tgoop.com/Optimisticbatch/3270
Create:
Last Update:
Last Update:
የ12ኛ ክፍል ፈተና የካቲት 29 ይሰጣል።
የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫልም ብሏል።
የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በቀጥታ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በፈተና አሰጣጡ ላይ ለተፈጠረው መዘግየት በይፋ ይቅርታ መጠየቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
BY Optimistic Batch

Share with your friend now:
tgoop.com/Optimisticbatch/3270