ISLAM_AND_SCIENCE Telegram 6341
[ ሁለቱ ፆታዎች: ሲሄዱ ]

ወንዶች በቃን ለማለት ይፈጥናሉ .... ሁሌም ግን ተመልሰው ይመጣሉ

ሴቶች ያስባሉ፣ አብዝተው ያስባሉ፣ ያለቅሳሉ፣ ይቀወር ይላሉ .... መቆየት ከሚገባቸው በላይ ይቆያሉ። ቆርጠው ከሄዱ .... አይመለሱም

{ ለምን ? }

ወንድ ልጅ በቃኝ ብሎ ሲሄድ ብዙ ጊዜ በድንገት ነው ... ስሜታዊ ሆኖ ነው። ክብሬ ተነካ፣ ተደፈርኩ ወይም ተናደድኩ በሚል መነሻ ለመሄድ ሲወስን ቀድሞ የሚታየው "ከእሷ የተሻለ" ሞልቶ ምን አንገበገበኝ የሚል ነው። ነገሮች እንዳሰቡት አልጋ በአልጋ አለመሆኑን የሚያየው "በቃኝ" ብሎ ከወጣ በኋላ ነው። ያኔ ገፍቶ የሄደውን ምቾት፣ ታማኝነት፣ እንክብካቤ፣ ልመና እና ልምምጥ፣ ማንም የማይታገሳቸውን ፀባዮቹን የታገሰችውን ሴት ይናፍቃል። ይኼኔ አይኑን በጨው አጥቦ ከለሊቱ 8 ሰዓት ላይ " እንዴት ነሽ .... ጠፋሽ" ብሎ መልዕክት ይልክልሻል።

በምሳሌ እንየው

አየለ ምርጥ የሴት ጓደኛ ነበረችው ... አየለች። የተከራየበት ቤት ድረስ ቤቱን አፅድታለት፣ ልብሱን አጥባ፣ ምግብ ሰርታ ... የወደፊት አላማህ ምንድነው ስትለው "ቤቲንግ በልቼ ሀብታም መሆን" ሲላት አንጀቷ እያረረ "ይቅናህ" ብላ ታግሳ እየኖረች ያለች ...

የሆነ ቀን በአሳብ አለመግባባት ይመጣል። አየለ ቱግ ይላል .... ሁለተኛ ቤቴ እንዳትደርሺ ብሎ ክብረ ቢስ በሆነ መልኩ ሰድቦ የቤቱን ቁልፍ ቀምቶ ያባራታል። ከሁለት እና ሶስት ወር በኋላ አብረውት ሲዘሉ ስለከረሙት ሴቶች ማሰብ እና ማስተዋል ይጀምራል። የከበቡት ሴቶች እሱ ጋር ለመምጣት ኮንትራት ታክሲ ቤታቸው ድረስ እንዲላክላቸው የሚጠብቁ፣ ሲመጡ ቅንጡ ሆቴል ወስዶ እንዲጋብዛቸው የሚፈልጉ፣ ፍላጎታቸው በየምሽት ክለቡ እየዞሩ መጨፈር እና መዝናናት ብቻ መሆኑን እና ከእሱ ጋር የሚቆዪት የተሻለ ብር ያለው እስኪመጣ መሆኑን ይረዳል። ይኼኔ አየለች ጋር ስልኩን አንስቶ ይደውላል። ስልኩ አይሰራም .... አየለች ሲም ቀይራ፣ እራሷን ከነበረችበት የፍቅር ግንኙነት ለማራቅ ትግል ውስጥ ናት። አሁን ሄዳለች ... ላትመለስ።

ሴቶች ዝም ብለው፣ ብድግ ብለው፣ ከመሬት ተነስተው .... አይሄዱም። መጀመሪያ በስሜት መራቅ ይጀምራሉ። በዝምታ ውስጥ .... ስሜት አልባ መሆን ያስቀድማሉ። በጊዜ ሂደት  ..... መጨቃጨቅ፣ መወትወት፣ ነገሮችን ማስታወስ፣ ቅሬታን ማንሳት፣ እንዲህ ሁን እንዲህ አድርግ .... ማለት ያቆማሉ። ዝምታ ያበዛሉ .... ነገሮች ተስማምቷቸው ሳይሆን በአይምሮአቸው የመውጫ በሩ ግማሽ ላይ ደርሰው ነው። በሩን አልፈው የወጡ ጊዜ .... በህሊናቸው፣ በአይምሮአቸው፣ በልባቸው እና በነፍሳቸው ካንተ እርቀው ከሄዱ ሳምንታት ምናልባትም ወራት ሆኗቸዋል።

ያለፉትን አምስት አመታት አንድም ቀን ተግብረኸው የማታውቀውን ቃልህን በተስፋ እየጠበቀች፣ ውሸቶችህን ሁሉ ይቅር እያለች፣ ግማሽ እውነቶችህን እየተቀበለች .... ጢባጢቤ ስትጫወትባት ችላ ኖራለች። ካንተም ብሶ በቃኝ እያልክ እየሄድክ ስትመለስ ምንም እንዳልተፈጠረ ስትቀበልህ ቆይታለች። ያልገባህ ነገር በየቀኑ እየሸራረፍካት እንደነበረ ነው። የሆነ ቀን መከራከር ታቆማለች። እንደዘበት ትተውሀለች። ሁለነገሯን ጠቅላላ ከህይወትህ ውልቅ ትላለች። ልብህ አብጦ "የራሷ ጉዳይ" ... "ለምናኝ ትመለሳለች" ብለህ ታልፈዋለህ። ጊዜው ሲነጉድ ግራ ትጋባለህ .... እንደምንም ደፈር ብለህ ትደውላለህ .... ስልኳን ቀይራለች። ላትመለስ ሄዳለች።

ሴት ትታገሳለች፣ ሴት ብዙ ትችላለች .... ሲበቃት ግን ድምፅ አታሰማ፣ ድራማ አትሰራ .... በዝምታ ውልቅ ነው። መመለስ አይደለም ወደኋላ ዞራ አታይም።

የትም አትሄድም ጨዋታ ላይ ከሆንክ .... አንደምን አደርክ: አንድ ቀን ትሄዳለች፥ ደግሞም አትመለስም። ስትሄድ ደግሞ የምትዝረከረክ፣ የማይመቻት፣ የምትጎሳቆል ከመሰለህ .... እንደምን አመሸህ: ሰላሟን ይዛ፣ ክብሯን ጠብቃ፣ የፀጉር አሰራሯ ሁሉ "ይሄንን ከንቱ ሲጀመር ምን ስሆን አፈቀርኩት" የሚል መልዕክት እንዲሰጥህ አድርጋ ነው።

                    © Abby Junior

💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group

tgoop.com/Islam_and_Science/6341
Create:
Last Update:

BY ISLAMIC SCHOOL

Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6341

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

On June 7, Perekopsky met with Brazilian President Jair Bolsonaro, an avid user of the platform. According to the firm's VP, the main subject of the meeting was "freedom of expression." On Tuesday, some local media outlets included Sing Tao Daily cited sources as saying the Hong Kong government was considering restricting access to Telegram. Privacy Commissioner for Personal Data Ada Chung told to the Legislative Council on Monday that government officials, police and lawmakers remain the targets of “doxxing” despite a privacy law amendment last year that criminalised the malicious disclosure of personal information. A new window will come up. Enter your channel name and bio. (See the character limits above.) Click “Create.” best-secure-messaging-apps-shutterstock-1892950018.jpg Healing through screaming therapy
from us

Telegram ISLAMIC SCHOOL
FROM American