በማኅበራዊ ሚዲያ በመልቀቅ የሚታወቀው አቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ ተመሰረተ !
ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የጥላቻ ንግግሮችን በማኅበራዊ ሚዲያ በመልቀቅ የሚታወቀው አቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ ተመሰረተ።
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕግ አገልግሎት መምሪያ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ክስ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የምርመራ መዝገቡ መብቱ ለሚፈቅድለት የዐቃቢ ሕግ ዘርፍ እንዲተላለፍ ጠይቋል።
የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካልን ለማዋረድ፣ለመስደብ እና የምእመኑን ስሜት ለመንካት ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እና ከ5000 በላይ ተከታዮች ባሉት የራሱ የዪቲዩብ ቻናል በውጪ ሀገር ሆኖ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።
በተጨማሪም ቅድስትቤተክርስቲያንን “የመተት እና ጠንቋይ ቤት ናት” በማለት ሲቀሰቅስ መቆየቱን የሕግ መምሪያው አስታውቋል።
በማያያዝም ግለሰቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችን፣በየገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ ገዳማውያን መነኮሳትና አገልጋዮችን ክብረ ክህነት የሚያቃልል ንግግሮችን ሲናገር እንደነበረም በክሱ ላይ አስታውሷል።
በክሱ ላይ አያይዞ መምሪያው እንደገለጸው ቤተ ተክርስቲያኒቱ የምትገለገልባቸውን ሃይማኖታዊ የጸሎት፣የታሪክ ፣የገድላትና ድርሳናት መጻሕፍትን “ድውያን መጽሐፍት ናቸው መጥፋት አለባቸው” ማለቱን ገልጿል።
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በቅድስና የምታከብራቸውንና የምትዘክራቸውን ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን “ጣኦታትና ጣኦት አምላኪ ናቸው” በማለት ግለሰቡ ወንጀል መፈጸሙንም በመሰረተው ክስ ላይ ጠቅሷል።
በአጠቃላይ ሰባት ነጥቦችን ያካተቱ የወንጀል ዝርዝሮችን በመግለጽም ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ግለሰቡ በሕግ ተጠያቂ እንዲደረግ አቤቱታውን አቅርቧል።
መረጃው:- የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።
#ድምፀ_ተዋህዶ
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

👍30❤22🙏11
tgoop.com/News_Tewahdo/14738
Create:
Last Update:

BY 🎤✨ድምፀ ተዋሕዶ✨🎤

Share with your friend now:
tgoop.com/News_Tewahdo/14738