADIO) ዘግቧል።
BY Optimistic Batch

Share with your friend now:
tgoop.com/Optimisticbatch/3334