tgoop.com/Islam_and_Science/6174
Last Update:
የዝሙት መዳረሻዎች ከሞላ ጎደል እየለፈለፉ የተንሰራፉ ሲሆኑ ኢኽቲላጥ ግን ድምፁን አጥፍቶ ውስጥ ለውስጥ የገዘገዘን የዝሙት መጋዝ ነው፡፡ እንደነርሱ እምነት ከሆነ እነዚህ መስፈርቶችም ኢኸቲላጥን በተገቢው ገደቦች ውስጥ የሚጠብቁ ናቸው::
ሆኖም ግን ለመሆኑ እናንተ ይፈቀዳል የምትሉት ኢኸቲላጥ ዛሬ ዛሬ በየት/ቤቱ፣ በየኮሌጁ፣ በየዩኒቨርሲቲው፤ በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየገበያ ማዕከሉ፣ በየንግድ ታዎሩ፣ በየመጓጓዣው፣ በየአደባባዩ፣ በየማህበራዊና ሕዝባዊ ስብስቦቹ ላይ የምናየው ዓይነት ነውን? እሺ! እነዚህ ሁሉ የኢኸቲላጥ ዓይነቶች እናንተ ይፈቀዳሉ በምትሏቸው ገደቦች ውስጥ ናቸውን? ለመሆኑ እናንተ ይፈቀዳሉ የምትሏቸው የኢኸቲላጥ ዓይነቶች በገሀድ አሉን? ሲባሉ አጥጋቢ ምላሽ የላቸውም፡፡ በእውነቱ ዛሬ ዛሬ በየቦታው የምናያቸው የኢኸቲላጥ ዓይነቶች በአለባበስ፣ በአነጋገር፣ በወንዶችና ሴቶች መካከል ባለው ኢንተራከሽንና በምግባር ረገድ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሉም፡
✅ ዛሬ ዛሬ ባሉ ኢኸቲላጦች ውስጥ የሴቶች መገላለጥ (ተበርሩጅ)፣ የሒጃብ መስፈርቶች ጥሰት፣ የሴቶች ልቅነትና በአጠቃላይም ሥርዓት አልበኝነት የሰፈነበት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
እነሆ በኢኸቲላጥ ሳቢያም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፊትናዎችን እያየን ነው፡፡ በተቃራኒ ፆታዎች መካከል ለሚፈፀሙ ወንጀሎች ሁሉ ምንጩና መፈልፈያው ኢኸቲላጥ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ኢኽቲላጥ ሲኖር በወንዶችና በሴቶች መካከል በቀላሉ የሚያስጠርጥሩ ግንኙነቶች ይፈጠራሉ፡፡ስለዚህ ዛሬ ዛሬ እየተከሰተ ያለው የኢኸቲላጥ ዓይነት ምንም ተቀባይነት የለውም፡፡
✏️✏️ ከሴቶች ልቅነት የተነሳ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሚደረጉ ኢኽቲላጦችም ተውጠዋል፤ ከስመዋል ማለት ይቻላል፡፡ ወጣም ወረደም ሸሪዓው እንዲህ በታመቀበት አግባብ ውስጥ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሚደረጉትን ኢኽቲላጦች እንኳን ማበረታታቱ አግባብነት የለውም፡፡
ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ለዝሙት ለም የሆነ የማብቀያ መሬትን በማዘጋጀት ይህንን ደዌ ለዚህ ደረጃ ያበቃው ትልቁ ነገር ኢኸቲላጥ (የፆታዎች ቅልቅል) ነው፡፡ዝሙትን መሥራት ውሀን የመጠጣት ያህል ቀላል ያደረገውና ከዚያም አልፎ ሰዎች በዝሙት እንዲፎካከሩ ያደረገው ይኸው ኢኽቲላጥ የተባለው ደዌ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ የዓለምን ማህበረሰብ ቀፍድዶ የያዘው የዝሙት ዛር በዋናነት የተፈለፈለው ከኢኸቲላጥ ነው፡፡እናም ከኢኸቲላጥ ጋር የተያያዘውን እውነታ መገንዘብና ማህበረሰቡን ከገባበት ሕመም መፈወስ እንገብጋቢ ጉዳይ ሆኖ ይታያል፡፡ እንደ ኢኸቲላጥ በዝምታ የዝሙትን መርዝ የረጨው ሌላ የመዳረሻ መንገድ የለምና፡፡ሌሎች የዝሙት መዳረሻዎች ከሞላ ጎደል እየለፈለፉ የተንሰራፉ ሲሆኑ ኢኽቲላጥ ግን ድምፁን አጥፍቶ ውስጥ ለውስጥ የገዘገዘን የዝሙት መጋዝ ነው፡፡
✅ ዛሬ ላይ ኢኽቲላጡ ያለማካበድ ከሌሎች ሀይማኖት በላይ ሙስሊሙ ላይ ይስተዋላል፡፡የኢኽቲላጥ መንገድ በኸይር ስራ ስም፡በሙስሊም የመድረክ ዝግጅቶች፡በሙነሺድ ተብየዎች በሚያዘጋጁት የነሺዳ ማስመረቂያ ሰም ኢህቲላጥ ተበራክቷል፡፡በፊት ታስታዉሱ ከሆነ የዛሬ 3አመት በፊት ሙነሺዶች መጣን መጣን ባሉ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ይዘዉ የመጡት ነገር ከባድ ነዉ ለወደፊት ከባድ መዘዝ ይዘዉ መጥተዋል እያልኩ ብቻየን ፁሁፍ ሳዘጋጅ በጣጣም ተቃዋሚ ይበዛ ነበር ትችቱ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ተዉኩኝ..ይሄዉ ዛሬ ነሺዳና ሙዚቃ መለየት እስከሚያቅተን በዜማ ሲጣሉ ሊደባደቡ ሲደርሱ
ነሺዳና ሙዚቃ ሲሰራረቁ እያየን ነዉ፡፡
የአሁን ሴት ሮል ሜድልሽ ማን ነዉ ብትባል አንዱን ሙነሺድ ነዉ😬 የምጠራዉ...ሚዲያ ላይ በፊት ብዙ ሴቶች በማስረጃ እንደነገሩኝ በጣጣም ብዙ የሙነሺዶች ገመና አቃለሁ የሚሰቀጥጡ ነገሮች በማስረጃ የማቀዉ አለ
አሁን ላይ የሚሻለዉ እነሱን አለመከታተል ነዉ ለምን የሚሰሩት ለአሏህ ብለዉ የአላህን ወዴታና የነብዩን ዉዴታ ለማግኘት ሳይሆን ታወቂ ለመሆን ለሴቱ የተሻለ ስራ እኔን ሴቱ እንዲወደኝ የትኛዉ ስራ ልስራ ስለሆነ እነሱን መከታተሉን ትቶ...አላህ ሆይ ቀጥተኛ መንገድ ምራቸዉ ወይ በዚሁ በዱንያ በሙነሺድ ስም የሚሰሩትን ግፍ ያሳየን ብሎ ዱአ ማድረጉ ይሻላል፡፡
«አደገኛው የኢስላም ጠላት አላዋቂ ሙስሊሞች ናቸው።በአላዋቂነታቸው ላይ ስሜታዊ ይሆኑና በድርጊታቸው የኢስላምን እውነተኛ ውበት ያጠለሻሉ።የሌላው ዓለም ሰዎች የነርሱን ድርጊት በመመልከት ኢስላም ያ እንደሆነ ያስባሉ። (ሽህ ኢሕመድ ዲዳት) የተናገሩት ንግግር የአሁን ዘመን ሙነሽዶችን ያካትታል👌👌
🫵 በተጨማሪ ዛሬ ላይ ኢኽቲላጡ በሙስሊሙ በዲን ስም ተጋኗል፡፡
🔶 #ሙነሺዶች፡ሚንበር ቲቪ የተለያዩ ሙሀለጣ ባላቸዉ ፕሮግራሞች አኽቲላጥ አለ በዚህ ኢኽቲላጥ ወደ ዝሙት መስመር የሚገቡ አሉ
🔶 #የሙስሊም_በጎ_አድራጎት_ማህበር እየተባሉ ሴትና ወንድ የሚደባለቁበት አለ፡፡አረጋዉያንን መንከባከብ..የተቸገሩ ለመርዳት ስበብ ለጀመአችን ማጠነከሪያ እየተባለ የሙስሊም ሴቶች ተበጃጅተዉ አንፀባራቂ ሎሚ ከለር ልብስ ለብሰዉ ከአጂ ነብይ ወንድ ለጀመአ ማጠናከሪያ በሚል ብር ማሰባሰብ..ለጀመአችን እየተባለ ሲዋክ መሸጥ...ቡና እያፈሉ በየመንገዱ መሸጥ...ጫማ የሚጠርጉ አለ...
የደካሞች ቤት ተብሎ የጀመአየ ልጅ አብረዉ ወንድ ጋር ሂደዉ ሴቶች ልብስ ሲያጥቡ ወንዱ ቤት ያስተካክላል..ሰዉ ያላስተዋለዉ ሙዱን የቀየረዉ የዝሙት መንገድ ነዉ☺️
#አሁንም እየሆነ ነዉ ለወደፊትም ታዩታላችሁ የዝሙት መንገድ ነዉ አሁንም አንዳንዶችም በድብቅ ገብተዉበታል::
የአላህን ዉዴታ አጅር ለማግኘትና ሴት ልጅ ቡና የምታፈላዉ ቤተሰቦቿን ለመሀደም እንጂ መንገድ ላይ ወንድ እንዲያት አይሆንም ነበር...ለጀመአየ ብላ ጫማ የምጠርገዉ የእናቷን የአባቷን ጫማ ረግጣ ወጥታ ነዉ...የአረጋዉያን ልብስ ልጠብ ብላ ስትወጣ የእናት የአባቷ ልብስ ግን ቆሾሾ ተቀምጧል...መቅደም ያለባቸዉ የአክስት የአጎቶቿ ልብስ የሚያጥብላቸዉ ተቸግረዋል ወይም ጎረቤቷ እማማ እንትና ልጅ የላቸዉ የሚንከባከብ የላቸዉ ልብሳቸዉን የሚያጥብላቸዉ የለ በርሀብ እየተሰቃዩ ይሆናል..ይህን ሁሉ አልፎ ሂዶ ጀመአየ አዘዘኝ አሚሬ አዘዘኝ ብሎ መንጦልጦል ከምር አስመሳይነት ነዉ🙄፡፡በፊት ወንድ ሴትን ልጅ ለማዉራት ካፌ ወይ ወጣ ያለቦታ ነበር ዛሬ ግን የጀመአ ፕሮግራም አለ በሚል ስም መገናኘት ሆነ አልሸሹም ዘወር አሉ ነገር ግን ኮዱን ቀየሩ😊 ነዉ የምንለዉ ወዳጄ..ቤተሰብ ሆይ ንቁ እባካችሁ‼️‼️
ግን ሴቶች ለብቻ ወንዶች ለብቻ የሆነ በጎ አድራጎት ወይ ጀመአዎች አሉ በተጨማሪ ትላልቅ ሰዎች ባለሀብቶች አሉ ለኸይር ስራ የተቋቋሙ እነዚህን ግን እንደማያካትት ልታቁልኝ ይገባል፡፡የእኔ ሀሳብ ኢኽቲላጥ ያለባቸዉ የወጣቶች ጀመአዎችን ነዉ
#በቀጣይ_ክፍል...የእጅ ዚና የጆሮ ዚና ላይ ያተኮረ ፁሁፍ ቢኢዝኒላህ ይዤ እቀርባለሁ
#ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን
#ምዕራፍ ➐
ይቀጥላል....
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6174