tgoop.com/Islam_and_Science/6164
Last Update:
🟡እስጢፋኖስ አበራ ደግሞ እንደዚህ ብሏል «በአዲስ አበባ ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑ መደበኛ ሴተኛ አዳሪዎች አሉ፡፡በየምሽቱ ደግሞ በከተማዋ ሰማይ ሥር ተጠልለው የወሲብ ንግድ የሚያካሄዱ ሴተኛ አዳሪዎች ብዛት 200 ሺህ ነው፡፡»ብሏል
🔴ረዳት ፕ/ር አደም ካሚል እንዲህ ብሏል
እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት በአዲስ አበባ ውስጥ 400ሺህ መደበኛ ሴተኛ አዳሪዎች አሉ፡፡ይኸው አኃዝ ደግሞ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችና በተለይ አሕጉራዊ ስብሰባዎች ሰሞን በእጥፍ በመጨመር 800 ሺህ ይደርሳል፡፡››ብሏል
ይህ ሁሉ ጥናት ከ2009 በፊት መሆኑ ይታወቅ፡፡
ሴት ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ቱሪስቶች በጣም በዝተዋል..ለእነዚህ ቱርስቶች የሚያገናኝ ደላላ በዛዉ ልክ በዩኒቨስቲ በመስሪያ ቤት በአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወጥመድ ዘርግተዉ ድንግል የሆነችዉንም ያልሆነችዉንም በየምርጫዉ ያቀርባሉ፡፡
የዴይሊ ኔሽን ፀሐፊው አዲስ አበባን ከባንኮክ ጋር በማነፃፀር እንዲህ ይገልፃታል፡-
‹‹ብዙ የዓለም ሀገሮችን ጎብኝቻለሁ፡፡እንደ ታይላንዷ ባንኮክ የወሲብ ንግድ የሚካሄድባት ከተማ አላየሁም የሚለው አንድሪው በቀናት የአዲስ አበባ ቆይታው የተመለከተው የከተማዋ የምሸት ገፅታ እና የወሲብ ንግድ ባንኮክን እንዳስታወሰው እና ከባንኮክ ጋር እንደተመሳሰለበት ይጠቁማል፡፡ ባንኮክ እና አዲስ አበባ በብዙ ነገሮች ይመሳሰላሉ፡፡ሁለቱም በወሲብ ያበዱ እና ወሲብ በስፋት የሚነገድባቸው ከተሞች ናቸዉ ሲልም ይገልፃቸዋል፡፡እንደ ባንኮክ ሁሉ በአዲስ አበባ ናይት ክለቦችም የጦፈ የወሲብ ንግድ ይካሄዳል፡፡ በጎበኘኋቸው ናይት ክለቦች ሁሉ ለሽያጭ የቀረቡ በርካታ ውብ ታዳጊ ሴቶችን ተመልከቻለሁ፡፡መኪና ውስጥ እና በየግድግዳው ሳይቀር ወሲብ የሚፈፅሙ ሰዎችን በተለይ ቦሌ አካባቢ ተመልከቻለሁ፡፡እንደ ባንኮክ ሁሉ በርካታ የወሲብ ቱሪስቶችን በአዲስ አበባ መመልከቴ ደግሞ በጣም አስገርሞኛል፡፡ባንኮክ የአውሮፓ የወሲብ ቱሪስቶች መዳረሻ እንደሆነችው ሁሉ አዲስ አበባም የብዙ የዓረብ የወሲብ ቱሪስቶች መናኸሪያ ወደ መሆን መቃረቧንም ተረድቻለሁ ይላል፡፡››
የውጭ ዜጎች ስለ አዲስ አበባ ከተናገሩት መካከል አንዱ እንዲህ ብሏል<<አዲስ አበባ ከሳምንት እስከ ሳምንት ጭፈራ የደራባት፣ሰርክ ጭሰት ያለባት፣ ናይት ክለቦቻ ሰርክ እንዳቃሰቱ የሚያነጉባትና ሰርክ በወሲብ ንግድ ያበደች የዓለማችን ልዩ ከተማ ናት። ከተማዋ ዕረፍት የሚባል ነገር የላትም፤ ጭፈራ፣ ዳንስና የወሲብ ንግድ የዘወትር ልማዶቿ ናቸውና፡፡»ብሏል
╔══════════════════════╗
🔶 #በአዲስ_አበባ_የድንግልና_ንግድ_መስፋፋት
╚══════════════════════╝
ያደጉ አገራት በዕለታዊ ጋዜጦቻቸው ላይ ሴተኛ አዳሪን ሲያቀርቡ ..በኢንተርኔት ድንግልና ሲቸረችሩ አዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶቿን በሴተኛ አዳሪ ሞልታ ከማንም አላንስም እያለች ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ ለድንግልና አፍቃሪዎች ለመገብየት የሚሠማሩ ደላሎች አሉ፡፡ ከትንሿ ሺህ ብር እስከ 20 ሺህ ብር ድረስ እንደሚከፍሉ በመንገር አዳጊ እና ወጣት ሴቶቹን ለማማለል ይጥራሉ፡፡
ከኢትዮጵያዉን ድንግልና አሳሾች መሀከል እየጎሉ የመጡ ታዋቂ ባለሀብቶች፣የማስታወቂያ ባለሙያና ዳያስፖራዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡›
ነጮቹ ሴተኛ አዳሪ ከፈለጉ በቀላሉ የምሽት ከልብ ሄደው አንስተው መምጣት እንደሚችሉ ስለሚያውቁት ትኩረታቸው የቤት ልጅ ላይ ነው፡፡ ጥያቄያቸውን ከአጥጋቢው በላይ መመለስ ደግሞ ለወሲብ ደላሎች በጣም ቀላል ሥራ ነው፡፡
የላይኛዉ ምንጭ መፅሀፍ ስለዚህ ጉዳይ ይህንን መረጃ አጋርቷል
>>የእኛ አገር ሴቶች ብዬ ሁሉንም መጠቅለል ባልችልም የሚገጥሙኝ ሴቶች ሁኔታ ግን በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ፈረንጅ ይዘን ስንሄድ ዓይናቸው ይቀላውጣል፡፡ቆንጆ እና አማላይ የምትላት ሴት አጣብሰኝ እንጂ,ብላ ትጠይቅሀለች፡፡በፈጣጣ ሰላም ብለው ከየት ነህ? ብለው ነጩን የሚያዋሩት ብዙ ናቸው፡፡ በተለይ ወደ ቦሌ የውጭ አገር ዜጎችን ይዘዋቸው ከሄዱ እንግሊዘኛን እንደ ውሃ የጠጡ ወጣት እንስቶች ፈረንጆቹን ተቀላጥፈው ጋይዶቹን ከጨዋታ ውጭ ያደርጓቸዋል፡፡ለእኛ 10 ብር ለመስጠት የሚያምጡ ቱሪስቶች ለሴቶች ለጊዜያዊ ቆይታ እስከ 200 ዶላር ይሸኛቸዋል፤ ይላል የቱር ጋይዱ ጌታሁን፡፡ የፈረንጆ፥ ወሲባዊ ፍላጎት ጥግ ድንግል ሴት ድረስ የሚሄድ ሲሆን የእነ ጌታሁን እና ንጋቱ ዓይን ይፈጣል፡፡ደከመውም ቢሆን ግን ፍላጎታቸውን ይሞላሉ፡፡ ጥያቄው አሁን አሁን እየተበራከተ ስለመጣ ከተሳካላቸው እንግዶች ከማግኘታቸው በፊት ድንግል ሴቶችን አግባብተው ለመጠበቅ ይሞክራሉ፡፡ከተማዋ ላይ ያለው የድንግል ሴት እጥረት ግን ይፈትናቸዋል፡፡
╔══════════════════════╗
✅ #በአዲስ_አበባ_የግብረሰዶም_መስፋፋት
╚══════════════════════╝
ግብረሰዶማዊነት (ወንድ ለወንድ እና ሴት ለሴት) በከተማዋ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡በምሽት መዝናኛ ቤቶች ውስጥ የሚከፈቱ ወሲብ ቀስቃሽ ሙዚቃዎች፣ጭፈራዎችና የራቁት ዳንስ ለግብረሰዶማዊነት መስፋፋት በዋናነት ተጠቅሰዋል፡፡
ዊክሊክስ ድርጅት ያጋለጠው ሀቅ ግብረሰዶማዊነት በአዲስ አበባ መስፋፋቱን አጋልጧል
“በሀገሪቱ ሕግ ግብረሰዶማዊነት በእስራት የሚያስቀጣ የወንጅል ተግባር ቢሆንም በተለይ ባለፉት አስር ዓመታት የግብረሰዶማዉያን ቁጥር በተለይ በአዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው፡፡በግብረሰዶማዊ የወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ በርካታ ወጣት ወንድ እና ሴቶችን ጭምር በቀላሉ በከተማዋ ማግኘት ይቻላል፡፡ ግብረሰዶማዉያን በምስጢር የሚሰባሰቡባቸው ድብቅ የመዝናኛ እና የመገናኛ ቦታዎችም አዲስ አበባ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ስማቸው እንዲጠቀስ ከማይፈልጉና በማህበር ጭምር ከተደራጁ የከተማዋ ግብረሰዶማዉያን ያገኘሁት መረጃ እንደሚጠቁመው ሊደርስባቸው የሚችለውን ማህበራዊ መገለል፣ መድሎና ወገዛ በመፍራት እራሳቸውን የደበቁ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ ወንድ እና ሴት ግብረሰዶማዉያን በአዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለው እውነትም ተመሳሳይ ነው፡፡በተለይ ዩኒቨርሲቲ በተስፋፋባቸው የሀገሪቱ ከተሞች መሰል ዝንባሌ ያላቸው ሰዎችን በብዛት ማግኘት ይቻላል፡፡(ጥናቱ ከ2009 በፊት የተጠና ነዉ አሁን 2016 እሰቡት)
እርግጥ ግብረሰዶም ከከተሞች አካባቢ ይልቅ በገጠር በጣም ይጠላል፡፡ ከአዋቂዎች ይልቅ ወጣቶች ግብረሰዶማዊነትን በተመለከተ አዎንታዊ አመለካከት አላቸው፡፡በዚህም የተነሳ ግብረሰዶማዊነት በወጣቶች መካከል በየጊዜው እየተስፋፋ ነው፡፡›>
📕📕 #በቀጣይ_ክፍል ዝሙት እንዲስፋፋ በር የከፈተዉ የቤተሰብ እንዝላልነት እና የዝምድና ትስስር መላላት እንደሆነ እንዳስሳለን
#ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ወንደኛ አዳሪ፣ወንድ ሸሌ፣ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት ኢላሂ ይወፍቀን
#ምዕራፍ ➍
ይቀጥላል...
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6164