tgoop.com/Islam_and_Science/6305
Last Update:
🎖🎖 #የሀቢቡና_ሙሀመድ_ﷺ_ስሞች🎖🎖
✍ አሚር ሰይድ
ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ በአባታቸው በኩል የሚገርም ታሪክ አላቸው። አያታቸው ዐብዱልሙጠሊብ ጁርሁም የሚባሉ ጉሳዎች የዘምዘምን ውሀ አዳፍነው በሄዱ ጊዜ ውሀዉን ፍለጋ ቁፋሮ ጀመሩ። ቁረይሾች በዚህ ሥራ ላይ ሊተባበሯቸው አልፈቀዱም። ዐብዱል ሙጠሊብ አንድ ወንድ ልጅ ብቻ ነበራቸውና ጌታዬ ሆይ አሥር ወንድ ልጆችን ከሰጠኸኝ አንዱን በስለት መልክ ላንተ ለማረድ ዝግጁ ነኝ በማለት ተሳሉ። አላህ ሱወ አስር ወንድ ልጆች ሰጣቸው። የመጨረሻ ልጃቸው የነቢያችን ﷺ አባት የሆኑት ዐብዱላህ ናቸው።
ዐብዱልሙጠሊብ በስለታቸው መሠረት
የነብዩ ﷺ አባት ለማረድ ወደ ካዕባ ወሰዱ። በዚህን ጊዜ ቁረይሾች ዐብዱል ሙጠሊብን በኛ መካከል ያልነበረ ባህል አታምጣብን። አንተ ዛሬ ይህንን ልጅህን ካረድክ ነገ ሌሎችም ይህን ነገር ልምድ አድርገው ይከተላሉና ይህን ሀሳብህን አንሳ በማለት አሳሰቡት። በዚሁ ጉዳይ ላይ ለማማከርም ብለው ከአንዲት ጠንቋይ ዘንድ ሄዱ። ጠንቋዩዋም የአንድ ሰው የደም ካሳ አስር ግመል ነውና ለእርድ በቀረበው ዐብዱላህና በግመሎቹ መካከል እጣ ተጥሎ የግመሎቹ እጣ በደረሠ ጊዜ ግመሎቹ በሱ ምትክ እንዲታረዱ መከረችና እጣ መጣል ተጀመረ። እጣው ከዘጠኝ ጊዜ ሙከራ በኋላ ነበር ግመሎቹ ላይ ወጣ። እጣው በግመሎቹ ላይ በመውጣቱ ዐብዱልሙጠሊብ እጅግ ተደሠቱ። መቶ ግመሎችም በዐብዱላህ ምትክ ቀርበው ታረዱና ሰደቃ ተደረጉ። የነቢያችን አባት ዐብዱላህ በዚህ መንገድ ነፃ ሊወጡ ቻሉ።
✨✨✨ ነቢዩም ﷺ ይህንኑ ክስተት ሲያስታውሱ እኔ የሁለት ለእርድ የቀረቡ ሰዎች ልጅ ነኝ ብለዋል። አንደኛው ለእርድ ቀርቦ የነበረው ሰው ቅድመ አያታቸው ነቢዩ ኢስማዒል እንደሆኑ ይታወቃል።
💚 የሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ ለአባታቸው.... ዐብዱልሙጠሊብ ከተከበረ ቤተሰብ የሆነችው አሚናን ከእርድ ለተረፈ ልጃቸው ለዐብደሏህ አጩ። በወቅቱ የነበረው ማህበረሰብ የጋብቻ ሥርዓቱ የተበከለ ዝሙትና አባታቸው የማይታወቁ ልጆች የበዙበት ነበር። የነቢያችን ﷺ አባት ግን በሕጋዊ ጋብቻ በክብር የሴቷ ቤተሰብ ተጠይቆ ነው የተዳሩት።
🩷 ነብዩ ﷺበእርግዝናቸው ወቅት አንድ ፍጡር ወደ እናታቸው መጣና በዚህ ዑማ ታላቅ ሰው ነውና ያረገዝሽው ይህን ልጅ በምትወልጂበት ጊዜ በአንድዬ ጌታ ከምቀኛ ዓይን ሁሉ እጠብቅሀለሁ" በይ።” አላት። እናታቸው አሚና ነቢዩን ﷺ ነፍሰጡር ሆና ሳለች ሌሎች ሴቶች የሚሰማቸው የድካም እና ሌሎች ዓይነት ስሜቶች ተሰምቷት አያውቅም ነበር።
🌹🌹🌹ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ስትወልዳቸውም ከሷ የወጣ ብርሃን የሻምን ቤተ-መንግሥታት አብርቷል።
ነቢያችን ﷺ እንብርታቸው ተስተካክሎ የተቆረጠ ሆኖ፣ ዐይናቸው ተኩሎና፧ ተገርዘው ነው ወደዚህች ዓለም ተውበው የመጡት። በዉልደታቸው ቀን የፐርሺያ ነገስታት ማረፊያ የተሠነጣጠቀ ሲሆን አሥራ አራት የሚሆኑ የቤተ- መንግሥቱ ጉልላቶቹ ወድቀዋል።
🌿🌿 ለ1ሺህ ዓመታት ሳትጠፋ የኖረችው የእሳት አምላኪዎቹ ፋርሦች እሳትም በዚሁ ቀን ጠፍታለች። በሚወለዱበት ጊዜ ቤቱ በብርሃን ተሞላ።ከዋክብት ወደሳቸው ሲቀርቡ ሁለቱ አዋላጆቻቸው በግልፅ ተመልክተዋል። አላህ(ሱወ) ታላቁንና የነቢያት ሁሉ መቋጫ የሆነውን መልዕክተኛውን ሙሐመድን ﷺ
በነኝህና በመሳሰሉት ተዓምራት አጅቦ ነው ወደዚህች ዓለም ያመጣቸው።
🩵🩵 ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ በርከት ያሉ ስሞች አሏቸው። በዋናነት የሚጠቀሱት እሳቸውም የመሰከሩት አምስት ናቸው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል
➊‹‹ እኔ ሙሐመድ ነኝ።
➋ እኔ አሕመድ ነኝ።
➌ እኔ 'አል ማሒ' (አላህ በኔ አማካኝነት ክህደትን የሚያብስበት) ነኝ።
➍እኔ አል ሓሽር (ሰዎች የቂያማ ቀን ከእግሬ ሥር የሚቀሰቀሱ) ነኝ።
➍እኔ 'አል ዓቂብ (የነቢያት ሁሉ መቋጫ) ነኝ።” ብለዋል።
🌹🌹ሙሐመድ ማለት ትርጉሙ 'ምስጉኑ፣ የተመሰገነ' እንደ ማለት ነው፡፡ ይህን ስም ያወጡላቸው አያታቸው ዐብዱልሙጠሊብ ናቸው። በርግጥም የሰው ልጅ ሆኖ እንደሳቸው የተመሰገነ የለም። አሕመድ ማለት ደግሞ ትርጉሙ “አመስጋኝ ማለት ሲሆን በርግጥም ከሳቸው በላይ አላህን ያመሰገነና የተገዛ በዚህች ምድር ላይ አልተፈጠረም።
አላህ ሱወ ነቢዩን ሲያልቃቸው እሳቸው መለኮታዊውን ተልእኮ ይዘው በመጡ ጊዜ ያስዋሿቸው የመካ ሰዎች ቁረይሾች እንኳን ሲሰድቧቸው በስማቸው ጠርተው ሰድበዋቸው አያውቁም ነበር። ሙሐመድ ከማለት ይልቅ ተቃራኒ ትርጉም ባለው መጠሪያ ሙዘምመም እያሉ ነበር የሚጠሯቸው። ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ አታዩም እንዴ! አላህ የቁረይሾችን ስድብ እንዴት እንደሚያርቅልኝ! እነሱ እኮ ሙዘምመም እያሉ ነው የሚሳደቡት እኔ ግን ሙሐመድ ነኝ' ይሉ ነበር፡፡
🌹🌹 ታላቁ ነቢይ ﷺ አባታቸውን ገና በእናታቸው ሆድ ሳሉ እናታቸውን ደግሞ በሕጻንነት እድሜያቸው ነው ያጡት። ወንድምና እህት አልነበራቸውም።
ነቢያችን ﷺ የቲም ሆነው በአያታቸውና በአጎታቸው ቤት ነው በቅብብሎሽ ያደጉት። ልጅ ሆነው ሣሉም ሆነ በወጣትነታቸው ታላቅ ሰው ነበሩ። መለኮታዊው የወሕይ መልዕክት ሳይደርሳቸው ከመላካቸውም በፊት ስብእናቸው ምሉእ ነበር። ቁርኣን ስለ ታላቅነታቸውና ስለ ደረጃቸው ከመመስከሩ በፊት ታላላቅ ተአምራት በሳቸው ዙሪያ ይታዩ ነበር።
✏️✏️ ከመላካቸው በፊት ድንጋይ ሰላም ይላቸው፤ ዛፍና ሌላ ግዑዝ ነገርም የአክብሮት ስግደት ይሰግድላቸው ነበር።
በወጣትነታቸው መካ እንደሳቸው ዓይነት እውነተኛና ታማኝ ሰው አላስተናገደችም። ብዙዎች የአደራ እቃዎችን እሳቸው ዘንድ ያስቀምጡ ነበር። “ሙሐመዱ አል- አሚን" (ታማኙ ሙሐመድ) ነበር መጠሪያቸው። ጣኦታትን እና ባእድ አምልኮን እጅግ አድርገው ይጠሉ ነበር።
🩵ሀቢቡና ﷺﷺﷺ
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6305