tgoop.com/Ketbeb_mender/3510
Last Update:
♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️
ክፍል ፲፱
✍ደራሲ - አብላካት
ቃል ሳልተነፍስ እየሮጥኩ ወደ ክፍሌ ገባሁኝ። እናቴ እጇን እኔ ላይ ማንሳቷን ለማመን ከበደኝ ፤ መምታቷ እኮ አደለም ያስለቀሰኝ ግን እነሱ የተናገሩትን ከቁብ ሳትቆጥር እኔን መናገሯ ነው ያሳመመኝ። እሷን ሲናገሯት የተከላከልኩላት ፣ ባጣች ሰዓት የደገፍኳት ፣ ባዘነች ሰዓት አለሁሽ ያልኳት እኮ እኔ ነበርኩኝ። እናትነቷን ዘንግተው ቀን ከሌት ክብሯን ዝቅ ለሚያደርጉት ወግና እኔን እነሱ ፊት ማዋረዷ ነው ሀዘኔን ያበዛው። አልጋዬ ላይ ድፍት ብዬ ተንሰቀሰኩኝ ከፋኝ ፤ የእነሱ ንግግር እኮ ለኔ ምንም አልነበረም ለሷ ብዬ ሁሉን እችለው ነበር ግን እሷም ለነሱ ከወገነች ማነው ለኔ እሚያዝነው ? አልቅሼ ቢወጣልኝ ብዬ ያለማባራት አለቀስኩኝ። በድንገት ስልኬ ጠራ ሳየው ማይለፍ ነበር በዚህ ሰዓት እንኳን እሱን ላወራው እራሴን እንኳን ማዳመጥ አልፈልግም ዘጋሁበት በድጋሚ ደወለ ስልኬን እስከመጨረሻው ዘጋሁት። ሳይታወቀኝ እዛው ባለሁበት እንቅልፍ ወሰደኝ። ሊነጋጋ ሲል እንደመባነን አደረገኝና ተነሳሁ....ማንም ሳያየኝ መውጣት ስለፈለኩኝ ልብሴን ቀያይሬ በዝግታ ከቤት ወጣሁኝ.....ግን ወዴት ልሄድ ይሆን አላውቅም ብቻ በዚህ ሰዓት ማንንም ማግኘትም ሆነ ማውራት አልፈልግም ብቻዬን መሆን ነው እምፈልገው። ወደ ስራ ብሄድ ማይለፍን ማግኘቴ አይቀሬ ነው ለዛም ለሰውየው ደውዬ ለሁለት ቀን አስቸኳይ ነገር ገጥሞኝ ከከተማ እንደወጣሁኝ ነገርኩት እግዚአብሔር ይስጠው አልተቃወመኝም። ቀለል እንዲለኝ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ እና እዛ ለረጅም ሰዓት ተቀመጥኩ። ሰላም ተሰማኝ...ድንገት ስልኬ ጠራ ሳየው አቤል ነበር .....
"ቃልዬ"
"ወይ አቤላ እንዴት ነህ ?"
"ደህና ነኝ በሰላም ነው የጠፋሽው ወይስ አስቀይመንሽ ነው ?"
"ኧረ በጭራሽ ያው ስራ ጀምሬ የለ ለዛ ነው"
"ቢሆንስ ከተገናኘን እኮ ቆየን አንቺም ዘጋሽን"
"ይቅርታ አቤልዬ አልመቻች ብሎኝ ነው"
"እሺ አሁን ቁርስ ልንበላ እየወጣን ነው ከተመቸሽ አብረን እንብላ" መሄዱን ባልፈልግም ግን ደግሞ አሁን እምቢ ብላቸው ሌላ ነገር ይመስልብኛል ብዬ "እሺ"አልኩኝ።
"የት ነሽ እንምጣ"
"ሰፈር ቤተክርስቲያን ነኝ"
"መጣን በቃ" ብሎኝ ስልኩ ተዘጋ። ለካ ሳይታወቀኝ ከጓደኞቼ እርቄአለው.... እነሱ እኮ ለኔ ብዙ ሆነውልኛል ሁሌም ከጎኔ ነበሩ ቢያንስ ስልክ መደወል ነበረብኝ። ከደቂቃዎች በኋላ ስልኬ ጠራ አቤል ነው......
"ውጪ በር ላይ ነን" አለኝ። ተሳልሜ ወጣሁኝ ጋቢና ብሩኬ ነበር መኪና የያዘችው ሳቢ ነበረች..... አቤል ከመኪናው ወርዶ ከኋላ አስገባኝ ሁሉንም ሰላም አልኳቸው ሳቢን ሰላም ልላት ስል ግን ዝም አለችኝ.....
"ሳቢዬ ምነው ?"
"ምንም ምነው ?" ጥያቄዬን በጥያቄ መለሰችልኝ....
"ታዲያ ሰላም አትይኝም እንዴ ?"
"እሺ ሰላም ነሽ!" አለችኝ እንደተናደደችብኝ ስለገባኝ ዝም አልኳት።
"እእእ የት ነው እምንበላው ?" አለቻቸው አቤላም ቀጠል አድርጎ.....
"ባለፈው የበላንበት ቤት እኮ አሪፍ ነበር ቦሌ ጋር ያለው"
"አዎ እዛ እንሂድ" አለ ይሳቅ ቀጠል አድርጎ..ለማዋራት ፈራኋቸው። ቦታው ጋር ስንደርስ ከመኪናው ወርደን ወደ ውስጥ ገባን...ሳቢ ልታየኝ እንኳን አልፈለገችም አቤላ ብቻ ነበር ሲያዋራኝ የነበረው.... ብሩክ እና ይሳቅም መናገር አልፈለጉም እንጂ ሊያዋሩኝ እንዳልፈለጉ ያስታውቅባቸዋል። ግራ ሲገባኝ....
"ቆይ እንደዚህ እየሆናችሁ ያላችሁት ስለጠፋሁኝ ብቻ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለ ?" ጠየኳቸው....
"አይ ምንም የለም" አለኝ ብሩኬ ....
"እሺ እንደዚህ እምትሆኑ ከሆነ ለምን ጠራችሁኝ ?"
"እኛ አልጠራንሽም አቤል እንጂ" አለችኝ ሳቢ... በጣም ነበር የደነገጥኩት ...
"ሳቢ አንቺ ነሽ እንደዚህ ያልሽኝ ?"
"ምነው ገረመሽ እንዴ እኔ ወይስ ግልፁን ስለነገርኩሽ ነው። እኔ እንግዲህ እንዳንቺ ማስመሰል አልችልም ይቅርታ" አለችኝ
"ስለምን ማስመሰል ነው ነው እምታወሪው ምን አድርጌ ነው ? ይሳቅ አንተ እንኳን ንገረኝ"
"ቃልዬ ሁለት ቀን እቤት ስንመጣ ሊድያ ነበር የከፈተችው እና አለች ግን ማንም ቢመጣ የለችም በያቸው ብላኛለች ብላ ከበር መለሰችን"
"ማን እኔ ?" አልኩት እንደመደናገጥ ብዬ
"እሱ ብቻ ቢሆን እኮ ጥሩ ነው እኛ እኮ ነን ጓደኞቿ ስንላት ታዲያ በዋናነት ማንን ሆነና ነው እንዳይገቡ ያለችው ማለቷ ነው እኔን የገረመኝ" አለ ብሩኬ ቀጠል አድርጎ....
"እና እሷን አምናችሁ ነው እንደዚህ እምትሆኑት ?"
"ለምን አናምናትም እስከዛሬም ያላመንኳት ይቆጨኛል" አለች ሳቢ...
"ከእኔ እሷን አመንሻት እኔ እኮ ስራ ነው እም ውለው ስራ ባይኖረኝ እንኳን ከመቼ ጀምሮ ነው እኔ እቤት እምቀመጠው ?"
"እሺ እንደዛ ካልሆነ ለምን ስልክ ስደውል አታነሺም መስመሩ ተይዟል ብቻ ነው እሚለው"
"መቼ ደውለሽ ?"
"ኧረ ቃልዬ እኔ እራሱ ብዙ ጊዜ ደውዬልሻለው" አለኝ ብሩኬ......
"ከፍተሽ እዪዋ" አለችኝ.... ስልኬን ከፍቼ ከዚህ ቀደም የተደወሉትን ሳይ ሳቢም ብሩኬም እንዳሉት ደውለዋል ግን ማይለፍን በማዋራበት ሰዓት ነበር። እውነቱን ለመናገር አንዱንም አላየሁትም.....
"እ አሁንስ ልትክጂ ነው ?"
"ሳቢ ፈጣሪ ምስክሬ ነው አንዱንም አላየሁትም እመኑኝ"
"ለነገሩ አታስቢ ለኛም ጥሩ ትምህርት ሆኖናል ከዚህ በኋላ ስልክሽም ላይ አንደውልም ቤትሽም አንደርስም በተለይ እኔ" አለችኝ
"ኧረ በፈጠራችሁ እኔ ከምታወሩት ውስጥ አንዱንም ነገር አላደረኩም እኔ እቤትም ውዬ አላውቅም"
"እስከዛሬ እሚቆጨኝ ሊዲያን አለማመኔ ነው ስላንቺ እስከዛሬ የተናገረችው ሁሉ እውነት ነበር ትላንት ስንገናኝ ስላንቺ እውነተኛ ማንነት ባትነግረኝ አላውቅሽም ነበር"
"ሳቢ እውነት ከእኔ ይልቅ ሊዲያን አመንሻት ?"
"አዎ" አለችኝ......ምድር የተገለበጠብኝ ያህል ተሰማኝ ብድግ ብዬ ከሆቴሉ ወጣሁኝ..... አቤላ ተከትሎኝ ወጣና እጄን ያዞ
"ተረጋጊ ቃልዬ እነሱ ስለተናደዱ ነው" አለኝ
"እቤላ እኔ እኮ ነኝ እንዴት እንደዚህ ትላለች"
" እባክሽን እንደዚህ አትሁኚ ሲገባቸው ይቄጫቸዋል"
"አሁን ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ ካላስቸገርኩህ" አልኩት....
"እሺ ደሞ ክላስ ነገ ነው እሚጀመረው" አለኝ
"እ እሺ"
"እነሱን ላናግራቸው እና ያለሽበት ድረስ እመጣለሁ እሺ" አለኝ
"በቃ ቻው" ብዬው ወደማላውቀው ቦታ መጓዝ ጀመርኩኝ። ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ተሰማኝ...መንገድ ላይ መሆኔ ሳይታወቀኝ በሀይል ጮኩኝ.... አላፊ አግዳሚው እብድ ናት ብሎ ይሆን አሳዝኛቸው ባላውቅም ጥግ ጥጋቸውን ይዘው ያዩኛል።
ይቀጥላል....
ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ......
ለአስተያየት - @Yetomah_Bot
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
BY የብዕር ጠብታ✍📒📖

Share with your friend now:
tgoop.com/Ketbeb_mender/3510