tgoop.com/Islam_and_Science/6199
Last Update:
በቀጣይነት ግን እየለመደች ስለምትመጣ ምንም እንኳን ሒጃብ ለብሳ ብትመጣም ያው አስቀድማ ሚሪንዳ ማዘዝዋ ያለ ነው፡፡ እርሱም ከባለፈው ተሞክሮ በመነሳት ዛሬ ኸምሩን በዛ አድርጎ ከሚሪንዳው ጋር ይቀላቅልላታል፡፡ እርሷም ወዳጅዋን ላለማስቀየም ስትል አትምረውም፡፡ በመቀጠልም አብዝቶ በብርጭቆዋ ውስጥ ይጨምርላታል፡፡ እርሷም ስለማታስከፋው ትጠጣዋለች፡፡ ምናልባትም ያሁኑ ሴቶች ዓይን አውጣዎች ስለሆኑ በዚሁ ዕለት ሒጃቧን ከፀጉሯ ላይ አውርዳ ቦርሳዋ ውስጥ በመከተት ሚሪንዳውን ትታ ድራፍቱን ልትጀምር ትችላለች፡፡ እኔ በፊት በፊት ባለኝ መረጃ ሴቶቹ ከሚሪንዳ ወደ ድራፍት ሙሉ በሙሉ ለመግባት ከአራት እስከ አምስት አጋጣሚዎችን እንደሚወስድባቸው ነው፡፡ ነገር ግን አሁን አሁን የሙስሊም ሴቶች ልቅነትና ሀፍረት ቢስነት በእጥፍ ስለጨመረ ምናልባትም በሁለተኛው አልያም በሶስተኛ የግብዣ አጋጣሚ ሒጃቧን አውልቃ ልትጠጣ ትችላለች፡፡ ከዚህን ዕለት ጀምሮም ሚሪንዳን በማቆም በድራፍት አልያም በቢራ ልትቀጥል ትችላለች፡፡ ከካፊር ሴት ጋ የሚገጥመው ወንድም በዚሁ እሳቤ ውስጥ ይገባል፡፡››
በዚህ ጉዳይ ቤተሰብ ሴት ልጅህ የት እንደዋለች ጓደኛዋ ማን እንደሆነ መከታተሉ ኸይር ነዉ...አብዘሀኛዉ ሴቶች እቤት ሌላ እዉጭ ሌላ ናቸዉ...አረ ጎበዝ ሴት ልጅና ቤተሰብ ሳይተዋወቅ ዳዲ ማሚ እያለች ሳትተዋወቁ እየኖራችሁ ነዉ ጎበዝ
╔════════════════════╗
🎖#የባለመኪናዎች_የሴት_ቀበኛነት_አባዜ🎖
╚════════════════════╝
የዘልዛላ ባለመኪናዎች የሴት ቀበኝነትና ሴሰኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ በተለይ በሊፍት ስም በርካታ ህሊናቸውን የሸጡ ባለመኪናዎች ሴቶችን እያማገጡ ይገኛሉ፡፡ ከቀበጥ ሒጃቢስቶች ቀጥሎ ምናልባትም ሙስሊሙን ማህበረሰብ እየተፈታተነ ያለው ጉዳይ ይኼው ነው:: በነገራችን ላይ የቀበጥ ሒጃቢስቶችን፣የሌላ ሀይማኖት ወንዶች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሙስሊም ሴቶችን፣ የስትኪኒ ወንዶችን፣ የዘልዛላ ባለመኪናዎችን ገመና ገለጥ አድርጎ ማየቱ ለሕዝቡም ትልቅ ግንዛቤን ያስጨብጣል፡፡ ስለዚህ ነገሮችን በጥሞና ማጤንና ከዚህ የሚለቀቁትን መረጃዎች በወጉ ማስተዋል ግድ ይለናል፡፡
በርካታ የዘመናችን ሴቶች (ቀበጥ ሒጃቢስቶችን ጨምሮ) ከዶላር፣ ከፋሽንና ከዕቃ ዕቃ (የሞባይል፣ የላፐቶፕ፣ የጨርቃ ጨርቅ ስጦታ) ባልተናነሰ መልኩ መኪናዎችን እንደሚያመልኩ ይታወቃል፡፡ ከዚህም የተነሳ የሴቶች ጭን ማስተር ኪው በዘልዛላ ባለመኪናዎች እጅ እንዳለ ሁሉ መታሰብ ተጀምሯል፡፡
የነዚህ የዘነዛላ ባለመኪናዎች ገመናም በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል፡፡ በከተማዋ የመኪና ውስጥ ወሲብ መስፋፋቱንና መለመዱን ተከትሎ የነዚህ ግለሰቦች ድርጊትም በሰፈው የተለመደ ሆኗል፡፡ በተለይ ሙስሊም ዘልዛላ ባለመኪናዎች አደገኛንታቸው እየጨመረ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከየሰፈሩና ከየመስጊዱ አመሻሽ ላይ መጥተው ሴቶችን ፒክ አድርገው በየአካባቢው በሚገኙ ጨለማ መንገዶች ዳር በማቆም ማጨማለቃቸውን ገፍተውብታል፡፡ሙስሊም ያልሆኑ ዘልዛላ ባለመኪናዎች ብዙውን ጊዜ በሰዓት እላፊ ጊዜያቸው አብዝተው የሚያመሩት የሴተኛ አዳሪነት በብዛት ወዳለባቸው አካባቢዎች ነው፡፡ ነገር ግን ሙስሊም ዘልዛላ ባለመኪናዎቹ ትኩረታቸውን ያደረጉት የቤት ልጆች ላይ ሲሆን መኪናዎቻቸውን በየሰፈሩ በሚገኙ ጨለማ ቦታዎች በማቆምም የመኪና ውስጥ ዝሙትን አስፋፍተዋል፡፡ ይኼው የተለመደ እኩይ ድርጊታቸው በተለይ በረመዷን ውስጥ የሴቶች ልቅነት ስለሚበዛ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ሴቶችን ከመስጊድ አካባቢ ፒክ አድርገው የሚሄዱ መኪናዎችም ጋጋታ ሲፈጥሩ ይታያሉ፡፡
╔════════════════════╗
🎖#ላማገጧት_ሴት_ስጦታን_መጀባትና_ላማገጣት
#ወንድ_ስጦታን_መቀበል🎖
╚════════════════════╝
በርካታ ዘልዛላ ወንዶች ለሚያማግጧቸው ሴቶች የተለያዩ ስጦታዎችን ሲጀቡና ዝሙተኛ ሴቶችም ካማገጧቸው ወንዶች ስጦታዎችን ሲቀበሉ ይታያሉ፡፡ በእውነቱ የዚህ ዓይነቱ ድርጊት እጅግ አደገኛ ነው፡፡ የማይወጡት የኃጢአት ቀለበት ውስጥም ይከታል፡፡ ይኸውም ለሚያማግጧቸው ሴቶች ስጦታዎችን የሚጀቡ ወንዶች ተውበት ለማድረግ ቢፈልጉ እነዚያን #ስጦታዎች_መልሰው_መውሰድ_ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያንን ደግሞ ማድረግ አይሳካላቸውም፡፡ ለዝሙተኛ ሴቶችም ቢሆን ተውበት ለማድረግ ከፈለጉ በብልግናቸው ሳቢያ የተጀቡትን ስጦታ መመለስ አለባቸው፡፡ ይህን ማድረግ ግን በቀላሉ አይሳካም፡፡ ስለዚህ እዚህ ደረጃ የደረሱ ዝሙተኛ ወንዶችና ዝሙተኛ ሴቶች ታላቅ መጥመምን ጠመዋል፡፡
አህመድ አዲስ አበባ ታዋቂ ባለሱቅ እንዲህ ብሏል፡-
«ስንቶቹን ሙስሊም ጥንዶች ቀን በጠራራ ፀሐይ ወደ ፔንሲዮኖች ተያይዘው ሲገቡ እያየን አይደል እንዴ? ያለ ምንም ኃፍረትና መሸማቀቅ ወደ ዝሙት ቤቶች ዘው ብለው ሲገቡ እያስተዋልን አይደል እንዴ? አንዳንዶቹማ የዝሙት አልቤርጎዎችን እንደ መኖሪያ ቤታቸው የቆጠሩ ይመስላል፤ ወደነዚህ ቤቶች ሲገቡ ምንም ኃፍረት አይታይባቸውምና፡፡ የዝሙት ውሏቸውን ሲያጧጡፉ አንዳችም ወንጀል የሰሩ አይመስላቸውም፡፡ በብልግና ብቻ መኪና የተጀባቸው ሴቶች አሉ፡፡ በከተማዋ ውስጥም ለባለጌ ሴቶች የተጀቡ መኪናዎችም ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ ለእንትና እኮ መኪናዋን የጀባት ያ ያማገጣት ሰውዬ ነው ይባላል፡፡ በርግጥ ዝሙተኞች ከብልግናቸውም በላይ ስጦታን ሲቀባበሉ ስታይ የባሰ ትደነግጣለህ፡፡ ወደፊት ከኃጢአታቸው እንዴት ይቶብቱ ይሁን? ብለህ ስታስበው ትጨነቃለህ፡፡ አላህ ይጠብቀን እንጅ፣ በርካታ ዝሙተኛ ሴቶች መኪና ተጀብተዋል፡፡»ብሏል አህመድ ባለሱቁ
📚📚 በጥቅሉ እነዚህና እስካሁንም የተነሱ ነጥቦች ዝሙት በሙስሊሞች መካከል መስፋፋቱን የሚጠቁሙ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ሌሎችም ያልተነሱ ነጥቦች ይኖራሉ፡፡ ይህም በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በሀገረ ደረጃና በሕዝበ ሙስሊሙ ደረጃም ዝሙት ተስፋፍቷል፤ ይፋም ወጥቷል፡፡ ይህም ማህበረሰባችን በዝሙት ደዌ መታመሙን ያመለከታል፡፡ ፈጥኖ ፈውስ ካልተገኘለትም በሽታው የባሰ ሥር እየሰደደ ከባድ ማህበራዊ ውድቀትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
#በቀጣይ ክፍል☞ሴቱ ሁሉንም ሀዲስ ያዳምጣል ግን ለወንድ የተፈቀደዉን ሁለተኛ ማግባት ባይሰሟት ደስ ይላቸዋል፡፡ ወንድም ብዙ ሱና አለ ፆሙ የለይል ሶላቱ ወዘተ እያለ ሱናዉን እንተግብር ብሎ የሚያወራዉ ሁለተኛ ሚስትና ምግብ በጀመአ እየበላ ሊተርፍ ሲል ሱናዉን ሀይእናድርግ ይላል😉፡፡
ግን ስለሁለተኛ ሚስት የሚያወራዉ 99%ወንድ ሁለተኛ ማግባትን ያወራል ከዚህ መሀል ግን 85%ያላገባዉ ወንድ ነዉ ስለ ሁለተኛ ማግባት የሚፈተፍተዉ 10%ያገባዉ ወንድ አገባለሁ እያለ ያወጋል ግን Money ኢንጅሩ😆...4%ወንድ አቅም ያለዉ ነዉ ግን 2%አግብቶ ሰላም ስለሚያጣ አያገባም 2%ወደቆላዉ አካባቢ ያለ አግብቷል፡፡
የሚመለከተዉ 4%አቅም ያለዉን ወንድ ነዉ እንጂ የሚፎክረዉን አይደለም....እናም የሀብታም ባል ሴቶች ሁለተኛ ሚስት በመከልከላችሁ ባሎቻችሁ ዚና ላይ እንዴት እንወደደቁ እንዳስሳለን
#ምዕራፍ ➊➎
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6199