tgoop.com/Islam_and_Science/6344
Last Update:
🎖🎖 #በመፅሀፉ_ከፊል_ታምናላችሁን?🎖🎖
✍ አሚር ሰይድ
አንድ ዕለት ኢማም አህመድ ኢብን ሐንበል በመንገድ ላይ ሲጓዙ አንዲት በሚገባ ሒጃቧን የለበሰች ሴት ይመለከታሉ፡፡ በዚያው ቅፅበት ንፋስ እየተግለበለበ መጥቶ ቀሚሷን ተረከዟ እስኪገለጥ ድረስ ወደ ላይ ያነሳዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ኢብን ሐንበል በመጐናፀፊያቸው ጠርዝ ፊታቸውን በመሸፍን የሚከተለውን ተናገሩ፦
..... #ይህ_የፈተና_ጊዜ_ነው!" አሉ
ተመልከቱ! ይህ ሁኔታ እርሳቸው አስበውት ሳይሆን በአጋጣሚ የተከሰተ ነው፡፡ እንደዚያም ሆኖ ምን ያህል ስሜታቸው እንደተጎዳ ከታሪኩ መገንዘብ አይከብድም፡፡ እኚህ ሰው በአሁነ እኛ ባለንበት ዘመን ቢኖሩ ኖሮ ምን ይሉ ነበር?
✨✨ አንዳንድ ሴቶች እንዲህ የሚሉ አሉ:- "እኔ ሒጃብ ባለመልበሴ ጥፋተኛ ልሰኝ አይገባኝም:: ጥፋቱ ያለው እይታውን መቆጣጠር አቅቶት እኔን በተመለከተኝ ሰው ላይ ነው::የሚሉ በተደጋጋሚ ይሰማል
ይህች ሴት አንድ ማወቅ ያለባት ጉዳይ ለዎችን ለመጥፎ እይታ የምትዳርጋቸው እርሷ ራሷ መሆኗን ነው፡፡
✏️✏️ በተጨማሪ ብዙ ሴቶች እንዲህ ይላሉ - "ዋናውና ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነገር ልብ ነው። ማንም ሰው ለአላህ እውነተኛ መሆን ይኖርበታል። ልባችን ንፁህ ከሆነ ደግሞ ሒጃብ ያን ያክል ወሳኝ ጉዳይ አይደለም፡፡ መሸፈን ያለበት በዋነኛነት ልባችን እንጂ አካላችን አይደለም:: ለምሳሌ እኔ በሌሊት እሰግዳለሁ፡፡ ግዴታ የተደረጉብኝን ሶላቶች ከመስገዴም በተጨማሪ የረመዷንን ወር እጾማለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሒጃብ ማድረግ እያስፈልገኝም ኢማን በልብ ነዉ የሚሉ ለራሳቸዉ ስድነት እንዲመቻቸዉ በኢስላም ላይ ፍልስፍና የሚጨምሩ ሴቶች አልፎ አልፎ እያስተዋልን ነዉ
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ- " የአላህን ሕግጋት በመጠበቅ የሚኖር ማንም የለም አላህ ሁሉንም ጉዳዩን የሚፈፅምለት ቢሆን እንጂ ብለዋል
⚠️ #ሴቶች_ሆይ! አላህ ፊት ቀርባችሁ በፍርዱ ቀን ጌታዬ ሆይ ብዙ መልካም ሥራዎችን ሰርቼና ባወረድከው ሕግ ሁሉ ስመራ በመቆየቴ ይኸው ይበቃኛል። ሆኖም ግን ሒጃብን በተመለከተ እያንዳንዱ ሙስሊም ልቡ ንፁህ እስከሆነ ድረስ ብዙም አያስፈልግም ብዬ አልተገበርከትም ማለት የምትችሉ አይመስለኝም፡፡
አይታወቅምና ምናልባት ይህን ከላይ የቀረበውን አባባል አላህ ፊት ቆማችሁ ለመናገር አስባችሁ ከሆነ ይህን ከዚህ በታችን የተጠቀሰውን የቁርአን አንቀፅ በመጀመሪያ ማስተዋል ሊኖርባችሁ ግድ ነው፡፡
أَفَتُؤۡمِنُونَ بِبَعۡضِ ٱلۡكِتَـٰبِ وَتَكۡفُرُونَ بِبَعۡضࣲۚ فَمَا جَزَاۤءُ مَن یَفۡعَلُ ذَ ٰلِكَ مِنكُمۡ إِلَّا خِزۡیࣱ فِی ٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَاۖ وَیَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ یُرَدُّونَ إِلَىٰۤ أَشَدِّ ٱلۡعَذَابِۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَـٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ
በመፅሐፉ ከፊል ታምናላችሁን? በከፊሉም ትክዳላችሁን? ከእናንተም ይህንን የሚሠራ ሰው ቅጣት በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡(አል-በቀራህ85)
👌ማስተዋል ያለብን አብዘሀኛዉ ሴቶች ፀጉራቸዉን በከፊል የሚያሳዩ የተወሰነ ክፍሉን የሚያሳዩ አሉ....ይህም አስተካክሎ ሂጃብ ያለመልበስ ነዉ፡፡
የሂጃብን ትርጉም በቅጡ ያልተረዱ ፀጉራቸዉን ያሳያሉ...ሂጃብ ከፀጉር ጫፍ እስከ እግር ጥፍር መሆኑን አንዘንጋ
ትክክለኛ ሒጃብ ለሙስሊም ሴት ዉበት ኩራት ነዉ!!!
4 another channal👇
www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6344