tgoop.com/Islam_and_Science/6210
Last Update:
እኔ በአይኔ ሁለት ልጆች ወልደው አይቻለሁ፡፡»የላይኛዉ ምንጭ መፅሀፍ ገፅ 54
🔰 እቴጌ ገረመዉ ባዘጋጀችዉ የጭን መነባንብ በሚለዉ መፅሀፏ ገፅ 98 ላይ እንዲህ ብላለች
«የኮሌጅ ተማሪዎች ድብቅ እውነታዎች ባሕር ዳር፦ የሀገራችን ተማሪዎች ከሚታሙባቸው የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች ይማግጣሉ ከሚባሉት ከተማ እንደመሆኗ ለመታዘብ ቸኮልን፡፡ ወሲብ ንግድ ያጧጡፋሉ የተባለላቸውን ተማሪዎቻችን አመሸሽ ለመቃኘት የሚባለውን ነገር ለመታዘብ አንድ ቤት ከ30ደቂቃ በላይ መቆየት እያስፈልግም::ግን ይህን የሚያዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ አፎን ከፍተው ሲመለከቱ ሊመሽብዎት ይችላል፡፡
የአብዛኞቹን የሴት ልጆች አለባበስ የቡና ቤት ሴቶችም ሲሞክሩት የምንሸማቀብበት አይነት ነዉ፡፡እጆቻቸዉ እግሮቻቸዉ ሁሉ ስራ የበዛባቸዉ ናቸዉ፡፡ በአንድ እጅ ሲጋራ በአንድ እጅ ቢራ፣ መጨፈር፣ መጮኸ፤ በየሙዚቃዉ የሚያስጨፍሩት ወንድ መለያየት
ከሚያስጨፍሩት ወንድ ስልክ መቀበል፣ በሚያስጨፍሩት ወንድ አንገት ውስጥ መወሸቅ፣ በሚያስጨፍሩት ወንድ መተሻሸት፣ወዘተ ....እነዚሁ ሁሉ እጅግ አሸማቃቂ ድርጊቶች ናቸው፡፡ ይሄ ለእነሱ ጀብዱ ሁሉ የመሰላቸው ይመስለኛል፤ ያለማፈራቸውና ድንገት የሚያውቀኝ ሰው ቢመጣ ብለው ግራ ቀኝ ያለመገለማመጣቸው፡፡ ተመልካች ሆነው እንኳን ያፍራሉ፡፡ በተለይ እነሱን በማስተናገድ የሚታወቁት ቤቶችም ጢም ያሉ ናቸው:: እኛ ተማሪዎች የሚገኙበት ቤት ብለን እንደመጣን ሁሉ የመጡ ይሄኔ ስንት ይኖራሉ? በዚያ ላይ ጥሩ ዋጋ ያወጣሉ ሲሉም ሰማሁ፤ እንግሊዘኛ ይሞካከራሉና፡፡ የዚያኑ ያህል ሴቶቹ ከገንዘቡ ይልቅ የሚማርካቸው ግዳይ ጥለው ማደራቸው መሆኑ ይወራል፡፡
╔═══════════════╗
🎖 #ዲላ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═══════════════╝
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የሚስተዋሉ አጓጉል ወሲባዊ ባህሪያት (ዓባይነህ አናሾ እና ታረቀኝ ታደሰ የታተመ ጥናታዊ ጽሑፍ)
እስካሁን እንደተገለፀው በዲላ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የሚታዩ ዋና ዋና አደገኛ ተያያዥ የወሲብ ባህሪያት እርስ በርስ ለወሲብ መነሳሳት።በአደባባይ መሳሳምና መተሻሸት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ያለ ኮንዶም ወሲብ መፈፀም፣ በርካታ የወሲብ ጓደኞችን ማፍራት፣ ያልተፈለገ እርግዝና፣ ማስወረድና ከሴተ አዳሪዎች ጋር መዳራት ናቸው፡፡
አደገኛ ወሲባዊ ባህሪይ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ላይ፣ በኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲዎች፣ የ ኮሌጆችን ጨምሮ የሚስተዋል ነው፡፡
╔═════════════════╗
🎖 #ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═════════════════╝
ከአዲስ አበባ ከተማ 513 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውና በ2010 እ.ኤ.አ ለ14ሺ ተማሪዎች የትምህርት ገበታ በዘረጋው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ላይ የኤች.አይሺ ሥርጭትን የሚገመግም ጥናት ተካሂዶ በአቶ ታሪኩ ደንጌታ አማካኝነት ለሕትመት በቅቷል፡፡ በጥናቱ መግቢያ ላይ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው በዩኒቨርሲቲ የሚኖሩ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ከሌሎች ወጣቶች በተለየ መልኩ ለኤች አይ.ቪ በሚያጋልጡ አደገኛ ድርጊቶች ላይ እንደሚሰማሩ ተገልጿል፡፡
⚡️⚡️በጥናቱ ላይ ከተሳተፉት ተማሪዎች ዉስጥ
☞ 22.8% የሚሆኑት ወሲብን ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀሙት ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
☞ ወሲብ የመፈፀም ልምድ እንዳላቸው ከተናገሩት ወንድ ተማሪዎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር አንሶላ የሚጋፈፉ መሆናቸውን እራሳቸው አምነዋል፡፡
☞ እንዲሁም ኮንዶም በአግባቡ የማይጠቀሙት 60% መሆናቸው ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሌሎች ወጣቶች በተሻለ ተምረዋል የሚባሉ ቢሆኑም ኮንዶም አለመጠቀምን ጨምሮ ሌሎች ጥንቃቄ የጎደላቸው ድርጊቶችን ሲፈፅሙ የሚስተዋሉ እነርሱ ናቸው፡፡ በተለይ ወሲብ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈፅሙ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ኮንዶም የመጠቀም ዝንባሌያቸው በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ መደብር ጎራ ብለው ኮንዶም ለመግዛት ስለሚያፍሩ ነው፡፡
╔═══════════════════╗
🎖 #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═══════════════════╝
እትጌ ገረመዉ የጭን መነባንብ ሌሎችም በሚለዉ መፅሀፍ ከገፅ44-45 ድረስ ስለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይህ ሰፍሯል
(ሊሊ!) እኔ የምልሽ! የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወንዶች እናንተ ጋ ሊዝናኑ አይመጡም? ሊሊ ይመጣሉ፤ ግን እነሱን ሌላ ቢዝነስ መፈለጊያ ነው የምንጠቀምባቸው፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከየት አምጥቶ ያወጣሻል? ማታ ቺቺኒያ አመሸሁ ለማለት ነው የሚመጡት፡፡ ለአልጋ መያዣ እንኳን ብር ስለማይተርፋቸው እስኪነጋ ድረስ ሲጨፍሩ ነው የሚያድሩት፡፡ እነሱን ለዳንስ ነው የምንጠቀምባቸው፡፡ በጣም አሪፍ ደናሾች ናቸው፡፡ ከነርሱ ጋር ሰትደንሺ የሚጎትትሽ አይጠፋም፡፡ ደግሞም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ቢኖረውም ማውጣት የለብሽም፤ አይፋቱሽማ፡፡ አንድ ቀን ካወጡሽ በቀን ሊያገኝሽ ይፈልጋል፤ ካልቃምን፣ ወደድኩሽ ምናምን እያሉ ይጃጃላሉ፡፡ስራ ቦታ በዚያ ምሸት ባዶ እጁን መጥቶ ውጭ አስጠርቶ እትት ሊል ይፈልጋል፡፡ አሁን አሁን ሁሉም ሴት ሰላወቀ ብር ቢኖራቸው እንኳን ማንም እሺ አይላቸውም፡፡»
በምን ታውቋቸዋላችሁ? ይለያሉ ማለት ነው? ልጅነታቸው፣ ሁለትና ሶስት ሆነው መምጣታቸው፤ አስሬ ብራቸውን እያወጡ መቁጠራቸው በአንድ ዕይታ ያሳልቀባቸዋል:: የሚጀምሩት በዳንስ መሆኑ መለያቸው ነው፡፡ እየደነሱ ሊገቡ ሁሉ ይችላሉ፡፡ ብታያቸው በዳንስ እና ስራችን የሆነ ቢዝነስ ማሯሯጫ በየቀኑ የምናስነካዉ እንኳን አንደርስባቸው ... የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ፌስቡክ የለሽም? የፌስቡክ አድራሻሽን ስጪኝ ስለሆነ #ላይክ ነው የምንላቸዉ፡፡ካለ እነሱ አራዳ ያለ አይመስላቸዉም፡፡ነገ ከቤተሰብ ስለሚላከልኝ ለዛሬ ተቸገሪልኝ የሚለው ብዛቱ ቀላል እንዳይመስልሽ፤ ባለፈው ሳምንት እምቢ ብለሽው ተመልሶ እንደ ጫትና ሲጋራ ለዱቤ ጥየቃ ይንጓተትሻል፡፡ ዱቤ መጠየቅ ከልክል ነው ብለን እንነቀስላቸው እየተባለ ሙድ የሚያዝባቸው ናቸው:፡»”
✏️✏️በጥቅሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻችን ገመና ባጭሩ ከሞላ ጎደል እስካሁን ያየነውን ይመስላል፡፡ የዩኒቨርሲቲዎች መብዛት ብቻውን ለምሁር መፍለቅ በቂ አይደለም፤ ምናልባትም ትምህርትን ለብዙኃን ለማዳረስ ካልሆነ በቀር፡፡ ልክ ዩኒቨርሲቲዎች የበዙትን ያህል ተማሪውን ከትምህርቱ የሚያግዱ ነገሮችም አብረው ይበዛሉ! ምናልባትም ከዚያ በብዙ እጥፍም ሊያድጉ ይችላሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ተማሪው ከትምህርቱ ይታገዳል፡፡ ተማሪው ካልተማረ ደግሞ አስተማሪው አያስተምርም፡፡ ይህም በመሆኑም ተማሪው ትምህርቱን እንዲማር የተለያዩ ሥራዎች መሠራት አለባቸው:: በዚያው ልክ ተማሪውን ከትምህርቱ የሚያግዱ ነገሮችም እንዲጠፉ አብዝተው መሥራት ግድ ይላል፡፡
#በመጨረሻዉ_ክፍል
በዚና የተበከለ ትዉልድ የመጨረሻ ዉጤቱ
ጋብቻን ማዘግየትና ማጣጣል..የፍች መበራከት...እራስን የማጥፋት ወንጀሎች መበራከት በህብረተሰቡ ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ እንዳስሳለን
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6210