tgoop.com/Islam_and_Science/6196
Last Update:
ሲኒማ ቤቶች ሒጃብ በለበሱ ሴቶችም እየተለመደ የመጣ የመዝናኛ ዘርፍ እንደሆነ ይታያል፡፡ በርካታ ሒጃብ የለበሱ ሴቶች ከወንዶች ጋር፣ ወይም ከሴቶች ጋር
በጀማዓ እየሆኑ፣ አልያም ብቻቸውን ሲሰለፉና ሲገቡ ይታያሉ፡፡ በተለይ ቀበጥ ሒጃቢስቶች (ግብዣ ፍለጋ የሚወጡቱ ይባላሉ) አብሶ እሑድ እሑድ ወደ ሲኒማ ቤቶች አብዝተው እንደሚሄዱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የዚህም ዓላማ ወይ አስቀድመው ከወንዶች ጋር እዚያ ተቀጣጥረው ይሆናል፤ አልያም እዚያው ለመሞዳሞድ ይሆናል ምክንያቱም በአንፃራዊነት ሲታይ ወደዚያ የሚመላለሱ ወንዶችም ኪሳቸው ደህና እንደሆነ ይገመታልና፡፡ መቼም አንዲት ሴት የጥገኝነት ሜንታሊቲ አዳብራ ወደዚህ የምትመጣ ከሆነ በውነቱ ይህ ለርሷ ተጨማሪ ውድቀት ነው፡፡ ለሰው ልጅ ክብሩ ከገንዘብ ይበልጥለታልና፡፡
በተለይ የቀበጦቹ ሒጃቢስቶች የእሑድ እሑድ ሽር ብትን ለሲኒማ ቤቶች መልካም ገቢ እንደሆነ ሲታመን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ግን ትልቅ ማፈሪያ መሆናቸው አይካድም፡፡ ብዙ ሙስሊሞችም በነርሱ ድርጊት በመሸማቀቅ አምርረው ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ይህም በመሆኑ እባካችሁ ይህንን የምታደርጉ እህቶች ድርጊታችሁ ኢስላምን ሳይቀር የሚያሰድብ በመሆኑ ከዚህ እንድትታቀቡ ዘንዳ በአላህ (ሱ.ወ) ስም እንጠይቃችኋለን፡፡ «ሌላው ስለኔ ምን አገባው, የምትሉ እንኳን ብትሆኑም ኢስላም ከብር ስትሉ ከዚህ ድርጊታችሁ ታቀቡ እላለሁ፡፡
╔══════════════════════╗
🎖 #ዘፈን_በሙስሊሞች_መካከል_መንሰራፋትና
#የሙነሺዶች_ተቀባይነት_መጨመር
╚══════════════════════╝
ዒምራን ቢን ሑሰይን (ረ.ዐ) ቀጣዩን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
አንድ ጊዜ ሀቢቡና ሙሀመድﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ከዚህ ኡምመት የሆኑ የተወሰኑ ሰዎች በመሬት ይዋጣሉ፣ የተወሰኑቱ ወደ እንስሳነት ይለወጣሉ፣ እንዲሁም የተወሰኑቱ በድንጋይ ይወገራሉ (ይቀጠቀጣሉ) አሉ። ከሰሓቦች መካከል አንዱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ያ መቼ ነው የሚሆነውን ሲል ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም ዘፈኖችና የሙዚቃ መሳሪያዎች በተንሰራፉበትና አስካሪ መጠጥ በብዛት በሚጠጣበት ጊዜ ነው አሉ፡፡ (ቲርሚዚ)
ዘፈን ለዝሙት ትልቁን በር የሚከፍት ዓይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡ ዘፈን የሰዎችን ሙድ በመቀየር ለታሰበው ዓላማ መንገዱን ጨርቅ የማድረግ ኃይሎም ከፍ ያለ ነው፡፡ በተለይ የፍቅርና ወሲብ ቀስቃሽ ዘፈን በሴቶች ሙድና ስሜት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን በመፍጠር አርሷን ወደዝሙት በቀላሉ የማስገባት ኃይሉ አቻ የለውም፡፡
የሴቶችን ስሜት በማጦዝና በማሾር እነርሱን ከፍተኛ የሆነ ፆታዊ ስሜት ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ በተለይ በዘፈን ላይ አልኮል ከወሰደችበት ሴቷ መቅለጥ ነው፡፡ እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ» እንደሚባለው የዘመኑ ሴቶች እንኳን ዘፈን ተከፍቶባቸው ይቅርና በፊትም #ልባቸው_ከንፈራቸው_ላይ_ነው ይባላል፡፡ የሆነ ሆኖ ሴቶች ረቂቅ እንደመሆናቸው መጠን ልባቸው በዘፈን በቀላሉ ይከፈታል፡፡
ያው ዘፈን የትም ያለና የተለመደ ነገር ነው፡፡ ዘፈን የማይገባበት ቦታ የለም ማለት ይቻላል፤ መስጊድ ሲቀር፡፡ በርግጥ ወደ መስጊድም ገብተው ሞባይላቸውን ሳይለንት ሳያደርጉ ዘፈን የሚያፈተልከባቸው ሰጋጆች ሰርክ ያጋጥማሉ፡፡ ስለዚህ ዘፈን መስጂድ ድረስ ሁሉ በተዘዋዋሪ መጥቷል ማለት ይቻላል፡፡
በተጨማሪነትም ዘፈን በሙስሊሞች መካከል መንሰራፋቱን ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል አንዱ የተለያዩ #ኢስላማዊ_ዲጄዎች ብቅ ብቅ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ኢስላማዊ ዲጄዎች በተለይ የበርካታ ሰዎችን ሰርግ መጀመሪያ አካባቢ በነሺዳ በማድመቅ የሚታወቁ ሲሆን አሁን አሁን ግን ምናልባትም ከሁለት ነሸዳዎች ለጥቆ ወዲያው ወደዘፈን እንደሚገቡ መረጃዎች ያመለከታሉ፡፡ እነዚህ ዲጂዎችም በተለይ በወጣት ሙስሊም ሴቶች ( #ቀበጥ_ሒጃቢስቶች) ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙ ሲሆን በርካታ ቀበጥ ሐጃቢስቶችም ከዲጄዎቹ ጋር አልጋ መውደቃቸው ይነገራል፡፡በተጨማሪ በጣጣም ብዙ ቀበጥ ሒጃቢስቶች ሚዲያ ላይ ከምናቃቸዉ የመድሰክ ሰዎች ጋር አልጋ ላይ ወድቀዋል
⚠️⚠️⚠️ በተለያዩ ከተሞች በተለይ በአዲስ አበባ ጋጠወጥ ሴቶች ይሄን አመለካከት ይዘዋል፡፡ቢክራን ለታወቂ ሰዉ መስጠት በሚል ገና ከአንደኛ ደረጃ ትቤት ያሉ ሴቶች ጀምሮ እስከ ካምፓስ ድረስ ያሉ ተማሪዎች በዚህ አደገኛ አባዜ ነገ ስትዳር ሲመጣ ቢክራ ነሽ አይደለሽም ብሎ ይጠይቀኛል አይጠይቀኝም እያሉ የሚያስቡበትን የማይመለስ ቀይ የደም ሴላቸዉን በሀራም እየሸኙት ነዉ፡፡ በመድረክ የምናቀዉ ዘፋኞች ታዋቂ ሰዎች በምድረክ የምናቀቸዉ እነስም አይጠሬ☺️ሙስሊሞች(እነማን እንደሆኑ የገባዉ ይግባዉ)
በሴቱም አስገዳጅነት በታዋቂ ሰዎች ቸልተኝነት ለታዋቂ ሰዉ ድንግልናን መስጠት የሚል ፋሽን ከተጀመረ ሰነባብቷል፡፡እባካችሁ ሴቶች ...የሴትነት ህይወት ቀላል አይደለም፡፡ሴትነት ማለት አላማ ግብ ላይ ለመድረስ በዙሪያዉ የተተከለ እሾህ ብዙ ነዉ እሱን እያፀዱ እየነቀሉ የመኖር ህይወት ነዉ፡፡እሾሁ እየወጋ መሄጃ እንዳያሳጣሽ ተጠንቀቂ!!!
#በቀጣይ_ክፍል፡-የሙስሊም ሴቶች ከካፊር ወንድ ጋር ወሲባዊ አጋርነት መመስረት እና የዘልዛላ ባለመኪናዎች አባዜ እና ላማገጧት ሴት ስጦታን መጀባትና ከማገጣት ወንድ ስጦታን መቀበል ላይ ያተኮረ ፁሁፍ ይቀርባል
#ምዕራፍ ➊➍
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6196