tgoop.com/Ketbeb_mender/3509
Last Update:
♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️
ክፍል ፲፰
✍ደራሲ - አብላካት
የቀረበውን ምግብ በልተን ከጨረስን በኋላ እንሄዳለን ወዳለኝ ቦታ ለመሄድ ብለን ከሆቴሉ ወጣን። መኪና ውስጥ ከገባን በኋላ አንዳንድ ነገሮችን እያወራን ሜክሲኮ የእርሱ ድርጅት ጋር ስንደርስ መኪናውን አቆመው......
"እንዴ እዚህ ምን እንሰራላን ?" አልኩት
" ስንገባ ታይዋለሽ"... ብሎኝ እዛው መኪናው ውስጥ አይኔን በጨርቅ ሸፍኖኝ ከመኪናው ወርደን ወደ ህንፃው ገባን.... ከቆይታ በኋላ ጨርቁን ከአይኔ ላይ ፈታልኝ። ቴራሱ ላይ ነበርን አይኔን ስገልጥ ያየሁትን ለማመን ከበደኝ መሬቱ ሙሉ በሙሉ በአበባ አሸብርቋል መሀል ላይ ጠረፔዛ እና ሁለት ወንበሮች ከጠረፔዛው ላይ ደግሞ መጠጥና ብርጭቆ ተቀምጧላ። ቦታው ከበፊቱ በተለየ ውብ ሆኗል.....ልቤ በጣም ይመታ ጀመር ደስታዬን መቆጣጠር አቃተኝ እና ዘልዬ ተጠመጠምኩበት....አቀፈኝ ጠረኑ ይለያል ከእቅፉ ባልወጣ ምነኛ ደስ ባለኝ...
"ወደድሽው ?" አለኝ በጆሮዬ
"አዎ በጣም ያምራል አመሰግናለሁ" አልኩት እና ወንበሩ ላይ ተቀመጥን። ውስኪውን ከፍቶ በብርጭቆ ላይ ለኔም ለሱም ቀዳና እየጠጣን ጨዋታችንን ቀጠልን......
"ማይለፍ እውነት ለመናገር ይሄንን አልጠበኩም ነበር በጣም ደስ ብሎኛል"
" ዋናው ያንቺ ደስታ እንጂ ይሄ ትንሹ ነገር ነው"
"ብቻ አመሰግናለሁ"
"ምንም አደል"
"እእእ ማይለፍ ቅድም መኪና ውስጥ እምነግርሽ አለኝ ብለህ አልነበር ታዲይ አሁን ንገረኛ" አልኩት
"አይ ተይው ሌላ ጊዜ"
"እንዴ ለምን ምን ተፈጠረ ?"
"ምንም አልተፈጠረም ግን አሁን ብነግርሽ ይሄን ሁሉ ያደረኩት ለዛ ብዬ የመስልሻል"
"በፍፁም እንደዛ አላስብም ይልቅ አሁን ንገረኝ"
"ቃልዬ ምን መሰለሽ...ማለት እኔ አንቺን... አለ አይደል" እያለ ሲርበተበት ንግግሩን ገታ አድርጌ እጆቹን በእጆቼ ያዝኩትና...
"ማለት የፈለከውን በእርጋታ ንገረኝ ለምን ትጨናነቃለህ "አልኩት።
" በቃ ወድጄሻለሁ ማለት ካንቺ ፍቅር ይዞኛል...አውቃለው ረጅም ጊዜ አልሆነንም ግን በቃ እማስበው ካንቺ ጋር መዋል ያስደስተኛል እመኚኝ ከልቤ ነው እምነግርሽ" አለኝ። ይሰማሁትን ላምነው ከበደኝ እምቢ ልበለው እሺ ግራ ገባኝ ግን ደግሞ ወድጄዋለው ላጣውም አልፈልግም ፍርሀቴ አሸንፎኝ እምቢ ብለውና ቢርቀኝ እድሜ ልኬን እፀፀታለው እንዴት ከአፌ እንደወጣ ባላውቅም ግን....
"እኔም አፈቅርሀለው" አልኩት.... ፊቱ ላይ የነበረው ፈገግታ እኔንም ፈገግ አስባለኝ። አመሰግናለሁ አለና ከተቀመጠበት ተነስቶ አቀፈኝ ፤ በዛውም እንደንስ አለኝና አስነሳኝ...ወገቤን ይዞ ወደ እሱ ሲያስጠጋኝ ልቤ ልትወጣ ደረሰች.... ቀስ አድርጎ በእጁ ወገቤን ያዝ አደረገኝ እጄን ትከሻው ላይ ማድረግ አስፈራኝ.... እሱም ስለገባው እጄን በእጁ ይዞ ትከሻው ላይ አደረገውና መደነሳችንን ቀጠልን። ውስጤን የደስታም ፣ የፍርሀትም ስሜት እየተሰማኝ ነው ያለው ለምን እንደሆነ ግን ሊገባኝ አልቻለም አፈቅረዋለው ታዲያ ለምን ይሄ ስሜት ይሰማኛል ለምን እፈራለው ለምን ልቤ የዚህን ያህል ይረበሻል ? ግራ ገባኝ።
አንዳንዴ እኛ ሰዎች የሆነን ነገር እንፈልግና ያ ነገር በእጃችን ሲገባ ግን ያንን ነገር መፈለጋችንን እንጠራጠራለን....የሆነ እሚጨንቅ ስሜት እየተሰማኝ ነው ያለው ....ቸኩዬ ይሆን ? በዚህ ፍጥነት እሺ ማለቴ እሱ ለኔ ያለውን ግምት ያወርድበት ይሆን ? ስለሱ ማንነት ያን ያህል ሳላውቅ ፍቅሩን መቀበሌ ትክክል አይደለም እንዴ ? ምስቅልቅል ያለ ስሜት ይሰማኝ ጀመረ። ከዚህ በላይ መቆየቴ ልክ መስሎ ስላል ታየኝ.....
"ማይለፍ ቅር ካላለህ ወደ ቤት ልሂድ ?" አልኩት...
"ምነው ችግር አለ ?"
"አይ እቤት ለእናቴ ማምሸቴን አልነገርኳትም እና ከዚህ በላይ ከቆየሁኝ ጥሩ አይመጣም"
"ካልሽ እሺ...እንሂድ" ብሎኝ ተነስተን ወጣን። ሰፈር አካባቢ ስንደርስ የለበስኩት ልብስ ትዝ አለኝ በገዛ እጄ እላዬ ላይ ለሚለኩሱት እሳት ክብሪት አቀባይ ሆኜ አረፍኩት። የት ነበርኩ ልባቸው ነው ? አይ እዳዬ አያልቅብሽስ መባል የነበረብኝ እኔ ነበርኩ....
"በቃ ወደቤት ልግባ" አልኩት
"እሺ ስለዛሬው በጣም አመሰግናለሁ ደስ ብሎኛል በጣም"
" እኔም ደስ ብሎኛል አመሰግናለሁ። መልካም አዳር" አልኩት
"እሺ ቃልዬ ሰላም እደሪ" ብሎ ግንባሬን ሳመኝ ደስ እሚል ስሜት አለው......ቻው ብዬው ከመኪናው ወረድኩኝ። አሁን እቤት ምን ብዬ ነው እምናገረው ወይኔ በቃ እየተቀባበሉ ምሽቴን ሊያበላሹት ነው። እሱስ ይበላሽ ለምጄዋለው እናቴ ባልተቀየመችኝ.... ከራሴ ጋር እየተብሰለሰልኩኝ ስራመድ ከኋላዬ "ጃስ" አለኝ ቆሌዬ ነበር የተገፈፈው ማነው ብዬ ስዞር የአማን ነበረ።
"እንዴ አንተ በዚህ ሰዓት እዚህ ምን ትሰራለህ መሽቷል እኮ"
"አስፈቅጄ ነው ጓደኛዬ ቤት እያጠናሁኝ ነበር"
"እስከዚህ ሰዓት የምን ጥናት ነው እንዳይለመድህ" አልኩት
"እሺ በቃ ይቅርታ። አንቺ ግን ከየት ነው አንቺም እኮ አምሽተሻል በዛ ላይ አለባበስሽ ፀጉርሽ እእእ" አለኝ
"እሺ አባትየው ግብዧ ነበረብኝ እዛ ቆይቼ ነው"
"እንግዲህ የነ ሊዲያን ስድብ ቻይው"
"የአማንዬ በእናትህ አንተ ዘዴ አታጣም የት ነበርኩኝ ልበል ?" ትንሽ አሰበና...
"በቃ የብሩክ ልደት ነበር በያቸው እሱን አያዋሩት" አለኝ.....ልክ ነው ብሩክን ብዙም ስለማያውቁት እንደዚህ ካልኩኝ ማንም አይናገረኝም....
"አይ የኔ መልካም ወንድም ምርጥ እኮ ነህ። በል አሁን እንግባ" አልኩትና ወደ ቤት ገባን.....ሳሎን ውስጥ ሁሉም ተቀምጠዋል ገና ሲያዩኝ ከእግር እስከራሴ ድርስ አፍጥጠው ተመለከቱኝ። እማዬም ከጓዳ እየወጣች....
"የኔ ልጅ የት አምሽተሽ ነው እስካሁን ደሞስ አለባበስሽ"..... አለችኝ
" አይ እማዬ የጓደኛዬ ልደት ነበር" ስል ሊዲያ ክትክት ብላ እየሳቀች
"አይን ያወጣ ውሸት ከየት ነው እምታመጭው ከማንም ጋር ስትዳሪ አምሽተሽ እንዲህ ስትል አታፍሪም" አለችኝ.... የሆነ እነቂያት እነቂያት እሚል ስሜት ተሰማኝ...
"አንቺ ታላቅሽ እኮ ነኝ እንዴት እንዴት ነው እምትናገሪው!" አልኳት
"የታላቅ ስነምግባር ሲኖርሽ እኮ ነው እንደ ትልቅ እምትከበሪው ሽርሙጥና እያስተማርሽ መከበር ፈለግሽ " አለኝ ሳሙኤል ቀጠል አድርጎ.....
"ትሰሙኛላችሁ ማናችሁም አያገባችሁም ይሄ የኔ ቤት ነው እንደፈለኩኝ ሆኜ መግባት እችላለው ባባቴ ቤት ማን አዛዥ አደረጋችሁ ስፈልግ ላሶጣችሁ እንደምችል አታውቁም እንዴ ከዚህ በኋላ ሶስታችሁም አንድ ትርፍ ንግግር ስትናገር ብሰማ በፖሊስ አስቀፍድጄ ነው እማሶጣችሁ ተከበሩ!" አልኳቸው.....ይህንን ተናግሬ ዞር ከማለቴ እናቴ በጥፊ አለችኝ.....በድንጋጤ እንዳቀረቀርኩኝ ቀረሁ። እናቴ እኔን መምታቷን ለማመን ከበደኝ.....
"ለካ እንደዚህ ልቅ ነሽ በያ እንግዲህ አሶጪን ጎሽ ያንቺ ቤት መሆኑን ስላሳወቅሽን እናመሰግናለን አንቺን በመውለዴ እፍረት ተሰማኝ" አለችኝ እናቴ።
ይቀጥላል....
ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ......
ለአስተያየት - @Yetomah_Bot
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
BY የብዕር ጠብታ✍📒📖

Share with your friend now:
tgoop.com/Ketbeb_mender/3509