tgoop.com/Islam_and_Science/6161
Last Update:
«መጥፎዎቹ ወንዶች ልጃገረዶችን ያበላሻሉ፡፡ ከዚያም ማግባትን ሲያስቡ ሷሊሕ ሚስት ፍለጋ ይሄዳሉ፡፡ ግን የምታገኛት ሚስት ያንተው ዓይነት ሥነ-ምግባር ያላት ትሆናለች፡፡ አብዛኛው ወጣት ገርልፍሬንድ ብሎ የያዛትን ሕገወጥ የወሲብ አጋሩን በፍፁም አላገባትም ይላል፡፡ ታዲያ እኔ የምልህ ነገር ቢኖር የዝሙት ጓደኛህን ባታገባትም እንተ የምታግባት ሚስት የሌላ ሰው የዝሙት አጋር እንደነበረች ቅንጣት ታክል አትጠራጠር፡፡ ከፈለክ ይህንን የአላህ ተባረከ ወተዓላ ቃልን አንብብ፡- መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎች ወንዶች መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡ (አን-ኑር 26)
╔══════════════════════╗
✅ #ሴቶች_በዝሙት_የሚያስተናግዱት_ጉዳት
╚══════════════════════╝
በዚና ሳቢያ የሴቶች ወሲባዊ ህይወት ውጥንቅጡ ወጥቷል፡፡ትዳርና ቤተሰብን አጥተዋል፡፡ለሰቅጣጭ ወሲባዊ እብደቶች ተዳርገዋል፡፡ ከሰው ያልተፈጠሩ በሚመስል መልኩ የወሲብ መንገደኞች የጭካኔ አያያዝ አርፎባቸዋል፡፡ሴቶች የሕዝቡ መሠረት መሆናቸው ቀርቶ የሕዝብ ቢራቢሮ ሆነዋል፡፡እራሳቸውን ለማሻቀጥ እዚያም እዚህም ሲርመሰመሱ ይውላሉ፡፡
☞ ውርጃ እንደጉድ ይካሄድ።
☞የእንስቶች ማሕፀን እንደጉድ ይሳሳል፡፡
☞ የማሕፀን ግድግዳቸው ይደማል፡፡
☞ ሴትነታቸው ረክሶ የስሜት ማራገፊያ ዕቃ ተደርጎ ይታያሉ፡፡ ታዲያ የነዚህ ሁሉ ጉዳቶች ሰለባ የሆኑ ሴቶች ብዙኃኑ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን የሙጥኝ ያሉ ናቸው፡፡
🟡 ሴቶቹ በተደጋጋሚ በሚደርስባቸው ወሲባዊ ጥቃቶችና በሚፈፀምባቸው ወሲባዊ እብደቶች የተነሳ እነሆ ዛሬ ዛሬ የወሲብ ሕይወታቸው ምስቅልቅሉ ወጥቶ በወንዱ ፍላጎት ውስጥ ታጥረው ይገኛሉ፡፡ ይህች ዓለም ከሴቶች ማግኘት የሚገባትን ፈርጀ ብዙ አስተዋፅኦ ተጨናግፎ፣ሴቶች የማህበረሰቡ የሕይወት አካል ሳይሆኑ ለወንዶች የስሜታቸው ማራገፊያ እንደሆኑ ተደርገው ታይተዋል፡፡
ዛሬ ዛሬ ሴቶች ስብዕናቸው ወርዶ፣ ገመናቸው ገሀድ ወጥቶ፣ ገላቸው በአሻንጉሊት ቅርፅ ሳይቀር ተሠርቶ፣ የሴትነት ወጋቸው ጠፍቶ፣ክብራቸው ተዋርዶ፣ዓለም በሴት ልጅ ላይ ፊቷን አዙራ የሚደርስባትን ችግር ብቻዋን ትጋፈጠዋለች፡፡የዓለማችን እኩያንና የኢስላም ጠላቶች ሴቶችን አራቁተው በገላቸው ይዝናናሉ፡፡ ሴት ልጅ የሕይወት አጋር መሆኗ ቀርቶ የወሲብ አጋር ብቻ ተደርጋ ትታያለች፡፡ይህም ችግር በዓለም ደረጃ ሥር የሰደደና የዝሙት መስፋፋትን በጉልህ የሚያሳይ ነው::
⚠️ከዚና ወንጀል ተውብትን ሳያደርጉ የሚሞቱ ግለሰቦች ቅጣት በመቃብራቸው ውስጥ ይጀምራል፡፡በረጅም ሐዲስ ውስጥ እንደተዘገበው አንድ ጊዜ የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ህልም ማየታቸውን ተናገሩ፡፡ከርሳቸውም ጋር ሁለት ሰዎች (ጂብሪልና ማሊክ በሰው ሱረት ሆነው) ነበሩ፡፡ሁለቱ ሰዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ኃጢአተኞች አንዴት በበርዘኸ(በሞትና በፍርዱ ዕለት መካከል ባለው ሕይወት ውስጥ) ሲቀጡ እንደነበረ ያሳዩዋቸው ጀመር፡፡ ይህንኑ ሲገልፁ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡-
« በመሬት ውስጥ ያለ ጉድጓድ ዘንድ እስከምንደርስ ድረስም እንዲሁ እያሳየኝ ወደፊት መዛዛችንን ቀጠልንበት፡፡ የመጋገሪያ ጉድጓድ ይመስላል፡፡ ከላይ በኩል ጠባብና ከታች በኩል ደግሞ ሰፊ የሆነ ነው፡፡ ጉርምርምታና ድምፆችም ከርሱ ውስጥ ይወጡ ነበር፡፡ ወደ ውስጡ ተመለከትን፡፡እርቃነ ስጋቸውን የሆኑ ወንዶችና ሴቶችንም እየናቸው፡፡ከጉድጓዱ ስር ከታች በጣም የነደደ እሳት ነበር፡፡ እርሱ ድንገት በነደደ ቁጥርም ወንዶቹና ሴቶቹ ይጮኻሉ፡፡ወደላይም ከፍ ይላሉ፤ከሞላ ጎደል ከጉድጓዱ ውስጥ ለመውደቅ አስከሚቀርቡ ድረስ፡፡ እሳቱ እያነሰ በሄደ ቁጥርም ወደ ስሩ ይመለሳሉ፡፡እኔም እነዚህ እነማን ናቸው? ስል ጠየኳቸው፡፡እነርሱም,እነዚያን ራቁታቸውን በጉድጓዱ ውስጥ ያሉትን ወንዶችና ሴቶችን በተለመከተ፤ እነርሱ በዚና ላይ የወደቁ ወንዶችና ሴቶች ናቸው በማለት መለሱልኝ::(ሰሒህ ቡኻሪ)
╔════════════════════════╗
✅ #ስሜትን_ለመቆጣጠር_የሚያስችሉ ጥበባዊ ምክሮች
╚════════════════════════╝
ታላቁ ሊቅ ኢማሙ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ስሜትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ጥበባዊ ምክሮች አል-ፈዋኢድ ከተሰኘ መፅሀፋቸዉ የተወሰዱ ምክሮችን ያስተንትኗቸዉ
➊ የሰው ልጅ የመላዕክት አእምሮ የእንሰሳት ፍላጎትና የሰይጣን ትልም አለው፡፡ከነዚህም አንዳቸው ያይላል፡፡ አንተ ትልምህንና ፍላጎትህን ማሸነፍ ከቻልከ ከመላኢካ የበለጠ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ትሆናለህ፡፡ ትልምህና ፍላጎትህ ካሸነፉ ግን አንተ ከውሻ የበለጠ ዝቅ ያለ ደረጃ ላይ ትሆናለህ
➋ ነፍስያህን ተጠንቀቃት፤ምክንያቱም በርሷ ቢሆን እንጂ ምንም መጥፎ ዕድል አያገኝህምና፡፡ስለዚህ ከርሷ ጋር በጭራሽ አትታረቅ፡፡በአላህ እምላለሁ! ክብሯ የሚገኘው ለአላህ እጅ በመስጠቷ ነው፡፡ ልዕልናዋ የሚገኘው ከመተናነሷ ነው፡፡ሕዳሴዋ የሚገኘው ከስብራቷ ነው::ምቾቷ የሚገኘው ከፈተናዎቿ ነው፡፡ ደህንነቷ የሚገኘው ከአላህ ፍራቻዋ ነው፡፡እንዲሁም ደስታዋ የሚገኘው ከሐዘኗ ነው፡፡
➌ ለአላህ ጥራት ይገባው! ውጫዊ ገፅታዎቻችሁን በተቅዋ ልብሶች አስጊጦላችኋል፤ውስጣዊ ማንነቶቻችሁ ለከንቱ ስሜቶች እጅ በሰጠቡት ጊዜ፡፡ እናም ልብሶቻችሁ የትም ባወዱ ጊዜ፣የከንቱ ፍላጎቶቻችሁ ተፅዕኖ ብቅ ይላል፡፡ታማኝ ሙእሚኖች ግን ከዚያ ችላ ይላሉ፡፡ክፉ ሠሪዎች ግን ወደዚያ ያዘነብላሉ፡፡
➍ አንድ ሰው የእዝነት የለሽ ሚስት ባለቤት፣ምህረት የማያደርግ ልጅ አባት፣ የማይታመን ጎረቤት፣ ምንም ምክር የማይለግሰው ጓደኛ፣በተሳሳተ መንገድ የሚፋረደው የስራ አጋር፣ጠላትነቱ ፈፅሞ የማይቋረጥ ባላንጣ፣ ወደ ከፋት የተዘነበለች ነፍስያ፣ የተጋጌጠች ዓለም፣ ከንቱ ፍላጎቶች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስሜቶች፣ ከባድ ንዴት፣ የሰይጣን ሽንገላ እና የቁጥጥር ድከመት ባለቤት ሆኖ ሳለ እንዴት ነው ደህንነት ሊሰማው የሚችለው? በርግጥ አላህ እርሱን ከታደገውና ከመራው እነዚህ ሁሉ ችግሮች በቁጥጥሩ ሥር ይሆናሉ፡፡ ግን አላህ እርሱን ችላ ካለውና ከተወው፣ እርሱን ለራሱ ትቶት፣ እነዚህ ሁሉ ጭንቀቶች እርሱን ያጠፉታል፡፡
➎ ባሪያው ከፊት ለፊቱ የሚቆምለት ጌታ አለው፤ ብሎም የሚኖርበት ቤት አለው፡፡ ይህም በመሆኑ እርሱ ከአላህ ጋር ከመገናኘቱ በፊት የአላህን ውዴታ ማግኘት አለበት፤ ልክ ወደቤቱ ከመግባቱ በፊት የቤት ዕቃውን ማስገባት በዕቃ መሙላት እንዳለበት ሁሉ፡፡
➏ / መሬት ሰፊ ናት፡፡በርሷ ላይ የሚተከልባትን ማንኛውንም ነገርም ትቀበላለች፡፡አንተ የእምነትና የተቅዋ ዛፍን ከተከልክባት የአኼራን ጣፋጭነት ትሰጥሀለች፡፡ የድንቁርናና የስሜትን ዛፍ ከተከልከባት እርሷም መራራ ፍሬ ትሰጥሀለች፡፡
➐/ አላህ የመጪውን ዓለም ደስታዎች ቃል ገብቶላችኋል፡፡ስለዚህ ችኩል አትሁኑ፡፡እነርሱንም በዚህች ዱንያዊ ሕይወት ውስጥ አትፈልጉ፤ ልክ እናንተ ሰብሎችን ከመሰብሰቢያ ጊዜያቸው በፊት እንደማትቆርጧቸው ሁሉ፡፡ከቆያችሁ እነርሱ ለናንተ በላጭ ይሆናሉ፡፡ልክ እንደዚሁ የመጪው ዓለም ደስታዎች እጅጉን በላጮች ናቸው፡፡»
📌በቀጣይ ክፍል ኢትዮጲያ እንዴት ዝሙት እንደተስፋፋ እና አዲስ አበባ ላይ ያሉ የተደበቁ የዝሙት እዉነታዎች ላይ እንዳስሳለን...
📚#ምንጭ☞65%በዝሙት አንዘምን መፅሀፍ
#ምዕራፍ ➌ይቀጥላል.....
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6161