KETBEB_MENDER Telegram 3562
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል 26

    ደራሲ - አብላካት

አቶ ሰለሞን እና አቶ እስክንድር ጋር ስንደርስ .....ሁለቱም ተያዩና ቃልኪዳን አለኝ አቶ እስክንድር በመጠራጠር ስሜት ውስጥ ሆኖ.... " አዎ አልተሳሳትኩም ቃል ነሽ" አለኝ..... አቶ ሰለሞንም ቀጠል አድርጎ " ቢረሳ ቢረሳ እንዴት የዳይመንድ ፈርጦች ይረሳሉ ? ከሁሉም በላይ ደሞ ቃል አንቺን አለማስታወስ በእውነቱ ንፉግነት ነው" ብሎ ፈገግ አለ........ምን ቤተክርስቲያን ሳስቀድስ እና ስዘምር ወይ በጎ ነገር ስሰራ እንዳየ ሰው አለማስታወስ ንፉግነት ነው ይላል... ባያስታውሰኝ ነበር እኮ እሚሻለኝ...... በቃ እኛ ሰዎች አሉባልተኛ ሆነን ቀረን ማለት ነው ? .....ምናለ በደህና ነገር ብንተዋወስ .... ማይለፍ ግራ በመጋባት ስሜት ውስጥ ሆኖ አይኑን ከአንዳችን ወደ አንዳችን እያንከባለለ ይቃኘናል...
"ምነው ሰላም አትይንም እንዴ ቃል" አለኝ አቶ እስክንድር...
"በጣም ይቅርታ ሀሳብ ውስጥ ሆኜ ነው እንዴት ናችሁ ?" ብዬ ተራ በተራ ጨበጥኳቸው
"እኛማ ደህና ነን እናንተ የውሀ ሽታ ሆናችሁ ከራችሁ እንጂ... እንደቀልድ ብዙ ወራት ሆናችሁ ወደ ዳይመንድ ከመጣችሁ የቤቱ ድምቀት እናንተ ነበራችሁ" አለ አቶ ሰለሞን
"አዎ ረጅም ጊዜ ሆነን ከተያየን..... ደሞም እዚህም ቢሆን ጓደኞችሽን እስካሁን አላየኋቸውም ብቻሽን ነው እንዴ የመጣሽው ?" አለኝ አቶ እስክንድር ቀጠል አድርጎ
"ፈራ ተባ እያልኩም ቢሆን መመለሴ ግድ ሆነ...አዎ ከዳይመንድ ከራቅን ረጅም ጊዜ ሆኖናል ወደዛ አካባቢ መተን አናውቅም... ጓደኞቼ ደህና ናቸው ዛሬ ከማይለፍ ጋር ነው የመጣሁት ለዛ ነው" አልኳቸው
"በሰላም ከሆነ እሺ..ልጅ ማይለፍ ምነው በዝምታ ተዋጥቅ ? ችግር አለ እንዴ ?" አለ አቶ እስክንድር
"በጭራሽ እዚሁ ነኝ ንግግራችሁን ጨርሱ ብዬ ነው" አላቸው ማይለፍ
"በቃ እንግዲህ እንገናኛለን ቃልዬ ቁጥርሽ የበፊቱ ነው አይደል ? እደውላለው" አለኝ አቶ እስክንድር
"አዎ እሺ እንገናኛለን" አልኳቸው.... ከማለፍ ጋር በዓይን ቻው ተባብለው ወደ መቀመጫቸው ተመለሱ.... እንኳን ከዚህ በላይ አልዘባረቁ ብዬ ፈጣሪዬን እያመሰገንኩ ሳለሁ ማይለፍ...
"ከዚህ እንውጣ!" አለኝ በተቆጣ አነጋገር....ብደነግጥም ምንም ሳልናገር ተከትዬው ወጣሁ....መኪናው ውስጥ እንደገባን....
"ዳይመንድ ትሄጂ ነበር ?" አለኝ
"እእ አዎ እዛ እሰራ ነበር እና ደሞ ከጓደኞቼ  ጋር እዛው እንዝናና ነበር"
"ዳይመንድ ማለት እኮ ሴሰኝነትን ከወንዱ እስከ ሴቱ እንደ ጀብድ እሚቆጥሩበት... የርካሽ ሰዎች መናሀሪያ ነው እንዴት አንቺ እዛ ተገኘሽ...  ደሞስ በዚህ ደረጃ ታዋቂ የሆንሽው በምን ምክንያት ነው  ?" ብሎ በጥያቄ አፋጠጠኝ። መጠየቁ ልክ ሆኖ ሳለ ንግግሩ ትንሽ ከስርዓት የወጣ በመሆኑ ተበሳጨሁ !
"እና እዛ መገኘቴ ርካሽ ለመሆኔ ማረጋገጫ ነው እንዴ ?"
"እንደዛ እያልኩኝ ሳይሆን እዛ ቦታ ትገኛለሽ ብዬ አልጠበኩም ሲቀጥል ደግሞ እነ አቶ ሰለሞን ማለት እኮ እንኳን ዳይመንድ የተገኘች ሴት ቀርቶ መንገድ ላይ ፈገግ ያለችላቸውን ሴት ሳይቀር አልጋ ላይ ይዘው ካልወጡ እንቅልፍ እማይወስዳቸው ሴሰኞች ናቸው" .......ንግግሩን ሳይጨርስ አቋረጥኩት
"ስለዚህ በተዘዋዋሪ ከእነሱ ጋር ማደሬን እየነገርከኝ ነው ?"
"አልወጣኝም ግን ደግሞ ዳይመንድ መሄድሽ ግራ አጋብቶኛል... ጓደኞችሽስ የትኞቹ ናቸው አስተዋውቀሽኝም አሳይተሽኝም አታውቂም የዚህን ያህል የዳይመንድ ፈርጦች እስከመባል ያደረሳችሁ ነገር ምንድነው እውነተኛዋስ ቃልኪዳን ማናት እኔ ያፈቀርኳት ወይስ እነ ሰለሞን ያወሩላት ? መቼስ ዳይመንድ መፅሀፍ ቅዱስ አምብበሽላቸው አደለም የወደዱሽ" ብሎ ንቀት በተሞላበት አነጋገር አፈጠጠብኝ.... ከሱ ያልጠበቁት አወራር ስለሆነ ደርቄ ቀረሁ...
"ምነው እውነት ስለሆነ መልስ አጣሽ አደል" አለኝ
"ታውቃለህ አሁን አንተ ያልካትን ቃልኪዳን እምሆነው መልስ ከሰጠሁክ ነው ! አንድ ነገር ግን ልንገርህ አንተም ብትሆን ዳይመንድ የሄድከው እና የዚህን ያህል ስለ ዳይመንድ ያወከው ለቅዳሴ ሄደህ አይደለም ! አመሰግናለሁ" ብዬ ከመኪናው ወረድኩኝ....

እያለፈ የነበረ የላዳ ታክሲ አስቁሜ ወደ ቤቴ መሄድ ጀመርኩ.....በዚህ ልክ እንዴት ሰውን መገመት ቀላል ይሆናል ? ሳያዳምጡ ሳይጠይቁ ሳያረጋግጡ መፍረድ ቀላል ነው እንዴ ? ስለ እኔ በቅጡ እንኳን ሳያውቅ እንዴት እንዲህ ይናገረኛል.... በርግጥ ስለዳይመንድ ያወራው ሁሉ ልክ ነው ነገር ግን ዳይመንድ መገኘቴ ብቻ እንዴት የኔን ማንነት ያራክሰዋል ..... ቆይ እስር ቤት የገባ ሁሉ ወንጀለኛ ነው እንዴ ?  ቤተክርስቲያን የሄደ ሁሉ ፃድቅ ነው እንዴ ? ....  ሰው በዋለበት እና በለበሰው ነገር ሊገመገም ይገባል ብዬ አላስብም....በየትኛው ንፁህነታችን ነው በሌሎች ጫማ ውስጥ ተቀምጠን ፍርድ እምንሰጠው....ማንም ይሁን ማንም በህይወቱ ስለሚሆነው እና ሰለሚያደርገው ነገር ሊጠይቀውም ሊፈርድበትም እሚገባው የፈጠረው አምላኩ ብቻ ነው ባይ ነኝ።  ማይለፍ በዚህ ልክ አውርዶ ይመለከተኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ከሚፈርድብኝ ቀድሞ እኔ እንዳስረዳው በአግባቡ ቢጠይቀኝ አንድም ሳላስቀር እነገረው ነበር እሱ ግን ቀድሞ ወነጀለኝ።

ይቀጥላል.......

ቀጣዩ ክፍል ከ100❤️ በኋላ ይለቀቃል።

✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
       @Ketbeb_Mender 
       @Ketbeb_Mender 
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯

tgoop.com/Ketbeb_mender/3562
Create:
Last Update:

BY የብዕር ጠብታ✍📒📖

Share with your friend now:
tgoop.com/Ketbeb_mender/3562

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

To edit your name or bio, click the Menu icon and select “Manage Channel.” Telegram channels fall into two types: Choose quality over quantity. Remember that one high-quality post is better than five short publications of questionable value. You can invite up to 200 people from your contacts to join your channel as the next step. Select the users you want to add and click “Invite.” You can skip this step altogether. Telegram desktop app: In the upper left corner, click the Menu icon (the one with three lines). Select “New Channel” from the drop-down menu.
from us

Telegram የብዕር ጠብታ✍📒📖
FROM American