ISLAM_AND_SCIENCE Telegram 6316
😍#ረሒማ_የእዝነት_የእውነተኛ_ፍቅር_አርዓያ 😍
                  ✍🏼አሚር ሰይድ

   ይህ ፁሁፍ እስከመጨረሻዉ ድረስ አንብቡት የአንተ ቤት ዉስጥ ያለችዉ ሚስትህ የተወሰነም ቢሆን እንደ ረሒማ ትሆናለች ወይ??ልታገባት ያሰብካት ከረሒማ አንፃር እንዴት ናት??አንቺስ ለባልሽ እንደ ረሒማ ነሽ??ያላገባሽ እህቴ ለወደፊት ባልሽ እንደ ረሒማ ለመሆን ከአላህ ጋር ያለሽ ግንኙነት ምን ያህል ነዉ??

  🎖🎖 ነብዩሏህ አዩብ ዐሰ ለ80 አመታት ያክል ተድላና ደስታ የሰፈነበት ህይወት መርተዋል፡፡14 የሚሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆች የነበሯቸዉ ሲሆን በቤተ ዘመድና በመንደራቸዉ ሰዉ እየታጀቡ ያማረ ህይወት አሳልፈዋል፡፡
        አላህ (ሱ.ወ) አዩብን (ዐ.ሰ) መፈተን በፈለገ ጊዜ መጀመሪያ ገንዘባቸውን ነጠቃቸው፡፡ ጎርፍ በጎቻቸውን ወሰደባቸው:: ቀጥሎ ደግሞ ኃይለኛ ንፋስ አዝርዕቶቻቸውን አወደመባቸው:: ሸይጧን ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ወደ አዩብ (ዐ.ሰ) እየተጣደፈ መጣ፡፡ እያለቀሰ😞የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፡፡

አዩብ ሆይ! ትልቅ አደጋ ተፈጥሯል፡፡ ሀብት እና ንብረትህ በሙሉ እንዳልነበር ሆኗል!..

አዩብ (ዐ.ሰ) በሰሙት ዜና ምንም ሳይደነግጡ አላህን አመስግነው ተረጋግተው በሰው ተመስሎ ወደ መጣው ሸይጧን በመዞር እንዲህ አሉት፦

«ሀብትና ስልጣን የሰጠኝ አላህ (ሱ.ወ) አሁን መልሶ ወሰደው፡፡ ሀብትም ይሁን ስልጣን የርሱ እንጂ የሌላ የማንም አይደሉም፡፡ ሲፈልግ ይሰጣል፣ ሲፈልግ ይወስዳል አሉት፡፡ ይህች መልሳቸው እና ፍፁም እርጋታቸው ሸይጧንን አበሳጨ፡፡

    ከዚህ ሁሉ በኋላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈጠረ፡፡ በአደጋው  የአዩብ (ዐ.ሰ) ልጆች ሞቱ፡፡ ሸይጧን እንደገና ተመልሶ ወደ አዩብ እያላዘነ መጣ፡፡ ዓይኖቹ በእንባ እየታጠቡ፡፡

“አዩብ ሆይ! አላህ ቤትህን በመሬት መንቀጥቀጥ አፈረሰብህ፤ ህፃን ልጆችህን ነጠቀህ፡፡ ዋይታ እና ጩኸታቸው የማንንም ልብ የሚሰብር ነበር፡፡ በእውነት ማንም ሰው ሊሸከመው የማይችል አደጋ ነው የደረሰባቸው::.

የሸይጧን ትረካ ልብ የሚያምስ ዓይነት ነበር፡፡ አዩብ (ዐ.ሰ) ተንሰቅስቀው አለቀሱ😢፤ በጣም አዘኑ፡፡ ይሁን እንጂ ብዙም ሳይቆዩ ራሳቸውን በራሳቸው አፅናንተው ትልቅ ትዕግስት በመላበስ መለኮታዊውን ውሳኔ በፀጋ መቀበላቸውን ገለፁ፡፡

የተንኮል መረቡ ያልያዘለት ሸይጧን በጣም ተናደደ😡፡፡ ሌላ ነገር ሊናገር ሲያስብ ሰይዱና አዩብ (ዐ.ሰ) ቀደሙት፡-

“አንተ እርጉም! በጌታዬ ላይ እንዳምፅ ትገፋፋኛለህ?? ዕወቅ፣ ልጆች ከአላህ (ሱ.ወ) የተቀበልኳቸው አደራዎች ነበሩ፡፡
#አደራ_አስቀማጩ_አደራውን_ወሰደ፣ሌላ ምንም አልተፈጠረም፤ ሰጪ እሱ ነው፤ ወሳጅም እሱ፤ ታዲያ ለምን አዝናለሁ? እኔ በየትኛውም ሁኔታ ለጌታዬ አመስጋኝ ባሪያው ነኝ!..አሉት

    አዩብ (ዐ.ሰ) የመጨረሻው ፈተና ቀረበላቸው፡፡ በከባድ በሽታ ተይዘው ወደቁ፡፡
#ከውድ_ባለቤታቸው_ረሒማ ውጭ ሁሉም ሰው በሽታዉ ወደ እኛ ይተላለፋል ብለዉ ካጠገባቸው እስኪርቅ ድረስ በጠና ታመሙ::ቆዳቸዉ እየተቀረፈተ መዉደቅ ጀመረ ከቤት ጭራሸሸ መዉጣት አይቻል ሆነ፡፡

   😍 ረሒማ የእዝነት ተምሳሌት! የእውነተኛ ፍቅር እና ደግነት አርዓያ ሆነች:: የዕለት ጉርሳቸውን ለመሸፈን ደፋ ቀና ማለት ጀመረች፡፡

ያለመሰልቸት ሰይዱና አዩብን (ዐ.ሰ) ተንከባከበቻቸው፡፡ ነቢዩ አዩብም (ዐ.ሰ) ቢሆኑ በመታመማቸው አላማረሩም ነበር፡፡ ወደ አላህ (ሱ.ወ) ብቻ ተጠጉ፡፡ ትእግስት አደረጉ፡፡ ምላሳቸው ከምስጋና እና ከውዳሴ አልቦዘነችም፡፡ ነቢያዊ አደብ አሳዩ፡፡ ሕመማቸውን ወደ ሸይጣን አስጠጉት

{ وَٱذۡكُرۡ عَبۡدَنَاۤ أَیُّوبَ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥۤ أَنِّی مَسَّنِیَ ٱلشَّیۡطَـٰنُ بِنُصۡبࣲ وَعَذَابٍ }
ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡(ሷድ 41)

     ሸይጣን አለቅጥ በገነ፡፡ እርጋታቸው አንገበገበው: ሌላ ችግር ሊጨምርባቸው ከጀለ፡፡ አዩብ (ዐ.ሰ) ግን ሁሉም ከአላህ (ሱ.ወ) እንደሚመጣ ያውቁ ነበርና ለውሳኔው እጅ ሰጥተውና በእርሱ ፍፁም ተመክተው ይኖሩ ነበር።

አዩብን (ዐ.ሰ) ለመወስወስ ያደረገው ጥረት ሁሉ ከንቱ የቀረበት ሸይጣን ሰዎችን መወስወስ ጀመረ፡፡

«ንቁ! አንድም ሰው ረሒማን እንዳያገኛት፡ ማንም ሰው የእርዳታ እጁን እንዳይዘረጋላት፡፡ አለበለዚያ የአዩብ በሽታ ይተላለፍባችኋል፡፡ እንዲያውም ከከተማዋ ብታባርሯት መልካም ነው› እያለ ቀሰቀሳቸው።

......ሰው ሁሉ በሸይጣን ውትወታ ተረታ። ተሰባስበው ወደ ረሒማ ሄዱ

‹‹ባልሽን ይዘሽ ከዚህ አካባቢ ጥፊ! አለበለዚያ እስክትሞቺ ድረስ እንወግርሻለን› በማለት ዛቱባት፡፡

     ረሒማ ሌላ ምርጫ አልነበራትም😔፡፡ አዩብን (ዐሰ) #በጀርባዋ_ተሸክማ_ሠፈሩን_ጥላ_ሄደች፡፡ ከከተማዋ ውጭ ቦታ ፈልጋ አረፈች:: ከአሸዋ አልጋ ሰራችላቸዉ..የዲንጋይ ትራስ አደረገችላቸዉ..ቀጥላ ትንሽ ጎጆ ቀለሰች፡፡ አዩብን (ዐ.ሰ) ለማገልገል ከጎናቸው ተቀመጠች::

ታጋሹ የአላህ ነብይ አዩብ (ዐ.ሰ) በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንኳ የነብይነት ኃላፊነታቸውን ይወጡ ነበር፡፡ ለሚመጣ ለሚሄደው ሁሉ መልዕክታቸውን ያደርሱ ነበር፡፡ በመልካም በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል ዲናቸውን ያገለግሉ ነበር፡፡

   ሚስታቸዉ ረሒማ በበኩሏ ጥጥ እየፈተለች ለከተማዋ ሴቶች በማቅረብ ኑሯቸውን ትደግፍ ነበር፡፡ በሰዉ ቤት እንደ ሰራተኛ ሆና በማገልገል የምታገኘዉን እያመጣች ለ18 አመት ያህል አስታመቻቸዉ
በሌላ ዘገባም የችግራቸዉ ብርታት ፀጉሯን ላጭታ ሽጣለች የሚልም አለ፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ረሒማ  ወደ አዩብ (ዐ.ሰ) በመሄድ እንዲህ አለቻቸዉ፡-

እንተ ነብይ ነህ! ጤናህን እንዲመልስልህ አላህን ብትጠይቀው ምን አለበት??አለቻቸዉ

......አዩብም (ዐ.ሰ) እንዲህ በማለት መልሰው ጠየቋ:-
«በሰላም እና በጤና ስንት ዓመታት ኖርን

......"ሰማንያ ዓመታት..

«ችግሬን አቅልልኝ ብዬ ለመጠየቅ እፈራለሁ! ምከንያቱም ይህን ሁሉ ጊዜ ሰማንያ አመት በድሎት አኑሮኛል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ተቆጥሮ የማይዘለቅ ፀጋ ሰጥቶናል፡፡ ታዲያ ከእርሱ የመጣችውን ትንሽ ችግር ብታገስ ይሻለኛል...ታግሼ ሳልቆይ ይህን እንዲያደርግልኝ አለምነዉም አሏት፡፡

  አዩብን (ዐ.ሰ) በመወስወስ ተስፋ የቆረጠው ሸይጧን አሁን ደግሞ ወደ ረሒማ ሔደ፡፡ ግማሽ አካሉን ብቻ ገልጦ ከፊት ለፊቷ መጣ፡፡ አዕምሮዋን ለማጭበርበር ሞከረ፡፡ ለአዩብ (ዐ.ሰ) የገጠማትን ስትነግራቸው:- “አንቺ እመቤት! መንገድ ላይ የገጠመሽ ሰይጣን ነው፡፡ ተጠንቀቂው፡፡ ከእኔ እንድትለይ ለማድረግ ይጥራልና ንቂ!›› በማለት አስጠነቀቋት፡፡

ረሒማ የዩሱፍ (ዐ.ሰ) ዘር ነበረች፡፡ ይህም ከዩሱፍ (ዐ.ሰ) ማራኪ ውበት ጥቂትም ቢሆን ለመጋራት አብቅቷታል፡፡ በአካባቢው በውበት የምትስተካከላት አንዲት እንስት አልነበረችም፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ወደ እሷ ሲመጣ በማራኪ አለባበስ ተውቦ ነበር፡፡ እንዲህ አላት፡-

«የዚህ አካባቢ ነዋሪ ነኝ፡፡ የናጠጥኩ ሀብታም ስለሆንኩ ሁሉም ያውቀኛል፡፡ እዚህ አካባቢ እንዳንች ዓይነት ቆንጆ አይቼ አላውቅም፡፡›› አላት
የዛሬ ሴት ብትሆን ኮብልላ ነበር ወዳጄ☺️

የልብ ፍቅር ባለቤት ረሒማ ግን ፈጥና ወደ ጌታዋ ተጠጋች፡፡ እንዲህ አለችው፡-👇👇👇

tgoop.com/Islam_and_Science/6316
Create:
Last Update:

BY ISLAMIC SCHOOL

Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6316

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Just at this time, Bitcoin and the broader crypto market have dropped to new 2022 lows. The Bitcoin price has tanked 10 percent dropping to $20,000. On the other hand, the altcoin space is witnessing even more brutal correction. Bitcoin has dropped nearly 60 percent year-to-date and more than 70 percent since its all-time high in November 2021. During a meeting with the president of the Supreme Electoral Court (TSE) on June 6, Telegram's Vice President Ilya Perekopsky announced the initiatives. According to the executive, Brazil is the first country in the world where Telegram is introducing the features, which could be expanded to other countries facing threats to democracy through the dissemination of false content. The public channel had more than 109,000 subscribers, Judge Hui said. Ng had the power to remove or amend the messages in the channel, but he “allowed them to exist.” SUCK Channel Telegram ‘Ban’ on Telegram
from us

Telegram ISLAMIC SCHOOL
FROM American