tgoop.com/Islam_and_Science/6340
Last Update:
🎖🎖=========== #ሃያእ========🎖🎖
✍ አሚር ሰይድ
ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል- 'ሃያእና ኢማን አንዱ ከሌላዉ ጋር የተጠላለፉ ናቸው። እንድ ሰው እንዱን ካጣ ሌላውንም ማጣቱ አይቀርም፡፡*
☞ ኢምራን ኢብን ሁሴን (ረ.ዐ) ባወሩት ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ኢስላማዊ ሃፍረት (ሃያእ) የሚያመጣው ነገር ሌላ ሳይሆን ጥሩነትን ነው፡፡''
☞እንደገናም በሌላ ሐዲስ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ሃያእ የሚመጣው ከኢማን (እምነት) ነው፡፡ እምነት ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስድነት (ባለጌነት) ከክህደት የሚመነጭ ሲሆን ክህደት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል፡፡
☞ #የኢማም_ማሊክ መወጠእ ኪታብ ላይ የተጠቀሰ
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “እያንዳንዱ ሃይማኖት የየራሱ የሆነ ተፈጥሮኣዊ ባህሪያት አሉት፡፡ የኢስላም ተፈጥሮአዊ ባህሪ ሃያእ ነው፡፡"
⚡️⚡️⚡️ አዒሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ብላለች
"የአላህ መልዕክተኛ ﷺእንዲሁም አባቴ አቡበክር (ረ.ዐ) በቤቴ አንድ ጥግ ላይ ተቀበረው እያሉ በቤት ውስጥ እንደልቤ ተገላልጬ እቀመጥ ነበር። ሆኖም ግን ከጊዜ በኋላ ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) ሞተው ከእነርሱ ጐን ሲቀበሩ ለእርሳቸው ከነበረኝ ሃያእ የተነሳ በቤቴ ውስጥ እያለሁም እሸፋፈን ነበር፡፡ የምሸፋፈነዉ ኡመር (ረ.ዐ) ሙት መሆናቸውን እያወቅኩ ነው... ግን እሷቸዉ ቢሞቱትም ቀብራቸዉ ከነብዩ ﷺ ቅርብ ስለሆነ ነዉ ብላለች
፡፡
⚠️ግን እኛስ የሀያእ መጠናችን ምን ያህል ይሆን???
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6340